Get Mystery Box with random crypto!

በትምህርት ዘርፉ ባለፉት ሦስት አመታት የተጀመሩ አበረታች ለውጦች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። ፕሬዚዳንት | Ministry of Education Ethiopia

በትምህርት ዘርፉ ባለፉት ሦስት አመታት የተጀመሩ አበረታች ለውጦች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ።
---------/-----------
የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ6ኛው የሁለቱ ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የትምህርቱን ዘርፍ በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ ባለፈው አመት በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ከ6.9 ሚሊዬን በላይ ተማሪዎች ቁርስና ምሳ እንዲመገቡ በማድረግ ድህነትን ከመቀነሰ ባሻገር አምራች ዜጋ ለመፍጠር የሚያስችል የሰብዓዊ ልማት ለውጥ ማምጣት መቻሉን አንስተዋል።

በዚህም ዓመት በትምህርት ዘርፉ ባለፉት ሦስት አመታት የተመዘገቡ አበረታች ለውጦች መሠረት እንዲይዙ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ክብርት ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል።