Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_moe — Ministry of Education Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81.50K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-11-25 11:59:49
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአለም አቀፍ ትብብርና አጋርነት ስራዎች ላይ በስፋት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::

ህዳር 15/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ከአውሮፓ ህብረት ኤራስመስ+ (Erasmus+) የትምህርት፣የስልጠና፣የወጣቶችና ስፖርት ትብብር ፕሮግራሞች እንደ ሀገር ያለውን ጠቀሜታ ማሣደግ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

በምክክር መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ቁልፍ መልእክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ብቃት ያለው የሠው ሀይል ለማፍራት እና በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትብብርና አጋርነት ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ሚኒስቴር ዴኤታው አያይዘው እንደገለጹት በአውሮፓ ህብረት ኤራስመስ+ (Erasmus+) የትምህርት፣የስልጠና፣የወጣቶችና ስፖርት ትብብር ፕሮግራሞች ላይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለሚያደርገው ጥረት ምስጋናቸውን አቀርበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሜጀና በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ኤራስመስ+ (Erasmus+) የትምህርት፣የስልጠና፣የወጣቶችና ስፖርት ትብብር ፕሮግራሞች አስፈላጊነትና ቁልፍ የአተገባበር ስልቶችን ያጋሩ ሲሆን በዚህም የሚገኘውን ድጋፍ አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ዝርዝር ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0Z5Dc5hBFmeoz2n5eyctairRCE7Y8p4DCjkzG6aiDZQjEsWGq7AgsPcsxDccRLvF3l&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
19.7K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-23 21:37:33
ከ10 ነጥብ 6ሚሊዮን በላይ መጻህፍት ለክልሎች ተከፋፈሉ
...................................................

ህዳር 13/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጁ ከ10 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ መጻህፍት ለክልሎች ተከፋፍለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ወደ አገር ውስጥ የገባ 10 ሚሊዮን 649 ሺ የ2ኛ ደረጃ መጽሀፍት ለክልሎች ተከፋፍለዋል።

በጅቡቲና በደረቅ ወደብ የሚገኝ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን መጻሕፍትም እስከ መጪው ታህሳስ ወር አጋማሽ ድረስ ተጓጉዞ ለክልሎችእንደሚሰራጭ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።

40 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ወጥቶባቸው ህትመታቸው የተጠናቀቁት መጻህፍት ከ9ኛእስከ 12ኛ ክፍል ለማስተማሪያነትና ለመምህሩ መምሪያነት የሚያገለግሉ ናቸው።

የመጽሀፍት ስርጭቱ በአገሪቱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያለውን የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የመማሪያ መጻሕፍት እጥረት እንደሚያቃልለው ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

የመጻሕፍት እጥረትን ለመፍታትም አሁን ከታተሙት የ20 ነጥብ 7 ሚሊየን መጽሐፍት በተጨማሪ በቀጣይ ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማሳተም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሃኑ አብራርተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
ይከታተሉ
18.2K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-23 16:25:47
የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
ይከታተሉ
20.4K viewsedited  13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-18 14:44:05
በኢትዮጽያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት ምን እየተስራ ነው?
......................................................................................................

ህዳር 9/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን/Mastercard Foundation፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ ከሻያሾኔ እና ከ50ዎቹ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት) ጋር በመሆን እየተገበረ ያለው ኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት (e-Learning for Strengthening Higher Education / e-SHE) የተሰኘው የአምስት ዓመት ፕሮጀክት በኢትዮጽያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ ውጥኖችም
1. ሀገር አቀፍ የኢ-ለርኒግ ፖሊሲ ማዘጋጀት፣

2. በ5 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርት የሚዘጋጅባቸው ደረጃቸውን የጠበቁ መልቲ ሚድያ ስቱዲዮችን መገንባት፣

ሙሉ መረጃውን ያግኙ

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid023vCkv1Zm4v3z7c4abWMPXs1Ys1scLYqzLWepRyB8Mc1cY4Q8kbUA1N3w3FhPgHNml&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
14.1K views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-15 21:28:11
#ማስታወቂያ፡- በረመዲያል ምደባ አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ
.............................................
በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም እንድታመክቱ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ይፈልጋሉ ብሎ የለያቸው ጉዳዮች፦

  የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች:- የምደባ ሲስተሙ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች እኩል እድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል። 

አስፈላጊ ማስረጃዎች፦ ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና የአካል ጉዳት ያለበትን የሰውነት ክፍል የሚያሳይ ፎቶግራፍና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

  ትክክለኛ የሕክምና ቦርድ ማስረጃዎች፡- በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡ 


ሙሉ መረጃው https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0JGvtXdm3xabN87MU9cTUn5jkfCn2cCQ3Rhxxo1fbDPFrRFh5KDDpagYNZdzWR5TFl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
19.5K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-15 12:05:19
#ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ

በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡ -

ከታች የተዘረዘሩ ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም የማያስተናግዱ መሆኑን እንገልጻለን።

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ

6. ኮተቤ የትምህርት ዪኒቨርሲቲ
34.6K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-14 19:15:07
የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ  ህዳር 05-6 /2016 ይሰጣል

...................................................

ህዳር 04/2016 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test) በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ  ህዳር 05-6 /2016 ይሰጣል።

ፈተናው በ46 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን ዘጠኝ ሺ ሰባ ተማሪዎች ለመፈተን ተመዝግበዋል።

ፈተናው ከህዳር 5-6 ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።
18.6K viewsedited  16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-14 15:01:24
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በዛሬው የምክር ቤት ምላሻቸው በትምህርት ዘርፍ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከተተገበሩ የለውጥ እርምጃዎች አንዱ የስርዓተ ትምህርት ለውጥ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከስርዓተ ትምህርት ትግበራው አንጻር በምክር ቤቱ ከተጠየቁ ጥያቄዎች አንዱ የሆነው የመጻህፍት ዝግጅትና ህትመት ስራ ነው። በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ከስርዓተ ትምህርት ትግበራው፣ መጻህፍት ዝግጅትና ህትመት ስራ ምን ይመስላል?
.............................................
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃዎች በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ ገብቷል።
በዚህም መሰረት የሥርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍና መርሀ ትምህርት በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 8ኛ ክፍል ያለው የመማሪያና ማስተማሪያ መጻሕፍት በክልሎች በመርሃ ትምህርቱ መሠረት ተዘጋጅቷል፡፡ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ወደ ሙሉ ትግበራ ተገብቷል። የሁለተኛ ደረጃ (ከ9ኛ-12ኛ ክፍሎች) የመማሪያና ማስተማሪያ መጻሕፍት እና የ11ኛና በ12ኛ ክፍሎች የሥራና ተግባር ትምህርት 20 የሙያ ዘርፎች መርሃ ትምህርት በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0aw15PCWJUhCxQuMhcfGubtg5QVh4Fz34sCJAoiN19vyjxPXiuZSknjVGziKbMot6l&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO
19.3K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-14 13:15:04
21.2K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-14 12:13:46
የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ፒኤችዲ) ትምህርት ዘርፉን በተመለከተ ለተጠየቁ ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ
............................................................................

የትምህርት ስብራቱ ዘመናትን የተሻገረ ነው፡፡ ይህንን ለማስተካከል በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን የፈተና ምዘና ስርዓቱም ከዚሁ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡

ከ50 በላይ ያመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይግቡ ብንልም፤ ከተቀመጠው ነጥብ ወረድ ብለን ድጋሚ የማካካሻ ፈተና ወስደው የሚያልፉት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚቀላቀሉበትን አሰራር እየተከተልን ነው፡፡ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያለውን ስብራት ማስተካከል ካልቻልን ልጆቻችን በህይወት ፈተና እንዲወድቁ እናደርጋቸዋለን፡፡ በመሆኑም በትብብር የተሻለ የትምህርት ስርዓት እንዲኖር መስራት አለብን።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et

ይከታተሉ
21.7K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ