Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_moe — Ministry of Education Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81.50K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-10-31 16:23:39
ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አመራር ምደባ ተካሄደ
................................................
ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አመራር ምደባ ተካሂዷል።

ዶክተር ጉቼ ጉሌ ሱላ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ ከጥቅምት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል።

የዩኒቨርስቲው ቦርድ በበኩሉ ዶክተር አክበር ጩፋን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ዶክተር ዘውድነህ ቶማስን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ መድቧል።

አዲስ የተመደቡት አመራሮች ከቀድሞው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር የስራ ርክክብ አካሂደዋል።
24.0K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-30 21:18:17
የትምህርት  ሚኒስተሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ።
....................................................ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር)  የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር  36ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን በጅግጅጋ ከተማ አካሂዷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ በስብሰባው ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ከሁሉም ክልሎች ከመጡ የመምህራን ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የመምህራን ማህበር የመምህራንን  ክብር ወደ ነበረበት ለመመለስ ጠንክሮ መሥራት ይኖርበታል ብለዋል።

የመምህራንን ክብር ለመመለስ የማስተማር ፍቅርና ችሎታው ያላቸውን መምህራንን ወደ ሙያው ላይ እንዲመጡ ማድረግና ያለ ችግር መኖር የሚያስችላቸው ደመወዝ መክፈል ይገባል ብለዋል።

የሙያ ማህበሩም በበኩሉ የመምህሩን  የትብብር    ጉልበት ተጠቅሞ እንደ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ  የመሣሠሉትን በራሱ አባላት በማቋቋም የመምህራን ኑሮ ለማሻሻል መስራት ይኖርበታል ያሉ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴርም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

አሁን ባለንበት ሁኔታ ሀገራዊ ችግር ውስጥ የገባነው የትምህርት ስርዓታችን በመውደቁ ነው ያሉት ሚኒስትሩ እንደ መምህራን ማህበር ችግሩን በግልፅ ተነጋግሮ ለመፍትሄው በጋራ መስራት ይጠበቃልም ብለዋል።

የሙያ ማህበሩም የሙያውን ክብር ለመመለስ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ማድረግና ተጠያቂነት እንዲሰፍን መሥራት እንደሚኖርበት ጠቁመዋል።

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0D3kfj6BaB8Sqzh2NFyReJfPtERzutYb7mVpgJNhkzSrVPF8CNwXCJTzGUAAFwfURl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO።
24.5K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 08:43:47
#ማስታወቂያ

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ)  ለመማር ያለፋችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እስከ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም እንድታመለክቱ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

የትምህርት ሚኒስቴር
18.5K viewsedited  05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-19 17:26:26
#ማስታወቂያ

በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ)  ለመማር ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርትቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡

 በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ምርጫችሁ ውስጥ በማካተት መመደብ የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን።

የትምህርት ሚኒስቴር
36.7K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-18 17:46:38 የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስቴር 2016 የበጀት ዓመት የትምህርት ዘርፍ ዕቅድ እና የአንደኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ለፓርላማ ሲያቀርቡ በቀጥታ ስርጭት የተላለፈ
https://fb.watch/nLvPIrm2Og/?mibextid=Nif5o
23.7K views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 16:22:02
"የትምህርት ስብራቱን ለማከም ከታች ጀምሮ በየደረጃው መሠራት ያለባቸው ብዙ የቤት ስራዎች አሉብን " ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ
.............................
መስከረም 28/2016ዐ ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር)የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ውጤት አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ተሰጥቷል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጠዋት መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በድረ-ገጽ እና በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ማወቅ እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ሮ ብርሀኑ ነጋ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ እንደተናገሩት በ2015 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከወሰዱ 845 ሺህ 188 ተማሪዎች ውስጥ 27 ሺህ ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት የማለፍያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልፀዋል።

ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 3.2% ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸውን የገለፁት ሚኒሰትሩ ውጤቱ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ0.01 መቀነሱንም አብራርተዋል።

ዘንድሮ 3 ሺህ 106 ትምህርት ቤቶች ፈተና ያስፈተኑ ሲሆን፣ ከነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻለቸውን መታየት ያለበት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም 42.8 ከመቶ ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸው ነው የተገለፀው።

የዘንድሮው ትልቁ የፈተና ውጤት 649 ሲሆን ይኸውም በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስክ በሴት ተማሪ የተመዘገበ ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 ከ600 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ በወንድ ተማሪ የተመዘገበ መሆኑ ተገልጿል።

ሙሉ መግለጫውን ለማግኘት

https://rb.gy/244bs
49.3K views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 16:19:52
በትምህርት ዘርፉ ባለፉት ሦስት አመታት የተጀመሩ አበረታች ለውጦች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ።
---------/-----------
የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ6ኛው የሁለቱ ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የትምህርቱን ዘርፍ በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ ባለፈው አመት በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ከ6.9 ሚሊዬን በላይ ተማሪዎች ቁርስና ምሳ እንዲመገቡ በማድረግ ድህነትን ከመቀነሰ ባሻገር አምራች ዜጋ ለመፍጠር የሚያስችል የሰብዓዊ ልማት ለውጥ ማምጣት መቻሉን አንስተዋል።

በዚህም ዓመት በትምህርት ዘርፉ ባለፉት ሦስት አመታት የተመዘገቡ አበረታች ለውጦች መሠረት እንዲይዙ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ክብርት ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል።
36.0K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-08 11:37:22
የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል።
..............................................................................

መስከረም 27/2016 ዓ/ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል። በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።

ተማሪዎችም ትክክለኛውን መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ገፆች ላይ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።

ፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
ቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
ትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
32.7K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-07 11:50:01
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ዘርፉ አካታችነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ተወያዩ
…………………………..//………………………

መስከረም 26/2016ዓ/ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አመራሮች ከትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጋር ተወያይተዋል።

የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት አካል ጉዳተኞችን ተደራሽ እና አካታች ከማድረግ አንፃር ያለበትን ችግር ተወካዮቹ ለፕሮፌሰር ብርሃኑ አብራርተዋል ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በትምህርት ፖሊሲው አካል ጉዳተኞችን በሚመለከት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት እንደተደረገ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በመርህ ደረጃ የትምህርት ስርዓቱን አካታች ለማድረግ ስምምነትና ፍላጎት ቢኖርም በትግበራ ወቅት እንደ ሃገር ያለውን የመንግስት የአቅም ውስንነት ከግንዛቤ በማስገባት አቅም በፈቀደ መጠን ደረጃ በደረጃ የሚተገበር መሆኑን አስረድተዋል።
20.3K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 13:33:46
ለመላው መምህራን እንኳን ለዓለምዓቀፋ የመምህራን ቀን አደረሳችሁ፡፡

በዓለምዓቀፍ ደረጃ የዛሬዋ ቀን የመምህራን መታሰቢያ በመሆን እንድትከበር ከተወሰነ ዛሬ 29 ዓመት ሆኗል፡፡

በዓለማቀፍ ደረጃ ዩኔስኮ እያከበረዉ የሚገኘው “The teachers we need for the education we want: The global imperative to reverse the teacher shortage” በሚል መሪ መልእክት ነው ፡፡

ክብር ለመምህራን ይሁን!
24.1K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ