Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 82.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2022-08-28 10:16:02
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንድቀጥል ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
****************************
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሃገር አቀፍ ፈተናዎች አገልግሎት የሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልፀው፤ ውጤታማነቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና አሰጣጥ ዝግጅት፣ የዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አሰጣጥ፣ የትምህርት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተቋማዊ ሪፎርም፣ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ (autonomous) ለማድረግ ስለተያዘው ዕቅድ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዋናነት ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድን ከመገንባት አኳያ በትምህርት ሚኒስቴር የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራና ተስፋ ሰጪ ጅምሮች ስለመኖራቸውም ተብራርቷል።
ቋሚ ኮሚቴው የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን በሚመለከት ከወላጆች የሚነሱ ስጋቶችን እና ጥያቄዎችን እንዲሁም፤ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮዎች ያሰባሰባቸውን መረጃዎች መሰረት ላነሳቸው ጥያቄዎች ፤ በስራ ኃላፊዎቹ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡
ምንጭ :- (ኢ.አ.ድ

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02piiUrXkxeHBLsrzDRnsiaohtBPj4PQE3JfHscQ5VhyPgFFUiGXeYnFpdSCF6AWwul&id=100064682287722
5.6K views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 12:18:27
የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በቀጣይ አመት እንደሚጀምር ተገለፀ።
-------//----------
የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት የሙከራ ትግበራ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በ2015 ዓ.ም ይጀምራል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሙከራ ትግበራ ከሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራን ስርዓተ ትምህርቱን የማስተዋወቅ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት በርካታ ደረጃዎችን አልፎ ለሙከራ ትግበራ የደረሰ መሆኑን የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ገልፀዋል ።

በስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ የተመረጡ የመማር ማስተማር የልህቀት ማዕከላት ዩኒቨርሲቲዎች እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በአማካሪነት እንደተሳተፉበት ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ ዛፉ አብርሃ በበኩላቸው ይህ ሥርዓተ ትምህርት ሀገር በቀል እውቀትን፣ ግብረ ገብነትን ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተላበሰ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመሆኑም በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከባለድርሻ አካላት ብዙ ግብዓቶች እንደሚሰበሰቡ ጠቅሰው ወላጆችና ሌሎችም አስተያየት እዲሰጡበት በድረ ገፅ ይለቀቃል ብለዋል።

በሙከራ ትግበራው ወቅት የሚመጡ አስተያየቶች ተካተው በ2016 ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል ።

የሚሰጠው ስልጠናም መምህራን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መጽሐፉ እዲተዋወቁ ይረዳቸዋል ተብሏል ።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2014 የሙከራ ትግበራ ተካሂዶ በ2015 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይታወቃል።
8.3K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:57:42
የካናዳ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፍ ገለፀ
--------------------------------- ----------------------------------

የትምህርት ሚኒሰትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የካናዳ መንግስት አምባሳደር ከሆኑት ሚስተር ስቴፋኒ ጆቢን ጋር ነሐሴ 19/2014 ዓም ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ላይ የተነጋገሩ ሲሆን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሃ-ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ የካናዳ መንግስት ሊያደርግ ስለሚችለው ድጋፍ እና የበጎ ፈቃደኞች መምህራን ስምሪት ላይ ውይይት ተደርጓል።

የካናዳ አምባሳደር በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ አድንቀው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሃግብር ለማሳካትም በኤምባሲያቸው በኩል፣ በካናዳ ዓለምአቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስቴር እና የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎች አማካይነት እና በኦታዋ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ግብረሃይል ጋር በመነጋገር እና በማስተባበር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተለያዩ የለውጥ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
6.9K views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 16:14:38
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነትን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ ምሁራን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡
------------------------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስትር ኤታ ዶ/ር ሳሙኤል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነፃነት ተፈፃሚነት ላይ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነት ተግባራዊ መደረግ የተቋማትን የውስጥ አቅም ለማሳደግ ሚናው የጎላ መሆኑንም ገልፀዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነፃነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ ተቋማቱ የአመራር፣ አስተዳደር፣ አካዳሚያዊ፣ የሰው ኃይል እንዲሁም የገንዘብና ቁሳዊ ሃብት አስተዳደርን በነፃነት እና በተጠያቂነት ለመምራት እንደሚያስችል ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነፃነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚሰጥ እና የአስተዳደር ስርዓት በአግባቡ በመዘርጋት፤የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት አሳሪ አሰራር ደረጃ በደረጃ ተላቀው በነፃነት የሚሰሩበትን ሰርዓት ለመዘርጋት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡

ተቋማዊ ነጻነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮአቸውን በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ፣ የመምህራንንም ሙያዊ አስተዋጾ ለማሳደግ እና ኑሯቸውን ለማሻሻል ትልቅ ሚና ያለው በመሆኑ መንግስትም በትኩረት የሚሰራበት መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው አክለዋል።

ተቋማዊ ነጻነት ከመጪው 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መተግበር የሚጀምር ሲሆን በቀጣይ ሁለት ዓመታትም አስር ዩኒቨርስቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
7.7K views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 10:12:18 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከወጣቶች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አስመልክቶ የተናገሩት ቀጣይ ክፍል ;-


ሁለተኛው የዩኒቨርስቲ መምህራን እናንተም መገንዘብ ያለባችሁ ኢትዮጵያ ደሃ አገር ናት። አሜሪካ እንኳን ዩኒቨርስቲ ተማሪ አስገብታ አትቀልብም። ዩኒቨርስቲ ሰው ከደረሰ ራሱን ነው ማስተማር ያለበት እንጂ ለአስተማሪም ደመወዝ፣ ለተማሪም ቀለብ አይነት ጥያቄ እንደኢትዮጵያ ላሉ አገራት ኢኖቬተርስ አይፈጥርም። ዩኒቨርስቲዎች ኦቶነመስ ሆነው ራሳቸውን ማስተዳደር አለባቸው። ሃይስኩል ላይ ኢንቨስት ካደረግን እኛ እሱ እንደ በቂ መወሰድ አለበት። ዩኒቨርስቲ ሆኖ ገንዘብ አምጥቶ የራሱን ደመወዝ መክፈል የማይችል ከሆነ ኢትዮጵያን ማሳደግ አይችልም ማለት ነው።

ሃርቫርድ መንግሥትን አይጠይቅም በጀት፣ ኦክስፎርድ አይጠይቅም በጀት፣ ኬንያም ዩጋንዳንም ብትሄድ አይጠይቅም በጀት፣ እዚህ ግን ቀለቡም፣ ደመወዙም ሁሉም ነገር የሚጠየቅ ከሆነ ችግር አለ።
ሁለተኛ የዩኒቨርስቲ መምህር ስታንዳርድ አለው። በሴሚስተር አራት ክሬዲት አወር፣ አምስት ክሬዲት አወር አስተምረህ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ አይባልም። ተጋባዥ መምህር ነኝ ነው የሚባለው።

አሁን ችግር የሆነው በጅምላ መታየት የለበትም። የዩቨርስቲ መምህራን አርሶ አደር ጋር የሚውሉ፣ የሚመራመሩ፣ ግቢ የሚቀይሩ፣ ለመንግስት ሀሳብ የሚያቀርቡ ታምር የሚሰሩ ሰዎች አሉ። እነዚህን ማመስገን ያስፈልጋል። ሶስትም አራትም ክሬዲት አወር እያስተማሩ፣ በሳምንት አንድ ቀን ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ እየተቀመጡ፣ ሌላውን ቀን ደግሞ ሌላ ቦታ እየዋሉ፣ ፌስቡክ ላይ እየቆዩ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝና አድማ አደርጋለሁ የሚሉ ሰዎች ደግሞ አሉ። ይሄ ጥሩ አይደለም ለነሱም ጥሩ አይደለም። አድማ ቢደረግ ዩኒቨርስቲ ይዘጋል፣ አድማ ቢደረግ የበለጠ ገንዘብ ይከስራል። ከዚያ ምን እናገኛለን? ጥቅም አናገኝም! ደረጃ በደረጃ ጥያቄ እየመለስን ብንሄድ። ለሁላችን ጠቃሚ ይሆናል፣ የሁላችን ችግር ነው። ሁላችን በየደረጃው እየፈታን መሄድ አለብን። ከአገር አቅም ጋር መታየት አለበት።
ኢትዮጵያን በሚያሳድግ መልኩ መታየት አለበት። በዚህ አግባብ ከታየ ጥያቄው አግባብ አይደለም፣ በቂ ደመወዝ አላቸው፣ ለምን ጠየቁ የሚባል አይደለም። ችግር አለ እውነታቸውን ነው።

መታረም ያለበት ነገር አለ። ባለፈው ዓመት ተኩል ጂኤጂ ስንወስን ጂኤጂ በጣም ብዙ ዓመት ቆይቷል። ከ30 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ጠይቆናል። ቀላል ነገር አይምሰላችሁ። በአገር ደረጃ ስለሆነ አጠቃላይ በጀት ይወስድብናል። በጀቱን በሙሉ ደመወዝ ከፍለን ልማት የማንሰራ ደግሞ ከሆነ ትክክል አይመጣም። እና ጥያቄያቸው ፌር የሆነበት አለ። አቅም በፈቀደ መጠን እንመልሳለን። ከእነሱ ግን ብዙ እርዳታ፣ ብዙ ድጋፍ እንደምንፈልግ ከወዲሁ ግንዛቤ ቢወሰድ ጥሩ ነው። ከዚያ ውጪ ያለው የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን ብዙ ፋይዳ የለውም። ነገር እየተካረረ ስለሚሄድ ያለውንም እያሳጣ ነው የሚሄደውና ትክክል ስለማይመጣ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። የዩኒቨርስቲ አመራሮች፣ ፕሬዚዳንቶች፣ ቦርዶች መፈተሽ አለባቸው። ማነው መምህር፣ ማነው መምህር ያልሆነው፣ ማነው እያገዘ ያለው፣ ማነው እያገዘ ያልሆነው? መለየት ያስፈልጋል። ያንን ካደረግን መልካሞችን እየደግፍን የማይሰሩ ደግሞ እንዲሰሩ የምናደርግበት እድል ይፈጠራል።
9.2K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 10:04:02
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከወጣቶች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አስመልክቶ የተናገሩት;-

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ዩኒቨርስቲን በሚመለከት ሁለት ሶስት ነገር ማየት ጠቃሚ ነው። አንደኛ ዩኒቨርስቲዎች ምንም ብናማርራቸው በጣም ምርጥ ምርጥ ስራ እየሰሩ ያሉ አሉ። አሁን ለምሳሌ ዶክተር ፍሬው የባህርዳር ዩኒቨርስቲ በግቢው ውስጥ የጀመረው የልማት ስራ በጣም የሚደነቅ ነው። በጣም የሚደነቅ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲ ግቢውን ለማሳመር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። አርሶ አደር ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። በጣም ጥሩ ነው ይሄ። አሰላ ላይ የዛሬ ዓመት የነበረው ዩኒቨርስቲና ዛሬ ያለው በጣም ይለያያል። የዛሬ ዓመት አይመችም ነበር: አሁን በጣም ብዙ ስራ እየሰሩ ነው።

የቦንጋ ዩኒቨርስርቲ በጣም በጣም ጥሩ ስራ እየሰሩ ነው። ሌሎቹም እንደዚሁ የሚሞክሩ አሉ። ለማልማት፣ አርሶአደር ለማገዝ ፣ ሃይስኩል ለማገዝ ጥረት የሚያደርጉ ዩኒቨርስቲዎች አሉ። መምህራንም አሉ። ስለእነሱ እኔም ኢትዮጵያም ታመስግናቸዋለች።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0QcpopCDHueRK6MkwDJUfGPGpeXHu3UEkhvtWYTWnriSjRuGvn2dyhd64qQQEnybRl&id=100064682287722
7.1K viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:22:07
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
------------------------------------------------------------------------

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ስራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የፈተና ዝግጅቱም የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዋና ዳይሬክተሩ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆችም መረጃዎችን ከተቋሙ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉም ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ መስከረም 30,2015ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡
10.3K views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:24:53 የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ለምን አስፈለገ?

በ2015 የትምህርት ዘመን ለመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ብቻ መሠጠት ከሚጀምረው የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ከፈተናው በፊት ሊቀድሙ የሚባቸው ነገሮች አሉ በሚል የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ።

የግብዓት አቅርቦት ችግር ባለበት ሁኔታ ፣ የትምህርት ተቋማት አቅም በሚፈለገው ደረጃ ባልሆነበት ፣ የመምህራን ብቃት በራሱ ሳይመዘን / መምህራን ሳይመዘኑ ተማሪዎችን መመዘን እንዴት ይሆናል ፤ እንዴትስ ውጤት ያስገኛል በሚል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቆይታ ዝርዝር ጉዳዮችን ዳሰዋል።



8.3K viewsedited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 10:59:24
በጦርነቱ የወደሙ ት/ቤቶችን መልሶ የመገንባቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

----------------------------------------------- //
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰቆጣ ከተማ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት የአደጋ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትን መልሶ ለመገንባት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ደመቀ መኮንን፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የአ/ብ/ክ/መ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የመሰረት ድንጋይ ማሥቀመጥ ብቻ ሳይሆን በቶሎ በማጠናቀቅ ለስራ ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት ቤቱን በአንድ አመት ውስጥ ገንብቶ በማጠናቀቅ ለተማሪዎችና ለአካባቢው ማህበረሰብ ተደራሽ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ለዚህም የአካባቢው የመንግስት መዋቅርና የክልሉ መንግስት ክትትል እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል፡፡

ክቡር ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ በበኩላቸው በጦርነቱ የተጎዱ ት/ቤቶችን መልሶ በመገንባት ረገድ ትምህርት ሚኒስቴር እያደረገ ያለውን ተግባር አድንቀው የክልሉ መንግስትም የሚቻለውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

በጦርነቱ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በተሻለ ሁኔታ መገንባት የመንግስት ቀዳሚ ተግባር እንደሚሆንም አክለው ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በአዲሶቹ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ዲዛይን በተሻለ መልኩ የመገንባት ስራ ጀምሯል።
8.5K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 10:38:03
Internationalization for Quality Education” Workshop held
--------------------------------------------
Ministry of Education in collaboration with Hawassa University hosted a workshop with a theme “Internationalization for Quality Education”and focused on sharing experiences and training on internationalization for higher education institutions with its contribution to quality education.

Representatives from more than 40 Ethiopian public universities have attended the workshop.
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02LN1N2SZCxYYtFHS8BczLYDMBywPnrh98QnkDierEtTBuJv3evdZNmB2K8E21Q1dDl&id=100064682287722
11.6K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ