Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 82.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-06-01 09:15:19
የ2015 ዓ.ም ሀገራዊ የመመሰጋገንና የመደናነቅ ቀን አከባብርን አሰመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ግንቦት 23/2015 ዓ.ም:-

የ2015 ዓ.ም የመመሰጋገንና የመደናነቅ ቀን ግንቦት 25/2015 ዓም. በሚሊኒዬም አዳራሽ ይከበራል
.............................................
የ2015 ዓ.ም የመመሰጋገንና የመደናነቅ ቀን ግንቦት 25/2015 ዓ.ም በሚሊኒዬም አዳራሽ የትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ይከበራል።

የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከመደበኛ የመማር ማስተማር ሥራዉ በተጨማሪ ሀገር ተረካቢው ትዉልድ በሥነ-ምግባር የታነጸና መከባበርና መመሰጋገንን እሴቱ ያደረገ ሆኖ እንዲቀረጽ የግብረገብ ትምህርትን በሥርዓተ ትምህርቱ በማካትት የመደበኛ ትምህርት አካል አድርጎ እየሠራ ነው። ከተለያዩ ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ድርጅቶች ጋርም በቅንጅት እየሠራ ይገኛል።

ቅን ኢትዮጵያ ማኅበር ከተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋርም ከ2013 ዓም ጀምሮ በየዓመቱ የመመሰጋገን ቀን በመሰየም በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። ላለፉት ሁለት ዓመታትም ሀገራዊ የመመሰጋገን ቀንን በተለያዩ መርሐ-ግብሮች አክብሯል።


ለዘንድሮም ለማክበር ጥሪዎችን ለሚመለከታቸው አካላት አስተላልፏል። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል በወዳጅነት አደባባይ ለማክብር የተያዘው መርሐ ግብር በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሚሊኒዬም አዳራሽ ተቀይሯል።

በመሆኑም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ግንቦት 25/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 በሚሊኒዬም አዳራሽ እንድትገኙ በአክብሮት እንጠይቃለን።

አስተባባሪ ኮሚቴ!
13.9K views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 08:36:17
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስርን ሊያግዝ በሚችል ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደ
....................................................................................

ግንቦት 22/2015 ዓ.ም፤(የትምህርት ሚኒስቴር) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የምርምር ተቋማትና የኢንዱስትሪዎችን ትስስር ሊያጠናክር በሚችል ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከአስረጂዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱም፤ ከከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱስተሪ ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ረቂቅ አዋጁ ሊያግዝ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎች የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል የምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪዎች በቅንጅትና በትብብር እንዲሰሩ ለማስቻል ረቂቅ አዋጁ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምር እና ማህበራዊ ጉድኝት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸው፤ የረቂቅ አዋጁ ዓላማ ኢንዱስትሪዎች ምርታማነት እንዲጨምሩ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማጠናከር ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት፡-

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0Lfe83TXPVTzY6SbmoHhvzngxtfSuTrGXnvH2mhvFEMNWyQzvksGena1Ap8meQf4Wl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
15.1K views05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:07:44
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ግምታቸው ከ5.8 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የተለያዪ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ
............................................
ግንቦት 7/2015ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር )የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ግምታቸው ከ5.8 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የትምህርት ቁሳቁሶችን አበርክቷል።

የተደረገው ድጋፍም የኮምፒውተር ፣ የመማሪያ ደብተር፣ እስክሪፕቶና ሌሎች መገልገያዎች ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ገላና ወልደሚካኤል (ዶ/ር) በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት የትግራይ ክልል ተማሪዎች ላለፋት 3 ዓመታት ከትምህርት ገበታ መራቃቸውን አስታውሰው አሁን ባለው የሰላም ስምምነት ወደትምህርት ተመልሰው ማየት እንፈልጋለን ብለዋል።

የትምህርት ቢሮው ያደረገው ድጋፍም ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝ መሆኑን ገልፀዋል።

ከትግራይ ክልል የሀብትና የትምህርት መሣሪያዎች አሰባሳቢ ኮማቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ አረጋዊ
በጦርነቱ ትምህርት ቤቶችና የትምህርት መሠረተ ልማት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መውደሙን ገልጸው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።
በቀጣይም ሌሎች አካላትም ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ ህፃናትን ወደ ትምህርት የመመለስ ስራውን እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
7.7K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 11:56:05
"በትምህርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም ይገባል" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
-----------------

ግንቦት7/2015ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤትና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና ውጤት የጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ የለውጥ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን ጠቅሰው  በዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ሥርአቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም ያሉት ሚኒስትሩ በሚታዩት ውጤቶች ሳንደናገጥ ዘርፉን ለመለወጥ ጠንክሮ መሥራት ይገባልም ብለዋል።

የተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ማነስ ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የመምህራን እጥረትና ተነሳሽነት አለመኖር፣ የትምህርት ቤቶች መሠረተልማት መጓደልና ለመማር ማስተማር ምቹ ያለመሆን እንዲሁም የትምህርት ቤቶች አመራር መጓደል ለውጤቱ መውደቅ ምክኒያቶች መሆናቸው በጥናቱ ተመላክቷል።

የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥም የትምህርት ዘርፍ ችግሮችን ፈጥኖ  ማረም እንደሚገባም ተገልጿል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በቀጣይ ወር የሚጀመር ሀገራዊ  ንቅናቄ እንደሚኖር እና ማህበረሰቡን በማስተባበር ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ሥራ እንደሚሰራም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በዚህ ሂደት ወላጆች የትምህርት ቤቶች ባለቤቶች መሆናቸውን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚገባቸውና  ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤት(NLA)  እና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና ውጤት በባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ተጨማሪ መረጃዎችን -https://www.facebook.com/fdremoe/
8.6K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 12:04:32
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የበጀትና የግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃጸም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ
.............................................
ግንቦት 6/2015ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከፌዴራል መንግስት ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም. የተመደበው በጀት እና የግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃጸም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

የኮሚቴው አባላት በምልከታቸውም ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደበው በጀት በተጨባጭ ለታለመለት ዓላማ ስለመዋሉ፣ የውስጥ ገቢን ከማሳደግና ከማስተዳደር፣ የንብረት አያያዝና አወጋገድ፣ በብድር እና በእርዳታ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮግራሞች እና የግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንዲሁም የኦዲት ተግባራት ያሉበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

ምልከታ ከተደረገባቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥም የተማሪዎች ማደሪያ፣ ቤተ-መፃህፍት፣ ካፍቴሪያ እና የመምራን መኖሪያ ይገኙበታል፡፡

ከምልከታው ባሻገርም የኮሚቴው አባላት የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ፣ ዲኖችን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን በአፈጻፀሞቹ ዙሪያ አወያይተዋል፡፡

የቡድኑ አስተባባሪ የተከበሩ አቶ አኔሳ መልኮ ከሁለት አመታት ወዲህ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ለውጥ እየታየ መሆኑን ጠቁመው፤ ለመጣው ለውጥም የአመራሩ ቁርጠኝነትና በትብብር መንፈስ በጋራ መስራቱ ነው ብለዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid027R1ZhA1PQSXe7c3VVysPBWKEJfZtv25Wy8QF4FEbEm3LZXUQAkL84u95MvDHtZptl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
9.0K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 20:18:01
4.4K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:30:32
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተለያዩ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
--------------------------

ግንቦት 2/2015ዓም .(የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር የፓናል ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ ላይ እያደረገችው ያለውን ለውጥ እና ስራ አብራርተዋል።

በአጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም በመድረኩ አንስተዋል።

የአፍሪካ ሚኒስትሮች ውይይትም የተካሄደ ሲሆን አለም አቀፋ የትምህርት ጉባኤ በብሪታኒያ እየተካሄደ ይገኛል።
11.7K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:09:17
በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ክልሎች የሚውል ከ100 ሺ በላይ የሚሆን የመፅሐፍት ድጋፍ ተደረገ።
.................................................

ግንቦት 2/2015ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) ሪቮ ካፕ ፋውንዴሽን ከወንፈል ተራድኦና አዲስ ተስፋ ለጅማ የተባሉ  ድርጅቶች ጋር በመተባበር  በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ክልሎች የሚውሉ  መጽሃፍትን በማሰባሰብ ለትምህርት ሚኒስቴር አስረክቧል።

ድርጅቱ ከ100ሺ በላይ የሚሆኑ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት መርጃ መጽሐፍትን ከአሜሪካ በማስመጣት ነው ድጋፍ ያደረገው።

መጽሃፍቶችን የተረከቡት የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  ሪቮ ካፕ ፋውንዴሽን ያደረገው ድጋፍ የዛሬና የነገ ትውልዶችን ለመገንባት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጠቅሰው  ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እንደዚህ አይነት ድጋፎች የሚደረጉት ትውልድ ላይ በመሆናቸው ሌሎች ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሠል ድጋፎችን በትምህርት ዘርፉ  ማድረግ  ይገባቸዋል ብለዋል።

በቀጣይ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ሀገራዊ ንቅናቄ መድረክ እንደሚያዘጋጅ ጠቅሰው  እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለተማረበት ትምህርት ቤት በአቅሙ ልክ ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

ሙሉ ዜናውን

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02dXH48QP4zhXmhT66u7VecJgAQBsymrcTnAXoys2UScNcyJ9pfzEDmgrF4s75uPcSl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
10.1K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 10:13:33
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ
---------------------
ግንቦት 1/2015ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በእንግሊዝ እየተካሄደ በሚገኘው አለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በመድረኩም የሁሉም ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።

ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎን
ከብሪታኒያ የልማትና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አንድሪው ሚቼል እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የልጃገረዶች ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ከሆኑት ሄለን ግራንት ጋር በትምህርት ዘርፍ ያለውን ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የማሻሻያ ስራዎችን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑንም ተናግረዋል።

ሄለን ግራንት በበኩላቸው ብሪታኒያ የሴቶች ትምህርት ሊሻሻል በሚችልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

ሁለቱ አካላት በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን አንስተው በትኩረት መምከራቸውን በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

የዘንድሮው የትምህርት ጉባኤ አዲስ ጅማሮ፡ የመማር ባህልን ማሳደግ፣ የመቋቋም አቅምን መገንባት፣ ዘላቂነትን ማሳደግ። በንድፍ ሃሳብ የተደገፈ ጠንካራና የተሻለ ትምህርት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።
11.6K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 09:15:00
ከትምህርት ተቋማት መረጃ ለማሰባሰብ የሚረዳ ድረ-ገጽን መሠረት ያደረገ ዲጂታል መተገበሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ተደረገ
-------------------------------------------
ሚያዝያ 30/2015 ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር)የትምህርት ተቋማት መረጃ ለማሰባሰብ የሚረዳ ድረ-ገጽን መሠረት ያደረገ ዲጂታል መተገበሪያ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን በአጠቃቀሙ ላይ በተግባር የተደገፈ ሥልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው የተሰጠው ከመምህራን ኮሌጆች ለተውጣጡና ከመረጃ ጋር ተያያዥነት ላላቸው የትምህርት ባለሙያዎች ነው።

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓትና ኣይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስብ ለማ ዲጂታል መተግበሪያው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ከተቋማቱ ጋር በበይነመረብ (በኦንላይን) የሚያገናኝ መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም መረጃዎችን በየፈርጁ እንዲሁም በተቋም ደረጃ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ በፍጥነት ተንትኖ መረጃው ለሚፈለገው ዓላማ በግብዓትነት እንዲውል የሚያስችልና ለአጠቃቀም ቀላልና ቀልጣፋ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቴክኖሎጂው ከዚህ በፊት የነበረውን መረጃን በወቅቱና በጥራት ሰብስቦና ተንተኖ ለሚፈልገዉ ግብዓት እንዲውል ማቅረብ ያለመቻል ዉስንነቶችን በሚቀርፍ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የዲጂታል መተግበሪያው ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ሆነ ወደ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መረጃ ለሚልኩ ተቋማት በየጊዜው የተላከውን መረጃ ተንትኖ የሚያስቀመጥበት በቂ የማከማቻ ቦታ ያለው መሆኑም ተገልጿል።

በመረጃዎች ላይ ማስተካከያ ካለም ማስተካከያ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነና የተደረገው ማስተካከያንም በቀጥታ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተንትኖ የሚያስቀምጥ መሆኑን ሰራ አስፈጻሚዉ አስረድተዋል።
11.5K views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ