Get Mystery Box with random crypto!

'ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥ | Ministry of Education Ethiopia

"ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል" ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ
.............................................
ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት የሰው ሃይል አደረጃጀትና የበጀት አመዳደብን የተመለከተ አውደ ጥናት  አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል ብለዋል።

እንደ ትምህርት ሴክተር ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ትምህርት እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተው ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት ከማቅረብ አንፃር በርካታ ሥራዎች እንደሚጠበቁም አብራርተዋል።

ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው በሀገራችን ልማት የበኩላቸውን መወጣት ይችላሉ ያሉ ሲሆን  ለሁሉም ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትና ሥልጠና በፍትሃዊነት ለመሥጠት የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ስትራቴጂ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን አደረጃጀቱን ማስተካከልና  በበጀት  መደገፍ እንደሚገባ አንስተው ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮሐንስ ወጋሶ በበኩላቸው በልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ውስብስብ ችግሮች መኖራቸውን አንስተው ለነዚህ ችግሮች ትክክለኛ መፍትሄ አስቀምጦ መሥራት ይገባል ብለዋል።