Get Mystery Box with random crypto!

በአፍሪካ 9ኛው በኢትዮጰያ አምስተኛው የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተከ | Ministry of Education Ethiopia

በአፍሪካ 9ኛው በኢትዮጰያ አምስተኛው የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተከበረ፡፡
=============================

የካቲት 22/2016ዓም (ትሚ) በአፍሪካ 9ኛው በኢትዮጰያ አምስተኛው የትምህርት ቤት ምገባ ቀን " ለሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ ለተሻለ ትውልድ ግንባታ!!" በሚል መሪ ቃል በሀገር ደረጃ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተከበረ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበዓሉ ላይ ተገኝተው የትምህርት ቤት ምገባ ወጪ ሳይሆን በመጪው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ የሚደረግ አዋጭና ዘላቂ የሰብዓዊ ልማት ኢንቨስትመንት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መርሃ-ግብሩ በአግባቡ ከተተገበረ የልጆችን አካላዊና አዕምሮኣዊ ዕድገት በማፋጠንና ጤንነታቸውን በመጠበቅ የተማሪዎችን የትምህርት ውጤታማነት እንዲሻሻል በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የትምህርት ቤት ምገባ እንደሃገር በመንግሰት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ያለና ከ6.2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ተጠቃሚ ያደረገ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የመንግስት አካላት፣የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶችና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ታዳጊዎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ለመገንባት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍ እያበረከቱ ላሉት አስተዋጽኦ አመስግነው በቀጣይም ድጋፋቸውን ይበልጥ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሙሉ ዜናው

https://www.facebook.com/share/p/JX9bp4LQb6KfhXr7/?mibextid=Nif5oz