Get Mystery Box with random crypto!

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚተገበሩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች እውቀት-መር እና አሳታፊ በሆ | Ministry of Education Ethiopia

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚተገበሩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች እውቀት-መር እና አሳታፊ በሆነ አግባብ መተግበር እንዳለባቸው ተገለጸ።

………………………………………. // ……………………………….
የካቲት 4/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚተገበሩ የማህበረሰብ አገልግሎት እና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሁሉም ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጉድኝት የስራ ኃላፊዎች ስልጠና እየሠጠ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር የምርምር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ሥራ አሥፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር ሥልጠናውን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተደራሽነት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራ ቢሆንም ከምርምር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች አንጻር የተሻለ ስራ መስራት የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ሰለሞን አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት እና የአቅም ግንባታ ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑን ጠቅሰው የዚህ ስልጠና ዓላማም በተለይም በማህበረሰብ ጉድኝት ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሻለ አሰራር ስራ እንዲዘረጉና እንዲተገብሩ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው በኮሎራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አሠፋ ገብረ-አምላክ የተሰጠ ሲሆን በሀገራችን የሚተገበሩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ከአለም-አቀፍ ተሞክሮ አንጻር መቃኘት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

ሙሉ ዜናው https://www.facebook.com/share/p/KwN95ba3WXkQaw9h/?mibextid=2JQ9oc