Get Mystery Box with random crypto!

ጎንደር ፣ደብረብርሃን ፣ ደባርቅ እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛው እና በተከታታይ የትምህርት መ | Ministry of Education Ethiopia

ጎንደር ፣ደብረብርሃን ፣ ደባርቅ እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛው እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብር ተማሪዎች አስመረቁ።
-------------------------------------------------
ጎንደር ዩኒቨርስቲ በዛሬው እለት በመደበኛ እና በተከታታይ ትምህርት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ድግሪ፣ በሁለተኛ ድግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ ድግሪ መርሃ ግብሮቾ 3,927 ወንድ 1,600 ሴት በድምሩ 5,527 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በአጠቃላይ በ2014ዓ.ም በሁለት ዘር 11 ሽህ 493 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ፒ.ኤች.ዲ) በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የዛሬ ተመራቂዎች ቀደም ካሉ አመታት ተመራቂዎች ልዩ የሚያደርጋቸው አካባቢ፣ ሃገራዊ እና አለም አቀፋዊ የሆኑ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮዊ ጫናዎችን ተቋቁመው ለዚህ በመቃታቸው ነው ብለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች ባገኛችሁት እውቀትና ክህሎት ተጠቅማችሁ ለዚህ ላበቃችሁ ህዝብ ትርጉም ያለው አስተዋፆ ለማበርከት የተግባር ሰው መሆን ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዶ/ር አስራት ዛሬ የገባችሁትን ቃል ኪዳን አክብራችሁ የሃገር እድገት፣ ሁለንተናዊ ስላም ፣ሉአላዊነት እና ህልውና እንዲረጋገጥ ከምንም በላይ ሃገራችን በእናንተ ዘመን አንድነቷ ተጠብቆ ወደ ከፍታ ማማ እንድትወጣ ታሪካዊ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ ሲሉ አደራ ብለዋል።
በተመሳሳይ ደብረብርሃን ፣ ደባርቅ እና ሠመራ ዩኒቨርስቲዎችም በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 928 ተማሪዎች አስመርቋል።

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 326 እንዲሁም ሰመራ ዩኒቨርስቲ ከ1000 በላይ ተማሪዎች አስመርቀዋል።