Get Mystery Box with random crypto!

የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ያለማንም ተጽእኖ ዝንባሌያቸውንና ችሎታቸውን ብቻ ተከትለው የከፍተኛ | Ministry of Education Ethiopia

የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ያለማንም ተጽእኖ ዝንባሌያቸውንና ችሎታቸውን ብቻ ተከትለው የከፍተኛ ትምህርት የሙያ መስካቸውን  መርጠው እንድማሩ ማማከርና መደገፍ ለዘላቂ የህይወት ስኬታቸውም ሆነ ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት ውጤታማንት ወሳኝነት እንዳለው ተገለጸ፡፡
===============================

ትምህርት ሚኒስቴር ከአሜሪካን ኢምባሲ ጋር በመተባበር የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ዝንባሊያቸውን እንዲለዩ፥ እንዲያዳብሩና በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት የሙያ መስካቸውን እንዲመርጡ የማማከርና ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡ መምህራንን ለሚያዘጋጁ ከ70 የመንግስትና የግል ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ መምህራንና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ያለማንም ተጽእኖ ችሎታቸውን ብቻ ተከትለው የከፍተኛ ትምህርት የሙያ መስካቸውን  መርጠው እንዲማሩ የሚያስችል የማማከርና የመደገፍ አገልግሎት መስጠት ለዘላቂ የህይወት ስኬታቸውም ሆነ ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት ውጤታማነት ወሳኝነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ኢምባሲ የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ከፍተኛ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ዝንባሌያቸውን እንዲለዩ፥ እንዲከተሉና እንዲያሳድጉ ማድረግ የሚያስችል የማማከርና ድጋፍ አገልግሎት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ይበልጥ ተጠናክሮ እንድሄድ እያበረከተ ላለው ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ  አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡