Get Mystery Box with random crypto!

ከ10 ነጥብ 6ሚሊዮን በላይ መጻህፍት ለክልሎች ተከፋፈሉ .......................... | Ministry of Education Ethiopia

ከ10 ነጥብ 6ሚሊዮን በላይ መጻህፍት ለክልሎች ተከፋፈሉ
...................................................

ህዳር 13/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጁ ከ10 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ መጻህፍት ለክልሎች ተከፋፍለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ወደ አገር ውስጥ የገባ 10 ሚሊዮን 649 ሺ የ2ኛ ደረጃ መጽሀፍት ለክልሎች ተከፋፍለዋል።

በጅቡቲና በደረቅ ወደብ የሚገኝ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን መጻሕፍትም እስከ መጪው ታህሳስ ወር አጋማሽ ድረስ ተጓጉዞ ለክልሎችእንደሚሰራጭ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።

40 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ወጥቶባቸው ህትመታቸው የተጠናቀቁት መጻህፍት ከ9ኛእስከ 12ኛ ክፍል ለማስተማሪያነትና ለመምህሩ መምሪያነት የሚያገለግሉ ናቸው።

የመጽሀፍት ስርጭቱ በአገሪቱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያለውን የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የመማሪያ መጻሕፍት እጥረት እንደሚያቃልለው ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

የመጻሕፍት እጥረትን ለመፍታትም አሁን ከታተሙት የ20 ነጥብ 7 ሚሊየን መጽሐፍት በተጨማሪ በቀጣይ ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማሳተም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሃኑ አብራርተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
ይከታተሉ