Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ ከIIEP-UNESCO ዳይሬክተር ጋር ውይይት አካሄዱ .. | Ministry of Education Ethiopia

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ ከIIEP-UNESCO ዳይሬክተር ጋር ውይይት አካሄዱ
...................................................................
በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ከተማ እየተካሄደ ባለው 42ኛው የዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን የትምህርት ሚኒስትርና የብሔራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ ከIIEP-UNESCO ዳይሬክተር ማርቲን ቤናቪድሠን ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ሁለቱ ወገኖች በትምህርት ሚኒስቴር ፣ አዲስ የተዋቀሩ ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች እና የዩኒቨርሲቲ የእቅድ ዝግጅት ባለሙያዎችን አቅም መገንባት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም በከፍተኛ ትምህርቱ ዘርፍ ያሉትን የፖሊሲ ማዕቀፎችና በተለይም ዩኒቨርስቲዎችን በትኩረት መስክ መለየት እና የከፍተኛ ትምህርት ተቆማዊ ነፃነትን ማረጋገጥ ላይ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎች ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ይህን ተከትሎም የIIEP-UNESCO ዳይሬክተር ማርቲን ቤናቪድሠን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

በውይይቱ መጨረሻም ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን ትብብር በማደስና በማጠናከር በትምህርቱ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን ከመግባባት ላይ ደርሠዋል።