Get Mystery Box with random crypto!

በቀጣይ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ | Ministry of Education Ethiopia

በቀጣይ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው:- ትምህርት ሚኒስቴር
...............................................................................
ህዳር 17/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ
እንደገለጹት በቀጣይ ሁለት ዓመታት 9 ዩኒቨርስቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

በ32ኛው የትምህርት ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ትይዩ መድረክ መክፈቻ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት በማቅረብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ቴክኖሎጁ የሚጠቀም ፣ የሚመራመርና በሥነምግባር የታነጸ ዜጋ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።

የጉባዔው ዓላማ በከፍተኛ ትምህርቱ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ በመወያየት በቀጣይ ስለሚወሰዱ የእርምትና የለውጥ እርምጃዎች ላይ የጋራ ግንዛቤና አቋም ለመያዝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር በሽር አብዱላሂ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ በአፕላይድ ዩነቨርስቲ የተልዕኮና ትኩረት መስክ ለይቶ በተፈጥሮ ሀብት እርብቶአደርና እንስሳት ልማት እንዲሁም በምግብ ዋስትና ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ መስክ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02S887Ytq9QQBn55bzT54gyCDpavzUk6oBsQKyC5N9AwS293A1Wm6HGZU7cVGqsCjzl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO