Get Mystery Box with random crypto!

አስተያየትዎትን ይስጡን!! ትምህርት ሚኒስቴር የዋናውን ህንፃ ቀለም ቀድሞ ወደነበረበት ሞዛይክ ቀ | Ministry of Education Ethiopia

አስተያየትዎትን ይስጡን!!

ትምህርት ሚኒስቴር የዋናውን ህንፃ ቀለም ቀድሞ ወደነበረበት ሞዛይክ ቀለም ለመቀየር በማሰብ፣ የስነ-ህንፃ ባለሙያዎችን በማሳተፍ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

የህንፃ ቀለሙን ወደ ቀድሞው ተፈጥሯዊው ሞዛይክ ለመቀየር ያስፈለገበት ምክንያት በዋናነት:-

የትምህርት ሚኒስቴርን የትምህርት ፍልስፍና፥ ራዕይና ተልዕኮ የሚወክል እንዲሆን ለማድረግ፣

ተቋማዊ ባህሪ እንዲኖረው ለማድረግ

ታሪካዊና ከህብረተሰቡ ስነልቦና ጋር የተዋሃደ እንዲሆንና የአካባቢውን ባህሪና የከተማን አውድ ታሳቢ እንዲያደርግ ለማድረግ ነው፣

የሚቀየረው ተፈጥሯዊው ሞዛይክ በዋናነት አብርሆትን ፣ አወንታዊ አስተሳሰብን፣ የላቀ አዕምሮ ባለቤትነትን፣ ምክንያታዊ መሆንን፣ ዕውቀት መጠማትን፣ አዲስ አስተሳሰብን፣ ተግባራዊ መሆንን፣ ፈጠራን፣ መፍትሔ አፍላቂነትን፣ ተስፋንና ደስታን የሚሉ ሐሳቦችን የሚወክሉ ሲሆን፤

የሞዛይኩ ቀለም ሐሳቦች ደግሞ:- ተቋሙ ከሚከተለው የትምህርት ፍልስፍና እና ራዕይና ተልዕኮ ጋር ስምምነት እንዳላቸው እንዲሁም ታሪካዊና ከህብረተሰቡ ስነልቦና ጋር የተዋሃደ ፤ የአካባቢውን ባህሪና የከተማን አውድንም ታሳቢ ያደረገ ውህደት እንዳለው የስነ ህንፃ ባለሞያዎች ይናገራሉ።

በተጨማሪም ተቋሙ የቀድሞውን ተፈጥሯዊ መልክ ይዞ ተጨማሪ አላባውያን እንዲኖሩት ተደርጎም በባለሞያዎቹ ዲዛይኑ ተሰርቶ ለአስተያየት ቀርቧል።

ስለዚህ አስተያየት ያላችሁ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል እና የስነ-ህንፃ ባለሙያዎች ማስታወቂያው ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ በተቋሙ የማህበራዊ ድህረገጽ አማራጮችና በኢሜይል አድራሻ info@moe.gov.et በመጠቀም ሀሳብ አስተያየታችሁን እንድታደርሱን በትህትና እንጠይቃለን፡፡