Get Mystery Box with random crypto!

የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መከታተያ የመቁ | Ministry of Education Ethiopia

የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መከታተያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።
==============//==
ጥቅምት 23/2016 ዓ .ም (ትምህርት ሚኒስቴር ) በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም መከታተያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር ) እንደገለጹት በ2016 በግልና የመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ /Remedial Program / የሚከታተሉ ተማሪዎች መቁረጫ ነጥብ እንደተፈተኑት የትምህርት ዓይነት ብዛት 30% እና ከዚያ በላይ ሆኗል ።

በዚህም መሠረት በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር የመቁረጫ ነጥብ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 መሆኑን አስታውቀዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 የማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 መሆኑን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ታዳጊ ክልሎች ተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 መሆኑን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች መግቢያ 192 ታዳጊ ክልሎች ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች መቁረጫ180 መሆኑን አመልክተዋል።

ሙሉ መረጃው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0DDFte8gZynMFNPjAJqQ3E4BgCn54bGD3wY5sX2sjkPmbtaJFBRF6xjnxaR4X2hiSl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO