Get Mystery Box with random crypto!

በአሜሪካ ኢምባሲ የትምህርት ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ተክለሚካኤል ተፈራ ተቋማቸው በተለይ የ2ኛ | Ministry of Education Ethiopia

በአሜሪካ ኢምባሲ የትምህርት ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ተክለሚካኤል ተፈራ ተቋማቸው በተለይ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የማማከርና የመደገፍ አገልገሎት በስፋትና በጥልቀት ተጠናክሮ እንዲሰጥ ለማስቻል ለሚመለከታቸው አካላት የሚሰጠው  የአቅም ግንባታ ስልጠና  ዘዴን በተመለከተ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላትን መልምሎ ወደ ማዕከል በመጥራት፥ በቀጥታ በበይነመረብ በማግኝት፥ የተለያዩ ግብኣቶችን በመስጠት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የስልጠናው ይዘት ሳይንሳዊ እውነታንና የሀገራት ተሞክሮዎችን መሰረት ያደረገ ሲሆን በመክፈቻውም ወቅት አሜርካን ኢምባሲ 560 የተለያዩ የእንግልዝኛ ቋንቋ ማዳበሪያ መጽሃፍትን ለትምህርት ሚኒስቴር አበርክቷል፡፡