Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀት የበለጸገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ብዙ መሥራት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀ | Ministry of Education Ethiopia

በእውቀት የበለጸገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ብዙ መሥራት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስገነዘቡ
..................................................................................

ህዳር 18/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) 32ኛው አገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በጅግጅጋ እየተካሄደ ይገኛል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በጉባዔው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዕውቀት የሚጎለብተው በከፍተኛ ትብብርና መደጋገፍ ነው።

በመሆኑም ዕውቀት የበለጸገ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደአገር ገና ብዙ መሥራት እንደሚገባ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስገንዝበዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ መቀጠል እንደማይቻል የጠቆሙት ሚኒስትሩ ለሚቀጥለው ትውልድ የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ዕውቀት መስጠት ይገባል ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም የትምህርት ጉባዔው የተዘጋጀው ለሥራ ፣ለዕውቀት ፣ አብሮ ለመኖርና ለመሣሰሉት ያለንን አመለካከት ለመቀየር መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።
ሙሉ ዜናውን

https://www.facebook.com/100064682287722/posts/pfbid02smZknTxfdvCUr1ZQPHAvU9YtRJhmG98W6VLK8CGg6FxYi41XN2d4a8B6m6hTCQZMl/?mibextid=9R9pXO

የትምህርት ሚኒስቴር ዜናዎችን

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
ይከታተሉ