Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_moe — Ministry of Education Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81.50K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-11-14 11:46:11
20.7K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-14 11:30:39
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከፈተና ባሻገር ምን እየተሰራ ነው?

.............................................

ትምህርት የሰለጠነና የበቃ የሰው ኃይል በማቅረብ ረገድ የማይተካ ሚና አለው፡፡ ይህም የሁሉም ዘላቂ ልማት ቁልፍ መሣሪያ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በሀገራችን ትምህርትን ለሁለንተኛዊ ዕድገት ከመጠቀም ይልቅ የፖለቲካ ትግል መሳሪያ አድርጎ ለመጠቀም የሚደረግ ትንቅንቅ የፈተና አስተዳደር ሥራን ውስብስብ ከማድረጉም ባሻገር ከፍተኛ ጉዳትም ሲያደርስ ቆይቷል፡፡

የፈተና ኩረጃና ስርቆት የተለመደ እየሆነ በመምጣቱ በተማሪዎችን ዘንድ የመማር፣ የመመራመር፣ ተግቶ የማንበብ ፍላጎት መቀነስ እንዳሳየ የትምህርት ምዘና ጥናቶች ያመለክታል፡፡ ይህም በትምህርት ስርዓቱ ውስጥም ፈጠራና ልህቀትን እያቀጨጨው የመጣ ከመሆኑ በተጨማሪ የትምህርት ፍትኃዊነትንም ጎድቷል፡፡ ይህን ችግር የተገነዘበው መንግስት ችግሩን በዛላቂነት ለመፍታት በርካታ የሪፎርም ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡ የፈተና አስተዳደር ስርዓትን በተለይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናን በሂደት እያጋጠመው የመጠውን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሠራ ቆይቷል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማንበብ

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0rznMUMuRL1UshMZ41aMdz8egFw4JXPg8HncvTdRPrMVV8p5T4J1sK9HX3VjqNxz9l&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
23.4K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-13 18:56:18
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነገ ህዳር 4 ቀን ፣ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚካሄደው የምክር ቤቱ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በመገኘት ክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 28 ቀን፣ 2016 ዓ/ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ያቀረቡትን የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ።

በዚህም መሠረት ትምህርትን አስመልክቶ የሚሰጡትን ምላሽ የምናቀርብ መሆኑን እየገለጹን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።
16.0K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 09:50:36
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ-አይቢኢ የቦርድ ፕሬዝዳንት ስቬን ኦስትቬት ጋር ተወያዩ።
---------------------------------
ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር እና የዩኔስኮ ብሄራዊ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ከአለም አቀፍ የትምህርት ቢሮ (UNESCO-IBE) ቦርድ ፕሬዝዳንት ስቪን ኦስትቬት ጋር በፈረንሳይ በሚገኘው የዩኔስኮ ዋና መስሪያቤት የጎንዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የትምህርት ሥርዓት ለማሻሻል እና ለማዘመን ያከናወናቸውንና በመተግበር ላይ ያሉ የለውጥ ተግባራትን አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያ በተለይም በዘርፉ በተለዩ የትምህርት መስኮች ላይ የውጭ ልምድ እንደሚያስፈልጋት በአጽናኦት የተናገሩ ሲሆን የዩኔስኮ-አይቢኢ የቦርድ ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው የትምህርት ስርዓቱን በአዲስ መልክ ለማሻሻልና ለማዘመን ሚኒስቴሩ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀው ቢሮው ጥረታቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02roy5vu64ni87iEN6VtDtpgDqnGQNtVxdExXfKXYMZcxA9iYqQR4QLHSGMiybQr3Xl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
14.7K views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-08 19:33:08
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ ከIIEP-UNESCO ዳይሬክተር ጋር ውይይት አካሄዱ
...................................................................
በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ከተማ እየተካሄደ ባለው 42ኛው የዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን የትምህርት ሚኒስትርና የብሔራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ ከIIEP-UNESCO ዳይሬክተር ማርቲን ቤናቪድሠን ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ሁለቱ ወገኖች በትምህርት ሚኒስቴር ፣ አዲስ የተዋቀሩ ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች እና የዩኒቨርሲቲ የእቅድ ዝግጅት ባለሙያዎችን አቅም መገንባት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም በከፍተኛ ትምህርቱ ዘርፍ ያሉትን የፖሊሲ ማዕቀፎችና በተለይም ዩኒቨርስቲዎችን በትኩረት መስክ መለየት እና የከፍተኛ ትምህርት ተቆማዊ ነፃነትን ማረጋገጥ ላይ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎች ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ይህን ተከትሎም የIIEP-UNESCO ዳይሬክተር ማርቲን ቤናቪድሠን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

በውይይቱ መጨረሻም ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን ትብብር በማደስና በማጠናከር በትምህርቱ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን ከመግባባት ላይ ደርሠዋል።
20.3K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-08 16:35:37
ኢትዮጵያ በ42ኛው የዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች።
.............................................
ጥቅምት 28/2016 ዓ/ም (የትምህርት ሚኒስቴር) በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ከተማ ትናንት በተጀመረው 42ኛው የዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ላይ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስትርና የብሔራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል::

እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 7 እስከ 22 ቀን 2023 በሚካሄደው ኮንፈረንስ ላይ በአገራችን ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት በዩኔስኮ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት የብሔራዊ ፓሊሲ ንግግር ፣ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የአገር መሪዎች ፣ መንግሥት እና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስትሮች የሚሳተፉበት ስብሰባ፣ 13ኛው የወጣቶች መድረክ እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ1972 የተደረገው የዓለም ቅርስ ኮንቬንሽን አባላት ጠቅላላ ጉባኤ በኮንፈረንሱ የሚጠበቁ ልዩ ስብሳባዎች ናቸው።

ክቡር ሚኒስትሩ ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎን ከተለያዩ አገራት ሚኒስትሮች እና የዩኔስኮ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ።
ሙሉ ዜናው
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0FLZLSMcj9ZEaSM6g6ThCJRpFXtrev5k9Auhzh9zUCN1Na2J6gSpediZy7tSmUr6Xl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
20.6K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-07 21:20:18
"ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል" ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ
.............................................
ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት የሰው ሃይል አደረጃጀትና የበጀት አመዳደብን የተመለከተ አውደ ጥናት  አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል ብለዋል።

እንደ ትምህርት ሴክተር ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ትምህርት እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተው ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት ከማቅረብ አንፃር በርካታ ሥራዎች እንደሚጠበቁም አብራርተዋል።

ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው በሀገራችን ልማት የበኩላቸውን መወጣት ይችላሉ ያሉ ሲሆን  ለሁሉም ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትና ሥልጠና በፍትሃዊነት ለመሥጠት የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ስትራቴጂ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን አደረጃጀቱን ማስተካከልና  በበጀት  መደገፍ እንደሚገባ አንስተው ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮሐንስ ወጋሶ በበኩላቸው በልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ውስብስብ ችግሮች መኖራቸውን አንስተው ለነዚህ ችግሮች ትክክለኛ መፍትሄ አስቀምጦ መሥራት ይገባል ብለዋል።
18.3K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 19:39:49
የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መከታተያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።
==============//==
ጥቅምት 23/2016 ዓ .ም (ትምህርት ሚኒስቴር ) በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም መከታተያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር ) እንደገለጹት በ2016 በግልና የመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ /Remedial Program / የሚከታተሉ ተማሪዎች መቁረጫ ነጥብ እንደተፈተኑት የትምህርት ዓይነት ብዛት 30% እና ከዚያ በላይ ሆኗል ።

በዚህም መሠረት በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር የመቁረጫ ነጥብ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 መሆኑን አስታውቀዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 የማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 መሆኑን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ታዳጊ ክልሎች ተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 መሆኑን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች መግቢያ 192 ታዳጊ ክልሎች ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች መቁረጫ180 መሆኑን አመልክተዋል።

ሙሉ መረጃው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0DDFte8gZynMFNPjAJqQ3E4BgCn54bGD3wY5sX2sjkPmbtaJFBRF6xjnxaR4X2hiSl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
30.6K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 17:14:43
#የዩኒቨርስቲ ምደባ ማስታወቂያ

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለምትከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገልጻለን።

Website:  https://result.ethernet.edu.et/
Telegram bot: @moestudentbot
35.2K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-01 09:30:13
#የዩኒቨርስቲ ምደባ

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ

የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-

1. 1000 ለሚሆኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፡- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

2. ውጤት፡- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

3. የዩኒቨርሲቲ ምርጫ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡ መረጃው የተሰበሰበው https://portal.etherenet.edu.et ላይ ነው፡፡

4. በተማሪዎች የተመረጡ ተቋማት ያላቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5. ጾታ ፡- በተቋማት የጾታ ተዋጽኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋጽኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል፣

እስከ ተራ ቁጥር 11 የተዘረዘረውን ሙሉ ማብራርያ ለማግኘት
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02PHJz75Box4aFYmLGnxniAnWrJZMfPeiHk64ANXYnsUwwfMDbav8bBUbr587y19jCl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO!
27.0K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ