Get Mystery Box with random crypto!

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በዛሬው የምክር ቤት ምላሻቸው በትምህርት ዘርፍ የትምህርት ጥ | Ministry of Education Ethiopia

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በዛሬው የምክር ቤት ምላሻቸው በትምህርት ዘርፍ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከተተገበሩ የለውጥ እርምጃዎች አንዱ የስርዓተ ትምህርት ለውጥ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከስርዓተ ትምህርት ትግበራው አንጻር በምክር ቤቱ ከተጠየቁ ጥያቄዎች አንዱ የሆነው የመጻህፍት ዝግጅትና ህትመት ስራ ነው። በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ከስርዓተ ትምህርት ትግበራው፣ መጻህፍት ዝግጅትና ህትመት ስራ ምን ይመስላል?
.............................................
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃዎች በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ ገብቷል።
በዚህም መሰረት የሥርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍና መርሀ ትምህርት በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 8ኛ ክፍል ያለው የመማሪያና ማስተማሪያ መጻሕፍት በክልሎች በመርሃ ትምህርቱ መሠረት ተዘጋጅቷል፡፡ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ወደ ሙሉ ትግበራ ተገብቷል። የሁለተኛ ደረጃ (ከ9ኛ-12ኛ ክፍሎች) የመማሪያና ማስተማሪያ መጻሕፍት እና የ11ኛና በ12ኛ ክፍሎች የሥራና ተግባር ትምህርት 20 የሙያ ዘርፎች መርሃ ትምህርት በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0aw15PCWJUhCxQuMhcfGubtg5QVh4Fz34sCJAoiN19vyjxPXiuZSknjVGziKbMot6l&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO