2022-09-30 14:47:24
ትምህርት ሚኒስቴር እና ሰላም ሚኒስቴር በጋራ
ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
------------------------------------------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሟል።
ስምምነቱንም የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ሰላምን ለማረጋገጥ የሞራል መሰረት ያለውና በምክንያታዊነት የሚያምን ዜጋ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡
በዚህ ዓመት ወደ ስራ በገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ግብረ ገብነት ትምህርት እንዲሰጥ መደረጉን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ተደረገው ስምምነትም ይህን በማጠናከር ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
ግብረገብነትና ምክንያታዊነት በጋራ አብሮ የመኖር ዋነኛ መሰረቶች በመሆናቸው ውጤታማና ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠይቅም ሚኒስትሩ ተናግረዋል ፡፡
የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው የዜጎችን አስተሳሰብና አመለካከት፡ ባህሪ ለመቀየር እና የሰላም ባለቤት እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ዛሬ የተፈረመው የጋራ መግባቢያ ሰነድ ዓላማም በሀገሪቱ ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች አጠቃላይ የሰላም ግንባታ ዙሪያ ተቀናጅቶ በጋራ አብሮ ለመስራት እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡
ሰላም በዘላቂነት የማስፈን ስራ ለአንድ ተቋም ወይም አካል ብቻ ሳይን በጋራና በመደጋገፍ የሚሰራ ስራ መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል::
7.2K views11:47