Get Mystery Box with random crypto!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ-አይቢኢ የቦርድ ፕሬዝዳንት ስቬን ኦስትቬት ጋር ተወያዩ። ------ | Ministry of Education Ethiopia

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ-አይቢኢ የቦርድ ፕሬዝዳንት ስቬን ኦስትቬት ጋር ተወያዩ።
---------------------------------
ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር እና የዩኔስኮ ብሄራዊ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ከአለም አቀፍ የትምህርት ቢሮ (UNESCO-IBE) ቦርድ ፕሬዝዳንት ስቪን ኦስትቬት ጋር በፈረንሳይ በሚገኘው የዩኔስኮ ዋና መስሪያቤት የጎንዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የትምህርት ሥርዓት ለማሻሻል እና ለማዘመን ያከናወናቸውንና በመተግበር ላይ ያሉ የለውጥ ተግባራትን አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያ በተለይም በዘርፉ በተለዩ የትምህርት መስኮች ላይ የውጭ ልምድ እንደሚያስፈልጋት በአጽናኦት የተናገሩ ሲሆን የዩኔስኮ-አይቢኢ የቦርድ ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው የትምህርት ስርዓቱን በአዲስ መልክ ለማሻሻልና ለማዘመን ሚኒስቴሩ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀው ቢሮው ጥረታቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02roy5vu64ni87iEN6VtDtpgDqnGQNtVxdExXfKXYMZcxA9iYqQR4QLHSGMiybQr3Xl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO