Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 82.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-09-21 12:31:29
የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ የትምህርትን መሰረተ ልማት ማሻሻል የቀጣዩን ትውልድ የወደፊት እድል ማሻሻል መሆኑን ገለጹ።
---------------------------------//----------------

መስከረም 10/2016ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር ) የትምህርት ሚኒስትሩ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሜሪካ ኒውዮርክ መስከረም 08/2016 ዓ.ም ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳትፈዋል ።

መድረኩ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድህነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና በተለያዩ የአለም ክፍሎች የማያቋርጥ ግጭትን እና አለመረጋጋትን ጨምሮ ውስብስብ ፈተናዎች ያሉበት በመሆኑ የ2030 የዘላቂ ልማት ግብ (SDG) አጀንዳ እና ሌሎች የጋራ ተግዳሮቶችን በዘላቂ ልማት ለመቅረፍ አገሮችን አንድ ለማድረግ ያለመ ነው።

በዚህም ሚኒስትሩ የተባበሩት መንግስታት ትምህርት በዲጅታል ዘመን ውስጥ ለልማት፣ ለፍትሃዊነት፣ ለሠላምና ለደህንነት የሚያግዝ ኢንቨስትመንት በሚል በኒውዮርክ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገኝተው ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ላይ በተደረገ የጎንዮሽ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድርግ ስለ ቀጣዩ ትውልድና አለም ኢንቨስት ማድርግ ነው ያሉ ሲሆን እንደ ሀገርና መንግስት የተለያዩ ሪፎርሞችን በትምህርት ላይ እያካሄድን እንገኛለን ብለዋል።

ሙሉ ዜናው
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02WjS3oZmg1jvXcBisePJgZKm8rygbdcAax743BJxEAXFAhcVbY7Y8pfsATwJqWKFwl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
17.6K viewsedited  09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-19 12:44:05
17.4K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-16 14:02:29
የአጠቃላይ ትምህርት የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር

ማሳሰቢያ :- ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረግ
18.8K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-14 08:24:43
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የብሄራዊ መታወቂያ መርሃ-ግብር በጋራ ዲጂታል የተማሪዎች መለያ ስርዓት (የተማሪ መታወቂያ) ተግባራዊ አደረጉ
17.9K views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-11 18:26:43
የ2016 ዓ.ም የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (GAT) ከመስከረም 21- 23/2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በበየነ መረብ ይሰጣል
...................................................
ጳጉሜ 06/2015 ዓ .ም (የትምህርት ሚኒስቴር ) በ2016 ዓ.ም  የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና አፈጻጸም  የሚመለከት መረጃ 

https://shorturl.at/qAE56

ያገኛሉ
15.6K viewsedited  15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-11 13:45:36
14.5K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 20:10:33
የሕዳሴው ግድብ አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ !


የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
16.5K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 19:58:55
"አዲሱ ትውልድ አገሩን የሚወድ  የሚያነብ የሚመራመርና ችግር ፈቺ ሊሆን እይገባል" ክብርት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ጳጉሜ 5/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) ክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የትውልድ ቀንን በማስመልከት ባስተላለፋት መልዕክት ትውልዱ  በትምህርት የታነጸ ታሪክና ባህሉን የሚያውቅና  ስለአገሩ የሚቆጭ ሊሆን ይገባል። 

ትውልዱ  የማንበብ ባህል በማዳበር ችግርፈቺ ሆኖ  አገሩን የሚያሻግር  ሊሆን እንደሚገባም ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የታደለች መሆኗን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቷ ተስፋ ሰጪ የፈጠራ ችሎታውን  በማዳበር አገሩን መለወጥ እንዳለበት ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው አዲሱ ትውልድ በማንበብ በማሰላሰልና ምክንያታዊ በመሆን አገሩን ሊያሻግር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አገርን መውደድና መጠበቅ  ፣ ስልጣኔን  ማስቀጠል እንዲሁም  የዓለምን ፈተና መሻገር የሚችል መሆን እንደሚጠበቅበት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ተናግረዋል።

በእሳቸው ዘመን የነበረው ትውልድ ለስልጣኔ  የሚቆጭ ግብረገብ ፣ በማንበብና በማሰላሰል የሚያምን እንደነበረም ፕሮፌሰር ብርሀኑ  ጠቁመዋል።

በሥነ ስርዓቱ ላይ ክቡራትና ክቡራን ሚኒስትሮች ሚኒስትር ዴኤታዎች የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶችና ሌሎችም  ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዓሉን በጋራ ያዘጋጁት የትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርና የፍትህ ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ነው።
14.9K views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-27 11:13:49
"2016 በጀት ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ሪፎርሞች አጠናክረን የምንቀጥበት ነው" ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ -የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ

....................................................................................

ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የ2015 ትምህርት ዘመን ሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መርሃ ግብር ተጠናቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንደገለጹት ባለፉት አምስት ዓመታት የትምህርት ሴክተሩ ቁልፍ ችግር ተብሎ የተለየው የትምህርት ጥራትና ተገቢነት ጉዳይ ሲሆን ይህንንም ለማሻሻል በ2015 ዓ. ም በርካታ ሪፎርሞች ተተግብረዋል።

የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ መሰረት  የዩኒቨርሲቲ መነሻ የትምህርት ቆይታ ጊዜ ከሦስት ወደ አራት ዓመት የማሳደግ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን በትኩረትና በተልዕኮ የመለየት፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚደረገውን የመግቢያ ፈተና ጥራት ማስተካከል፣ የዩኒቨርስቲ የመውጫ ፈተናን መተግበር፣ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓት የመዘርጋትና አዋጁን የማጽደቅ እንዲሁም ተያያዥ የሆኑ ተጨማሪ የሪፎርም ሥራዎች ጥራት ላይ ማተኮር እና የውስጥ ግብዓቶችን ማሻሻል ከተወሰዱት እርምጃዎች መካከል መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://www.facebook.com/100064682287722/posts/pfbid02wsovyftriJ92fP6HQCW6nwCxHAfh6QZnEZMguViFLC9khQcUiAURgnYcTQHcoFGhl/?mibextid=9R9pXO
13.3K views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-25 18:26:02
"ቴክኖሎጂ ያመጣውን ጸጋ በመጠቀም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እየተሰራ ነው" ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ
.............................................
ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴርን) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የ2015 የትምህርት ዘመን አፈጻጸም ግምገማና የ2016 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ መርሃ-ግብር የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች በተገኙበት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በዛሬ ውሎ የ “e - Learning for Strengthening Higher Education (e-SHE)” https://e-she.ethernet.edu.et/ ፕሮጀክት አፈጻጸም ተገምግሟል።

በመርሐግብሩ መክፈቻ ቁልፍ መልእክት ያስተላለፉት የእለቱ የክብር እንግዳ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ትምህርትን በቴክኖሎጂ መደገፍ በፖሊሲ ደረጃ መካተት እንዲችል እየተሰራ ነው ብለዋል።

ለተፈጻሚነቱም ከወዲሁ የመምህራን ክህሎት ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ።

ዲጂታል ትምህርት የዲጂታል ኢትዮጰያ 2025 የሰው ሀይል ልማትን ለማሳደግ የተያዘው እቅድ ለማሳካትም እገዛ እንዳለው ገልጸዋል።

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02BJNLA1P2yFQArqJivVSt3HYchXZefbe64AAjhoGLfuP4Q5MwEZfvAkymq9iwC1cSl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
13.2K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ