Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ዘርፉ አካታችነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞ | Ministry of Education Ethiopia

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ዘርፉ አካታችነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ተወያዩ
…………………………..//………………………

መስከረም 26/2016ዓ/ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አመራሮች ከትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጋር ተወያይተዋል።

የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት አካል ጉዳተኞችን ተደራሽ እና አካታች ከማድረግ አንፃር ያለበትን ችግር ተወካዮቹ ለፕሮፌሰር ብርሃኑ አብራርተዋል ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በትምህርት ፖሊሲው አካል ጉዳተኞችን በሚመለከት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት እንደተደረገ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በመርህ ደረጃ የትምህርት ስርዓቱን አካታች ለማድረግ ስምምነትና ፍላጎት ቢኖርም በትግበራ ወቅት እንደ ሃገር ያለውን የመንግስት የአቅም ውስንነት ከግንዛቤ በማስገባት አቅም በፈቀደ መጠን ደረጃ በደረጃ የሚተገበር መሆኑን አስረድተዋል።