Get Mystery Box with random crypto!

#ማስታወቂያ በቻይና ሀገር ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ለነበራችሁ ተማሪዎች! በዓለም አቀፍ ደረጃ | Ministry of Education Ethiopia

#ማስታወቂያ

በቻይና ሀገር ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ለነበራችሁ ተማሪዎች!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ይሄንን ተከትሎ የቻይና መንግስት ባወጣው የኮቪድ- 19 ፕሮቶኮል ምክንያት በአጋጣሚ ወደሀገራችሁ መጥታችሁ መመለስ ላልቻላችሁ ተማሪዎች መንግስታችንና ቻይና ሀገር የሚገኘው ኤምባሲያችን ወደ ቻይና ተመልሳችሁ ያቋረጣችሁትን ትምህርት እንድትከታተሉ እየሰሩ ይገኛል።

ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘው ፎርም መሰረት አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላት እጅግ ቢዘገይ እ.ኤ.አ. እስከ June 20/2022 ብቻ በሚከተለዉ ማስፈንጠሪያ በመግባት ፎርሙን ሞልታችሁ በተከታዩ ኢሜይል አድራሻ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ
ይህ ማስታወቂያ የሚመለከተው በኢትዮጵያ መንግስት የተላኩትን ብቻ ነው።

Link- https://moe.gov.et/AddReso

Email፡ daddiketema@gmail.com, educationattache@ethiopianembassy.org.cn

ትምህርት ሚኒስቴር