Get Mystery Box with random crypto!

በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ። ------------- | Ministry of Education Ethiopia

በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ።
-----------------------
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ( ፕሮፌሰር) አዲስ ከተመደቡ የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

አዲስ የተመደቡ የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ውይይቱ በትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና የቦርድ አባላቱ ሃላፊነታቸውን አውቀው በባለቤትነትና በእውቀት እንዲመሩ ለማስቻል ያለመ ነው።

በቀጣይም በዩኒቨርስቲ የትምህርት ጥራት ፣ የሀብት ብክነት መከላከል እና የዩኒቨርስቲ አስተዳደር ነፃነት ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በአዲሱ ሪፎርምም የስርዓተ ትምህርት ለውጥ፣ የዩኒቨርስቲ የመስክ ልየታ ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነፃነት እንዲሁም ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መስጠት የተካተቱ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለማጠናከር አዳዲስ የቦርድ አመራሮችን መሾሙ ይታወሳል።