Get Mystery Box with random crypto!

የስራና ተግባር ትምህርት በቀጣይ ዓመት ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ። . | Ministry of Education Ethiopia

የስራና ተግባር ትምህርት በቀጣይ ዓመት ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ።
.............................................
ህዳር 17/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒሰቴር ) 32ኛው የትምህርት ጠቅላላ ጉባኤ አካል የሆነው የዘርፎች ትይዩ ጉባኤ በሶማሌ ብሄራዊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የጉባኤው ዋና አላማ በእቅድ ትግበራ ወቅት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ባጋጠሙ ችግሮች ላይ የመፍትሄ አማራጮችን ለመቀየስ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ወደ ሙሉ ትግበራ የተገባ መሆኑ እና የስራና ተግባር ትምህርት በቀጣይ ዓመት ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ የተለያዩ የለውጥ መርሃ-ግብሮች ተቀይሰው ወደ ተግባር መግባታቸውንም ጠቁመዋል።

የበጀት እጥረት፣ የስምሪትና መልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ያለመሆን፣የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ መሆኑ እና የመሳሰሉት ችግሮች የትምህርት ስርዓቱ የወቅቱ ፈተናዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በመድረኩ የሶማሌ ብሄራዊ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱላሂ አብዲ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid08Ni8hmbg2MDHq2WXLz93LB4d4FuYSJzG2yFdruADXku2jMPAEeTgsCEAy2GowF7Gl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO