Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_moe — Ministry of Education Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81.50K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 36

2022-05-06 17:10:17
ማስታወቂያ

በ2014 ዓ.ም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ
----------------------------------------

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት አምጥታችሁ በየዩኒቨርሲቲው የተመደባችሁ ተማሪዎች ምደባውንና የተለያዩ ጉዳዮችን ተከትሎ ያላችሁን ቅሬታ በኦንላይን ስንቀበል መቆየታችን ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ለቀረቡት ቅሬታዎች በሙሉ ተገቢውን ምላሽ ሰጥተን የጨረስን ስለሆነ ወደ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ዩኒቨርሲቲዎቹ በሚያደርጉት የጥሪ መርሃ-ግብር መሰረት በየተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ አስፈላጊውን መረጃ አሟልታችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር
11.0K viewsedited  14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 08:07:17
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1443ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

መልካም በዓል።

ትምህርት ሚኒስቴር
12.1K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:23:50
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ
-----------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ ያቀርባል፡፡
32.7K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 07:59:25
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

መልካም በዓል።

ትምህርት ሚኒስቴር
15.8K viewsedited  04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 17:38:03
ትምህርት ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ።
----------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ በትምህርት ልማት ዘርፉ ያከናወናቸውን ተግባራት ከተያዘው ዕቅድ አንፃር ለአጠቃላይ ሠራተኛው ያቀረበ ሲሆን ሠራተኛውም አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡

በግምገማው ወቅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በርካታ ስራዎችን በጥንካሬ ያከናወነ መሆኑ የቀረበ ሲሆን ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በክንውን ድክመት በታየባቸው፣ ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና መሻሻል በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተደርጎ የመፍትሄ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ በትኩረት አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በቀጣይ ሶስት ወራት መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት ሰፊ ውይይት በማድረግ፣ ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በቅንጅትና በመናበብ የትምህርት ልማት ዘርፉን ዕቅዶች ለመተግበርና የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡
14.2K views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 15:30:33
ትምህርት ሚኒስቴር ከክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመወያየት በ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና እርማት እና ውጤት ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ አጠቃላይ መግለጫ።
17.8K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 12:20:36 በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላለፈ።
------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር ተከታታይ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በመግለጫው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና እርማት በተመለከተ ያጋጠመ ችግር አለመኖሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በአብዛኞቹ ክልሎች ያጋጠመ የውጤት መቀነስ መኖሩን እና ትምህርት ሚኒስቴር አማራጮችን የማየት ስራ መስራቱንም በመግለጫው ተነስቷል።

በዚህም በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑ አካባቢዎች እና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡና ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲ መግባት ያልቻሉ ተማሪዎች በ2014ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላልፏል።

ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ ምክኒያት ለተጎዱ ክልሎችእንዲከፋፋል ውሳኔ ተላልፏል።

የፈተና ውጤት ማሳወቅን በተመለከተም በሁለት ዙር ፈተና በመሰጠቱ አጋጥሞ የነበረው ችግር መታረሙ በመግለጫው ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች በስነ-ዜጋ ትምህርት ካጋጠመዉ ችግር ውጪ ሌሎች ችግሮች ባለማጋጠማቸው የሌሎች ትምህርት ዓይነቶችን ውጤት ውድቅ ለማድረግ አሳማኝ የውጤት ትንተና አለመኖሩም ነው የተገለፀው ።

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ የሚያገኙትን በተመለከተ በቀደምት ዓመታት ከመሰናዶ ትምህርት በኋላ ከሚፈተኑ ጋር በማነፃፀር የተፈጠረ አለመረዳት መኖሩንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በቀጣይም እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይፈጠሩ የተጠናከረ ስራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።
15.7K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 16:11:25
አስተያየትዎትን ይስጡን!!

ትምህርት ሚኒስቴር የዋናውን ህንፃ ቀለም ቀድሞ ወደነበረበት ሞዛይክ ቀለም ለመቀየር በማሰብ፣ የስነ-ህንፃ ባለሙያዎችን በማሳተፍ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

የህንፃ ቀለሙን ወደ ቀድሞው ተፈጥሯዊው ሞዛይክ ለመቀየር ያስፈለገበት ምክንያት በዋናነት:-

የትምህርት ሚኒስቴርን የትምህርት ፍልስፍና፥ ራዕይና ተልዕኮ የሚወክል እንዲሆን ለማድረግ፣

ተቋማዊ ባህሪ እንዲኖረው ለማድረግ

ታሪካዊና ከህብረተሰቡ ስነልቦና ጋር የተዋሃደ እንዲሆንና የአካባቢውን ባህሪና የከተማን አውድ ታሳቢ እንዲያደርግ ለማድረግ ነው፣

የሚቀየረው ተፈጥሯዊው ሞዛይክ በዋናነት አብርሆትን ፣ አወንታዊ አስተሳሰብን፣ የላቀ አዕምሮ ባለቤትነትን፣ ምክንያታዊ መሆንን፣ ዕውቀት መጠማትን፣ አዲስ አስተሳሰብን፣ ተግባራዊ መሆንን፣ ፈጠራን፣ መፍትሔ አፍላቂነትን፣ ተስፋንና ደስታን የሚሉ ሐሳቦችን የሚወክሉ ሲሆን፤

የሞዛይኩ ቀለም ሐሳቦች ደግሞ:- ተቋሙ ከሚከተለው የትምህርት ፍልስፍና እና ራዕይና ተልዕኮ ጋር ስምምነት እንዳላቸው እንዲሁም ታሪካዊና ከህብረተሰቡ ስነልቦና ጋር የተዋሃደ ፤ የአካባቢውን ባህሪና የከተማን አውድንም ታሳቢ ያደረገ ውህደት እንዳለው የስነ ህንፃ ባለሞያዎች ይናገራሉ።

በተጨማሪም ተቋሙ የቀድሞውን ተፈጥሯዊ መልክ ይዞ ተጨማሪ አላባውያን እንዲኖሩት ተደርጎም በባለሞያዎቹ ዲዛይኑ ተሰርቶ ለአስተያየት ቀርቧል።

ስለዚህ አስተያየት ያላችሁ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል እና የስነ-ህንፃ ባለሙያዎች ማስታወቂያው ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ በተቋሙ የማህበራዊ ድህረገጽ አማራጮችና በኢሜይል አድራሻ info@moe.gov.et በመጠቀም ሀሳብ አስተያየታችሁን እንድታደርሱን በትህትና እንጠይቃለን፡፡
15.3K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ