Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ የትምህር | Ministry of Education Ethiopia

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ የትምህርትን መሰረተ ልማት ማሻሻል የቀጣዩን ትውልድ የወደፊት እድል ማሻሻል መሆኑን ገለጹ።
---------------------------------//----------------

መስከረም 10/2016ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር ) የትምህርት ሚኒስትሩ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሜሪካ ኒውዮርክ መስከረም 08/2016 ዓ.ም ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳትፈዋል ።

መድረኩ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድህነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና በተለያዩ የአለም ክፍሎች የማያቋርጥ ግጭትን እና አለመረጋጋትን ጨምሮ ውስብስብ ፈተናዎች ያሉበት በመሆኑ የ2030 የዘላቂ ልማት ግብ (SDG) አጀንዳ እና ሌሎች የጋራ ተግዳሮቶችን በዘላቂ ልማት ለመቅረፍ አገሮችን አንድ ለማድረግ ያለመ ነው።

በዚህም ሚኒስትሩ የተባበሩት መንግስታት ትምህርት በዲጅታል ዘመን ውስጥ ለልማት፣ ለፍትሃዊነት፣ ለሠላምና ለደህንነት የሚያግዝ ኢንቨስትመንት በሚል በኒውዮርክ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገኝተው ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ላይ በተደረገ የጎንዮሽ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድርግ ስለ ቀጣዩ ትውልድና አለም ኢንቨስት ማድርግ ነው ያሉ ሲሆን እንደ ሀገርና መንግስት የተለያዩ ሪፎርሞችን በትምህርት ላይ እያካሄድን እንገኛለን ብለዋል።

ሙሉ ዜናው
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02WjS3oZmg1jvXcBisePJgZKm8rygbdcAax743BJxEAXFAhcVbY7Y8pfsATwJqWKFwl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO