2023-06-05 19:15:24
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት ስኮላርሺፕን በተመለከተ:-
..................................................
ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በ2014 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሠዱትና ከፍተኛ ውጤት ካስመዝገቡት ውስጥ 273 ተማሪዎች ስኮላርሺፕ እንደሚሠጥ መገለጹ ይታወቃል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ:-
1. የተማሪዎች ቁጥር (ተፈታኞች)ለምን ከ273 በላይ ሆነ
2 .ከፍተኛ ውጤት ያለመጡ ተማሪዎች እንዴት ለፈተና ተቀመጡ የሚሉ ጥያቄዎች እየቀረቡ ይገኛል።
ስለሆነም ይሄን ጉዳይ ግልጽ ማድረግ ስለሚያስፈልግ
1. ለፈተና የተጠሩትን ቁጥር በተመለከተ:-
ስኮላርሺፑን የሠጡት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ባላቸው አሠራር መሠረት 273 ለስኮላርሽፕ ብቁ የሚሆኑ ተማሪዎች ለማግኘት ከፍ ያለ ቁጥር ማለትም 500 የሚሆኑ ተማሪዎች(ተፈታኞች) ለፈተና እንዲቀመጡ ስለጠየቁ ከ273ቱ ቀጥሎ ያሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለፈተና እንዲቀርቡ የተደረገ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
2.ከዚህ በመንግስት ለመንግስት ከተገኘው ስኮላርሽፕ ውጭ አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ኢምባሲ በኩል ስኮላርሺፕ የተመቻቸላቸው ሌሎች ተማሪዎች ያሉ ሲሆን ይህም በመንግስት በኩል ከተገኘው የ273 ስኮላርሽፕ ውጭ መሆኑን እንዲታወቅ እንፈለጋለን፡፡
በመጨረሻም ለሁለቱም አይነት ስኮላርሽፕ እድሎች የተለዩት እጩዎች በጋራ ፈተና እየወሰዱ እንደሆነ ማህበረሰቡ እንዲረዳ እንፈልጋለን፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር !
ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም.
9.1K views16:15