Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 82.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 27

2022-11-05 16:13:27
በሁሉም አማራጭ የዜጎችን የትምህርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ።
....................................................

የትምህርት ሚኒስቴር" ሀገር አቀፍ የመሠረተ ትምህርት ቀን " የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ለማህበረሰብ የተፋጠነ እድገት በሚል መሪ ቃል እያከበረ ይገኛል።

ትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) በስነስርዓቱ መክፈቻ ላይ እንዳሉት ሀገርን መለወጥ የሚቻለው በትምህርት ላይ ለውጥ ማምጣት ሲሰጡ ብቻ ነው።

በመሆኑም በጎልማሶች ትምህርት ማንበብ መጻፍ እና ማስላት የማስቻል ግብ እንዲሳካ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ለዘርፉ ትኩረተ እንዲሰጡና እንዲደግፉ ዶ/ር ፋንታ ጥሪ አቅርበዋል።

በጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም በእድሜያቸው ትምህርት ቤት ያልገቡትን ወጣቶችና ህጻናት በማቀፍና በማበረታታት የመደበኛ ትምህርትን መደገፍ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ፕሮግራሞ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮሴፍ አበራ በበኩላቸው የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥተውት ይሰጥ እንደነበረ ተናግረዋል።

የተለያዩ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ከገበያ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

''የጎልማሶችና' መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ለማህበረሰብ የተፋጠነ እድገት'' በሚል ርዕስ እየተከበረ ባለው በዚሁ በዓል ላይ ልዩ ልዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
3.3K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 11:59:36
ዓለም አቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ሊያደርግ ነው::
……………………………………………………………………………………………..
ጥቅምት 25/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) ዓለም አቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ሊያደርግ ነው::

በኢትዮጵያ መንግስት እና በዓለምአቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት መካከል ስምምነት የተፈረመ ሲሆን ስምምነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የትምህርት ምጥጥን እና የአካቶ ትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ለማጠናከር እንደሚያስችል ተገልጿል::

በስምምነት ፊርማ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መሰል ተቋማት ወደ ሀገራችን መምጣታቸው የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንጻር ሚናቸው ጎላ መሆኑን ገልጸዋል::

ሚንስትር ዴኤታዉ አክለውም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለተቋሙ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል::

በትምህርቱ ዘርፍ አለም አቀፍ አጋርነትና ትብብርን በማጠናከር አካዳሚያዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲዊ አቅምን ማጠናከር እና መገንባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል::

የዓለምአቀፉ ትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና ፀሐፊ መንሱር ቢን ሙሳላም በበኩላቸው ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረሙት ሥምምነት በትምህርቱ ዘርፍ አለም አቀፍ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም እና ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ የአሁኑን እና የመጪውን ትውልድ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል::
2.7K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 16:34:00
ዝክረ ጥቅምት 24ን ስናስብ ጠንካራ የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ስርዓት ያላት ሃገር ለመገንባት ሁላችንም አስተዋፆ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
---------------------------------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች ህወሀት በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት የፈፀመበትን ዕለት አስበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በስነ- ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዕለቱን ስናከብር ሃገራችንን በጠንካራ ኢኮኖሚና የፖለቲካዊ ስርዓት ባለቤት ለማድረግ የድርሻችንን የምናበረክትበት ቀን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ዕለቱ የሃገር ዳር ድንበርንና አንድነትን ለማስጠበቅ በተሰማሩ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት ተግባር መቸም በምንም ሁኔታ መደገም እንደሌለበት ለማስታወስ ሁሌም ሲዘከር የሚኖር ነው ብለዋል፡፡

ሁለተኛውን ዝክረ ጥቅምት 24 ስናከብር የሰላም ድርድሩ ውጤታማ በሆነ መልኩ በተጠናቀቀበት ማግስት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ፤ሆኖም የተደረሰው የሰላም ስምምነት የህይወት መስዋዕትነት የተከፈለበት መሆኑን የሚዘነጋ አይደለም ብለዋል፡፡

በዚህች ሃገር ዳግም ጦርነት ተመልሶ እንዳይመጣ የፖለቲካ ልዩነቶች በጉልበት ሳይሆን በውይይትና በምክንያታዊነት ችግራችንን መፍታት እንደሚገባም ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል፡፡

ዕለቱ ሰንደቅዓላማ በመስቀል፣ ለሰማዕታቱ መታሰቢያ ጧፍ በማብራት ፣ በ6800 አጭር መልዕክት ድጋፍ በመላክ እንዲሁም ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ ታስቦ ውሏል፡፡
3.4K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 19:28:19
ለቀጣይ ሁለንተናዊ የሀገር እድገት እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለው ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ
------------------------------------

ትምህርት ሚኒስቴር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ ለመሥራት በሚያስቻለቸው ጉዳይ ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለው ትውልድን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ በአዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርትም ሆነ በአዲሱ የትምህርት ቤቶች ግንባታ ዲዛይን ላይ የሙያና የተግባር ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብረሃኑ ባለፉት ጊዜያት ሙያዊ ክህሎትና ተግባር በሚጠይቁ ሥራዎች ላይ በሀገር ደረጃ በጥራትም ሆነ በመጠን ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት እንደነበር ገልፀው ይህንን ችግር በመቅረፍ ለቀጣይ ሁለንተናዊ የሀገር እድገት የሚበጅ እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለቸውን ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው እንደ ሀገር ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ተመራቂዎች የሚፈለገውን ብቃትና ችሎታ ይዘው እንዲወጡ ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02DtutAtE6KzHNr2XxXqMwj1GDrdowC4eWFdeQVFyZWwVEkTwqkESUatJJE7fGAPVLl&id=100064682287722
2.8K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 16:34:34
ኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሄለን ወልደሚካኤል የእንሰት ምርትን በሚያሻሽል የፈጠራ ሃሳብ አሸናፊ ሆኑ
…………………………………………………………………………………………………………………………………….

ጥቅምት 18/2015ዓም.(ትምህርት ሚኒስቴር) በምግብ ደህንነት ላይ ትኩረቱን ባደረገው ውድድር ኢትዮጵያዊቷ የእንሰትን ምርት በሚያሻሻል የፈጠራ ሃሳብ የ10ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆኑ፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ውድድሩን በገንዘብ መደገፉንም ሌክስ ብሎግ የተሰኘው ድረገፀ አስነብቧል፡፡
ውድድሩ የምግብ ደህንነትን የሚመለከት ሆኖ ከናይጄሪያና ከኢትዮጵያ ከ750 በላይ አመልካቾች ተሳትፈውበታል፡፡

አስር ሃሳቦች ለኢትሴፍ ብሄራዊ የምግብ ውድድሩ ቀርበው የመጨረሻዎቹ ሶስቱ በዴንማርክ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ላብራቶሪ የመጨረሻው ፍተሻ ተደርጓል፡፡

ቀዳሚ አሸናፊ ሃሳብ ሆኖ የተገኘው ከወልቂጤ የኒቨርሲቲ በረዳት ፕሮፌሰር ሄለን ወልደሚካኤል የቀረበው የፈጠራ ሃሳብ ሲሆን 20 ሚሊዮን ሰዎች የሚጠቀሙትን እንሰት አዘገጃጀትና አጠቃቀም ውጤታማነት የሚጨምር ነው ተብሏል፡፡

የፈጠራ ሃሳቡ እንሰትን ወደ ቆጮ በመቀየር ሂደት በተለይ የሴቶችን ጫና የሚቀንስ ፣የእንሰቱን ንፅህና የሚጠብቅና ለማዘጋጀት የሚፈጀውን ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ወደ ገበያ በብዛት ለማውጣት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ሁለተኛና ሶስተኛ የወጡት የናየጄሪያ ተወዳዳሪዎች ምግብን በፀሃይ ሃይል ሳይበላሽ ማቆየት በሚያስችልና ከብስባሽ ጥራት ያለውን ማዳበሪያ በማምረት አሸናፊዎች መሆናቸዉን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
6.3K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 20:10:21

6.8K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 15:06:45
8.5K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 11:50:05
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በርካታ ትምህርቶች የተገኙበት እንደሆነ ተገለፀ፡፡
-----------//---------------------------------------------------------------
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ትምህርቶች የተገኙበት እንደነበር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአግባቡ ከተመሩ፣ ከቆረጡና ጥረት ካደረጉ የትኛውንም ተልዕኮ መወጣት እንደሚችሉ ያየንበት ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም መላው ህዝባችንም ሲያማርርባቸው የነበሩ ጉዳዮችን መንግስት ለማረም ሲነሳና ጥረት ሲያደርግ ድጋፍ እንደሚሰጡ በተጨባጭ የተረጋገጠበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

አክለውም በቀጣይ እንደ ሀገር ህዝቡ በሚያማርርባቸው የተደራጀ ሌብነት፣መልካም አስተዳደር እጦት፣ለመንግስት አገልግሎት እጅ መንሻ መጠየቅ ላይ እንዲሁም በትምህርት ሴክተሩ ሃሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለማስተካከል ህዝቡን ከጎናችን ካሰለፍን ትርጉም ባለው መልኩ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ትምህርት ተወስዶበታል ብለዋል፡፡

የፈተና አስፈፃሚዎች ከተወለዱበትና ከሚያስተምሩበት ውጪ መመደባቸው ኢትዮጵያውያን አሁንም የተሳሰርንበትና የተጋመድንበት ጠንካራ ማህበራዊ ትስርስር ያለን መሆኑን የተረዳንበት ነበርም ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ፡፡

አጠቃላይ ሂደቱ የሚኒስቴር መስሪያቤቱን ቅቡልነት መልሶ ለመገንባት እድል የተፈጠረበት መሆኑን ጠቅሰው በትምህርት ሴክተሩ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ መተግባርና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አፈፃፀም ዙሪያ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
8.9K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 19:57:24
ከጥረት ውጭ የሚገኝ ውጤትን የሚጠየፍ ህዝብ እንዳለን ከፈተናው ሂደት ተገንዝበናል - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
************************

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል መጠናቀቁን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ፥ በፈተናው አሰጣጥ ሂደት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮን ማሳካት እንደሚችሉ አይተናል ብለዋል።

ከጥረት ውጭ የሚገኝ ውጤትን የሚጠየፍ ህዝብ እንዳለን ከፈተናው ሂደት ተገንዝበናል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሂደቱ በህብረተሰቡ እገዛና ትብብር በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻልም ያመላከተ እንደነበር ተናግረዋል።
8.2K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 17:08:16
የ2014 ዓ.ም  የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ የተሳካ እንደነበር  ተገለፀ

---------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ የተሳካ እንደነበረ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ሂደት ዝርዝር መረጃዎች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በታቀደው መሰረት መሰጠቱን እና የነበረው ሂደትም ውጤታማ እንደነበር ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም የፈተና አስተዳደር ስርዓቱ አደጋ ውስጥ ወድቆ መቆየቱን እና የፈተና ስርዓቱም የፓለቲካ ጥቅም ላይ ሲውል መቆየቱንም ገልፀዋል።

በ2014ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና በአጠቃላይ ከ 900ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው የተፈታኝ ቁጥር በእጅጉን እንደሚልቅ ተገልጿል።

በአጠቃላይም ከተመዘገቡት ተማሪዎች ውስጥ 98.8 በመቶ ተማሪዎች ተፈትነዋል፡፡ ፈተናውን ለማስፈፀምም ከ25ሺህ በላይ ፈተና አስፈፃሚዎች እና ከ 6ሺህ በላይ የፀጥታ ሀይሎች ለፈተናው  መሰማራታቸው ተሰማርተዋል።

ሙሉ ዜናው
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid037e7PEp4WcsfucS2nnH7DDQwa4u3rdcjj7RPJ8RRZ42ZWfVhbhcafgeSm9itVJrNBl&id=100064682287722
9.4K views14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ