Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ። ----------------------- | Ministry of Education Ethiopia

ትምህርት ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ።
----------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ በትምህርት ልማት ዘርፉ ያከናወናቸውን ተግባራት ከተያዘው ዕቅድ አንፃር ለአጠቃላይ ሠራተኛው ያቀረበ ሲሆን ሠራተኛውም አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡

በግምገማው ወቅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በርካታ ስራዎችን በጥንካሬ ያከናወነ መሆኑ የቀረበ ሲሆን ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በክንውን ድክመት በታየባቸው፣ ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና መሻሻል በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተደርጎ የመፍትሄ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ በትኩረት አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በቀጣይ ሶስት ወራት መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት ሰፊ ውይይት በማድረግ፣ ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በቅንጅትና በመናበብ የትምህርት ልማት ዘርፉን ዕቅዶች ለመተግበርና የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡