Get Mystery Box with random crypto!

የማላዊ ሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዳይሬክትር ከትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት | Ministry of Education Ethiopia

የማላዊ ሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዳይሬክትር ከትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄዱ::
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: :::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የካቲት 13/2016 ዓ.ም(ትሚ) በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሸኔ የማላዊ ትምህርት ሚኒስቴር ሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዳይሬክትር የሆኑትን ፕ/ር ቻሞራ ሜኬካን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ የትብብር መስኮች በተለይም በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ትብብር ለመፍጠር በሚያስችል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡

በተያያዘም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በኩል በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎረም ተግባራትን አስመልክቶ በክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በኩል ገለጻ ተደርጓላቸዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምር እና ማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸው ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የትብብር ፍላጎት ለመለየት እና ወደፊት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለማስጀመር መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡