Get Mystery Box with random crypto!

ሳውዝ ዌስት አካዳሚ በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 200 ሺ ብር የ | Ministry of Education Ethiopia

ሳውዝ ዌስት አካዳሚ በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 200 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ፡፡

የአካዳሚው ማነጅንግ ዳይሬክተር አቶ ከፍያለው ከተማ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት ድጋፉ በትምህርት ቤቱ እየተንቀሳቀሱ ካሉ ተጓዳኝ ትምህርቶች መካከል የበጎ አድራጎት ክበብን በማጠናከር የተሰበሰበ ነው ብለዋል ፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ መዝገቡ ቢያዝን በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት አካዳሚው ላበረከተው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቀርበዋል፡፡

በድጋፍ ርክክቡ ወቅት አቶ መዝገቡ እንደተናገሩት የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት የስራ አጋርነትን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡

ድጋፉም በተለያዩ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ለወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ግንባታ ይውላል ብለዋል አቶ መዝገቡ፡፡