Get Mystery Box with random crypto!

'ሁሉም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ ተወስኗል' በሚል | Ministry of Education Ethiopia

"ሁሉም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ ተወስኗል" በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የትምህርት ሚኒስቴርን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን በመልቀቅ ውዥንብር እየፈጠሩ ያሉ የማህበራዊ ገፆችን እያየን ነው።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን አውቃችሁ ትኩረታችሁን ትምህርታችሁ ላይ ብቻ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰቡ ይህንን በመረዳት ከተሳሳቱ መረጃዎች ራሳችሁን በማራቅ ሌሎች እንዳይሳሳቱ የማድረግ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብን የትምህርት ሚኒስቴር ትክከለኛ የመረጃ ማሳረጫዎች የሚከተሉት መሆናቸውን እናሳውቃለን

ፌስቡክ-https://www.facebook.com/fdremoe

ቴሌግራም - https://t.me/ethio_moe

ሊንክድኢን- https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia

ትዊተር- https://twitter.com/fdremoe?t=dFhfr8QytU_6LqQuVUIp2A&s=09

ከእነዚህ ውጭ ባሉ አድራሻዎች እኛን የሚመለከቱ አሳሳች መረጃዎች ስታገኙ እንድትጠቁሙንም በአክብሮት እንጠይቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር