Get Mystery Box with random crypto!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአለም አቀፍ ትብብርና አጋርነት ስራዎች ላይ በስፋት መንቀሳቀስ እንደሚ | Ministry of Education Ethiopia

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአለም አቀፍ ትብብርና አጋርነት ስራዎች ላይ በስፋት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::

ህዳር 15/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ከአውሮፓ ህብረት ኤራስመስ+ (Erasmus+) የትምህርት፣የስልጠና፣የወጣቶችና ስፖርት ትብብር ፕሮግራሞች እንደ ሀገር ያለውን ጠቀሜታ ማሣደግ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

በምክክር መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ቁልፍ መልእክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ብቃት ያለው የሠው ሀይል ለማፍራት እና በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትብብርና አጋርነት ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ሚኒስቴር ዴኤታው አያይዘው እንደገለጹት በአውሮፓ ህብረት ኤራስመስ+ (Erasmus+) የትምህርት፣የስልጠና፣የወጣቶችና ስፖርት ትብብር ፕሮግራሞች ላይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለሚያደርገው ጥረት ምስጋናቸውን አቀርበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሜጀና በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ኤራስመስ+ (Erasmus+) የትምህርት፣የስልጠና፣የወጣቶችና ስፖርት ትብብር ፕሮግራሞች አስፈላጊነትና ቁልፍ የአተገባበር ስልቶችን ያጋሩ ሲሆን በዚህም የሚገኘውን ድጋፍ አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ዝርዝር ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0Z5Dc5hBFmeoz2n5eyctairRCE7Y8p4DCjkzG6aiDZQjEsWGq7AgsPcsxDccRLvF3l&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO