Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 82.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2022-09-08 09:44:26
7.0K views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 10:14:04
3.6K views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 17:40:02
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቀን ደም ለገሡ
..................................................

ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን አስመልክቶ የጤና ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ ባከናወኑት የሙሉ ቀን መርሃ ግብር የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ እና የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ መርሃ ግብር በየተቋሞቻቸው አከናውነዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር በተደረገው የደም ልገሳ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ደም መለገስ ህይወትን መቀጠል በመሆኑ ሰዎች ደም ሲሰጡ አንድ ሌላ ሰው በህይወት እንዲኖር እየረዱት ነው ብለዋል ።
3.2K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 16:17:12
በትምህርት ጤና እና ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጥምረት እየተከናወነ ባለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን ማዕከል ተጎበኘ!

የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች ህሙማኑን የጎበኙ ሲሆን እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተቋማቱ በድምሩ 450,000 በሚገመት ወጪ አዲስ አመት መዋያ የተያዩ ስጦታዎች አበርክተዋል።
3.4K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 14:07:44
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሁል ጊዜ ተግባር አድርጎ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
---------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋና የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ጳጉሜ አንድ “የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቀንን “ አስጀምረዋል።

በዳግማዊዊ ሚኒሊክ 2ኛደረጃ ትምህርት ቤት በተከናወነው የበጎ ፈቃድ አልግሎት መርሃ ግብር ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን ሁላችንም የሁል ጊዜ ተግባር በማድረግ ቀጣይነት ባለው መልኩ መፈፀም እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ከሌሎች ጋር አብሮ በመኖር የምናከናውናቸው ብቻ ሳይሆን ለራሳችንም የምንሠራቸው መልካም ተግባራት መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል ፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቀን መርሃ ግብር በት/ቤት ውስጥ መሆኑ ተማሪዎች ይህንን አገልግሎት እንደ ባህል ይዘው እንዲያድጉ ለማድረግ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር ) በበኩላቸው ትምህርት ቤቶችን ንጹህ፣ ማራኪና ምቹ ለማድረግ ባለፈው ዓመት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቀን የተጀመረው ስራ በዚህ ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

በዳግማዊ ምኒሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት የትምህርት፣ ጤና ሚንስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ሰራተኛች እንዲሁም የዳግማዊ ሚኒልክ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች እና የትምህርቱ ማህበረሰብ የአካባቢ ጽዳት እና የችግኞችን የመንከባከብ ስራ ሰርተዋል።

ለትምህርት ቤቱም የትምህርት ስራ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎች በትምህርት ሚኒስቴር ተበርክቷል፡፡ ፡
4.1K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 17:07:12
የመውጫ ፈተና ለግልና ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የጋራ መመዘኛ መሆኑ ተጠቆመ
.......................................
ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመውጫ ፈተና ዙሪያ ውይይት ተደርጓል ፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ  ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የመውጫ ፈተና የሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱና ዋነኛው የጋራ መወዳደሪያ መስፈርት ነው፡፡

የመውጫ ፈተናን ውጤት መሰረት በማድረግም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት  እርስ በርሳቸው እንደሚወዳደሩ ሚኒስትር ደኤታው አመልክተዋል፡፡

በመሆኑም ጥሩ ውጤት ሊገኝ የሚችለው ጥሩ ሂደት ሲኖር በመሆኑ ተቋማቱ ተማሪዎች ለውጤት እንዲበቁ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ዶ/ር ፋንታ አስገንዝበዋል፡፡
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በበኩላቸው በመውጫ ፈተና ዝግጅትና አስተዳደሩ ላይ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻዎች እንደሚሳተፉበትና በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በማእከል እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች ለምረቃ መብቃትና የትምህርት ማስረጃዎቻቸውንም መውሰድ የሚችሉት የመውጫ ፈተናውን ካለፉ በኋለ መሆኑን ጠቁመው በፈተናው ያላለፉ ተማሪዎችም ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ደግመው መፈተን  የሚችሉበት አሰራር እንደሚኖር  አስታውቀዋል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለሚያደርጉት ዝግጅትም የትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል፡፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02WfwaTYfGTHMAMtq2tpxWCJuyMiRaCD6XzGUtEM87AuE46BsbT19pGviSH34wWj9Nl&id=100064682287722
1.5K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 12:54:41
3.2K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 08:11:16 በዓለም ላይ እድሜያቸው 10 አመት ከሆናቸው ህፃናት ውስጥ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ቀላል ፅሁፍ እንኳ ማንበብና መረዳት አይችሉም:- ዩኒሴፍ

-------------------- --------------------

ከ10 አመት ህጻናት መካከል ወደ ሁለት ሶስተኛ የሚጠጉት ቀላል ጽሑፍ እንኳ ማንበብ እና መረዳት እንደማይችሉ ፣ አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ አለም አቀፋዊ የትምህርት ኪሳራና የትውልድ ጥፋት ሊከተል እንደሚችል ዩኒሴፍ አስታውቋል።

ቀድሞውንም የተዳከመውን የትምህርት ስርዓት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት ችግሩን በአለም አቀፍ ደረጃ አባብሶታል ብሏል።

ህፃናት መሰረታዊ የማንበብ እና የሂሳብ ክህሎቶች እንዲኖራቸውና አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ዓለም አቀፍ ጥረት እንዲደረግ ዩኒሴፍ በ "Let me learn "መማር እፈልጋለሁ" ቅስቀሳው ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ ማድረግ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ማድረግ፣ የመማር ማስተማር ስራዎችን በመደበኛነት መገምገም፣ ለትምህርት ቅድሚያ መስጠት፣ ህፃናት ለመማር ዝግጁ እንዲሆኑ የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ጤና ደህንነትን ማዳበር የሚሉ እርምጃዎችን መንግስታት እንዲወስዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ንቅናቄ እየተደረገ ይገኛል ።

በአለም አቀፍ ደረጃ ከአስር ስድስት የሚጠጉ ህጻናት በድህነት ምክንያት በትምህርት ተጎጂ እንደሆኑና በአስር አመት እድሜያቸው ቀላል ፅሁፍ ማንበብ እና መረዳት አይችሉም ብሏል።

በፈረንጆቹ መስከረም 19/2022 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት "የትምህርት ለውጥ ሰብሰባ" የጠራ ሲሆን ጉባኤው ትምህርት የሰላም፣ የመቻቻልና የዘላቂ ልማት መሰረት ነው በሚል ጉዳዩን በልዩ ትኩረት ይመለከተዋል ተብሏል።

https://www.unicef.org/learning-crisis
2.7K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 15:18:14
ጎንደር ፣ደብረብርሃን ፣ ደባርቅ እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛው እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብር ተማሪዎች አስመረቁ።
-------------------------------------------------
ጎንደር ዩኒቨርስቲ በዛሬው እለት በመደበኛ እና በተከታታይ ትምህርት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ድግሪ፣ በሁለተኛ ድግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ ድግሪ መርሃ ግብሮቾ 3,927 ወንድ 1,600 ሴት በድምሩ 5,527 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በአጠቃላይ በ2014ዓ.ም በሁለት ዘር 11 ሽህ 493 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ፒ.ኤች.ዲ) በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የዛሬ ተመራቂዎች ቀደም ካሉ አመታት ተመራቂዎች ልዩ የሚያደርጋቸው አካባቢ፣ ሃገራዊ እና አለም አቀፋዊ የሆኑ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮዊ ጫናዎችን ተቋቁመው ለዚህ በመቃታቸው ነው ብለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች ባገኛችሁት እውቀትና ክህሎት ተጠቅማችሁ ለዚህ ላበቃችሁ ህዝብ ትርጉም ያለው አስተዋፆ ለማበርከት የተግባር ሰው መሆን ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዶ/ር አስራት ዛሬ የገባችሁትን ቃል ኪዳን አክብራችሁ የሃገር እድገት፣ ሁለንተናዊ ስላም ፣ሉአላዊነት እና ህልውና እንዲረጋገጥ ከምንም በላይ ሃገራችን በእናንተ ዘመን አንድነቷ ተጠብቆ ወደ ከፍታ ማማ እንድትወጣ ታሪካዊ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ ሲሉ አደራ ብለዋል።
በተመሳሳይ ደብረብርሃን ፣ ደባርቅ እና ሠመራ ዩኒቨርስቲዎችም በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 928 ተማሪዎች አስመርቋል።

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 326 እንዲሁም ሰመራ ዩኒቨርስቲ ከ1000 በላይ ተማሪዎች አስመርቀዋል።
2.6K views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:37:15
የትምህርት ማስረጃዎችን በዲጅታል መያዝ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ።
----------------------------
የትምህርት ተቋማትን መረጀ ማስቀመጥና ማሥተዳደር የሚያስችል "ኢ-ስኩል" የተሰኘ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆኗል።

ቴክኖሎጂው ዋልያ ቴክኖሎጂ በተባለ የግል ድርጅት የበለፀገ ሲሆን የመምህራንና የተማሪዎችን መረጃዎች መያዝ ከማስቻልም ባለፈ የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያዘምን መሆኑ ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ(ዶ/ር) የትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዝ ሥርዓታቸውን በማዘመን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ማስቀመጥና ማስተደደር እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

ቴክኖሎጂው በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ምክኒያት በትምህርት ማስረጃዎች ላይ የሚደርሰውን ጥፉት ይቀርፋልም ብለዋል።

ዶ/ር ፋንታ በቅርቡ በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ከትምህርት ተቋማቱ ባሻገር የትምህርት ማስረጃዎች መውደማቸውን ገልፀው
ከዚህም ትምህርት በመውሰድ በቀጣይ ትምህርት ቤቶች የመረጃና ማስረጃ አያያዝ ሥርዓታቸውን በማዘመን የመረጃ ማዕከላቸውን በድጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ እንዲያስተዳድሩ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የዋልያ ቴክኖሎጂ መስራች የሆኑት አቶ አንተነህ አሥራት ዲጂታል ቴክኖሎጂው ትምህርት ቤቶች መረጃና ማስረጃዎችን ዲጂታላይዝ አድርገው እንዲያስቀምጡትና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

ቴክኖሎጂው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መጽሃፍትን የሚያገኙበትንም ቤተመጽሃፍትንም ማካተቱ ተገልጿል።

ቴክኖሎጂውን በመጠቀምም የትምህርት ቤት ክፍያዎችን በኦንላይን እንዲከፍሉ የሚያስችል እና ዘረፋ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑም ተጠቅሷል ፡፡
3.8K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ