Get Mystery Box with random crypto!

የተማሪዎች፣ የመምህራና ወላጆች የመመሰጋገንና የመደናነቅ ቀን ተከበረ፡፡ --------------- | Ministry of Education Ethiopia

የተማሪዎች፣ የመምህራና ወላጆች የመመሰጋገንና የመደናነቅ ቀን ተከበረ፡፡
--------------------------------------------

ትምህርት ሚኒስቴር ከቅን ኢትዮጵያ ማህበር ጋር በመተባብር አገር አቀፍ የመምህራን፣ የተማሪዎችና የወላጆች የመደናነቅና የመመሰጋገን ቀን ለሁለተኛ ጊዜ አከበረ።

የቅን ኢትዮጵያ ማህበር መስራች የሆኑት ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና እንደተናገሩት የመድረኩ ዓላማ የተማሪዎች፣ የመምህራና ወላጆች የመመሰጋገንና የመደናነቅ ባህል ይበልጥ ለማሳድግ ታስቦ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ቶሎሳ ትምህርት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ይዘው የሚወጡት ዲፕሎም ወይም ዲግሪ ባሻገር በትምህርት ቤት ቆይታ በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ለቤተሰብ እና ለአገር ኃላፊነት ብቁ ለመሆን የሚዘጋጁበት ሂደት ነው።

ትምህርት ቤቶች የአስተዋዮች፣ የአስታራቂዎች፣ የመካሪዎችና የጨዋዎች ማሳደጊያ ማዕከል መሆን እንደሚገባም ዶ/ር ቶሎሳ ተናግረዋል።

“በመሐከላችሁ ሆነ በዘመናችሁ ማንም ከቋንቋው፣ ከብሔሩ፣ ከፆታው፣ ከችሎታው ከማንነቱ የተነሳ የሚገለል፣ የሚሰደድና አድማ የሚደረግበት ኢ-ሰብዓዊነት ስለሆነ በፍፁም መኖር የለበትም”፡- ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና ።

መምህራንና ወላጆችም ተማሪዎች ፍቅርን፣ መከባበርን፣ ቅንነትን፣ይቅርታ መጠየቅን፣ እውነትንና መልካምነት እንዲማሩ ለማድረግ ኃላፊነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በዕለቱም ተማሪዎች፣ መምህራንና ለወላጆች ላበረከቱት የቅንነትና የመልካምነት አስተዋጽኦ የመመሰጋገንና የመደናነቅ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡