Get Mystery Box with random crypto!

ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አመራር ምደባ ተካሄደ ........................... | Ministry of Education Ethiopia

ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አመራር ምደባ ተካሄደ
................................................
ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አመራር ምደባ ተካሂዷል።

ዶክተር ጉቼ ጉሌ ሱላ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ ከጥቅምት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል።

የዩኒቨርስቲው ቦርድ በበኩሉ ዶክተር አክበር ጩፋን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ዶክተር ዘውድነህ ቶማስን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ መድቧል።

አዲስ የተመደቡት አመራሮች ከቀድሞው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር የስራ ርክክብ አካሂደዋል።