Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች 128ኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ሁነቶች አከበሩ፡፡ | Ministry of Education Ethiopia

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች 128ኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ሁነቶች አከበሩ፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የካቲት 21/2016 ዓ.ም(ትሚ) «ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!»በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ128ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ሰንደቅ አላማ በጋራ በመስቀልና ሊሎች መርሃግብሮች አክብረዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ችቦ እና አርማ በመሆኑ የድሉን እሴቶችና ቱሩፋቶች በሚገባ ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንደሃገር የዓድዋ ድል መታሰቢያ የሆነው አድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ተጠናቆ በተመረቀበት የሚከበር በመሆኑ ድሉን ድርብ ያደርገዋልም ብለዋል

ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የመስቀል መርሃ ግብሩን ተከትሎ በማህበራዊ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ሃላፊ አቶ ኡመር ኢማም የውይይት መነሻ ያቀረቡ ሲሆን የህዝቦች አብሮ የመኖርና የመልማት እንዲሁም የሀገርን ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳዮች ላይ ይህ ትውልድ ከአባቶቹ ብዙ መማር እንደሚገባው አመላክተዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://www.facebook.com/share/p/xzABkDHNRqFwizd4/?mibextid=oFDknk