Get Mystery Box with random crypto!

ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። የፈተና አሰጣጡን | Ministry of Education Ethiopia

ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የፈተና አሰጣጡን ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅ ከዩኒቨርስቲዎች ታዛቢዎች መመደባቸውም ተገልጿል ።
..............................................
የካቲት 5/2016ዓ.ም (ትሚ)ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከነገ የካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጅና(ፒኤችዲ) የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ተግባራዊ መደረጉንና በመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ድንጋጌ መሠረት ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145 ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች እንደሚፈተኑ ተናግረዋል።

የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል በሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ታዛቢዎችን መመደባቸውንም ዶ/ር ኤባ ገልጸዋል ።

የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚው ታዛቢዎቹ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተመለመሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ