Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-26 11:30:03
በአጣየ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ በአርሶ አደሮች ላይ ጉዳት ደረሰ

በአጣዬ ዙሪያ አርሶአምባ እና አላላ በሚባሉ አካባቢዎች ታጣቂዎች ሰሞኑን እርሻ ላይ በነበሩ አርሶአደሮች ላይ በከፈቱት ተኩስ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል። ከብቶችንም ነድተው ወስደዋል።

ይህ የሆነው ልዩ ሀይሉ ከአካባቢው ከወጣ በኋላ ነው ተብሏል። አካባቢው አሁን ላይ በኮማንድ ፖስት ስር እንደሆነ ይታወቃል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 11:25:13 ከእስር አስፈታለሁ ባዩ ተከሰሰ

በሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እየታየ በእስር ላይ ያለውን ተከሳሽ ክሱ እንዲቋረጥና ከእስር እንዲፈታ አደርጋለሁ በማለት 2 ሚሊዮን ብር ጠይቆ ከዚህ ውስጥ 310 ሺ ብር በተቀበለው ተከሳሽ ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተበት

በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እየታየ በእስር ላይ ያለውን ተከሳሽ ክሱ እንዲቋረጥና ከእስር እንዲፈታ አደርጋለሁ በማለት 2 ሚሊዮን ብር በመጠየቅ ከዚህ ውስጥ በቅድሚያ 310 ሺ ብር በተቀበለው ተከሳሽ ላይ በፈፀመው በግል ተሰሚነት መነገድ የሙስና ወንጀል እና ህገ-ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ ተመሰረተበት፡፡

ሳሙኤል ታደሰ የተባለው ተከሳሽ በ1ኛ ክሱ ላይ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 29(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ፤ በ2ኛ ክሱ ላይ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ. 780/2005 አንቀፅ 29 (1)(ሀ) ላይ የተደገገውን በመተላለፍ ሁለት ክስ ቀርቦበታል፡፡

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ በ1ኛ ክሱ ላይ በአንድ የመንግስት ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰራተኛ ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ልዩ መብት ወይም ጥቅም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ፀረ-ሙስና ወንጀል ችሎት እየታየ በእስር ላይ ያለውን አለማየሁ ሶሬ የተባለን ተከሳሽ ከእስር ለማስፈታት ቀኑ በውል ባልታወቀ የካቲት ወር 2015 ዓ.ም አራዳ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ፒያሳ ጎንደር ሆቴል ውስጥ 1ኛ እና 2ኛ የዓቃቤ ህግ ምስክሮችን ካገኛቸው በኋላ እኔ ሁሉንም አቃቤ ህጎችንና ሃላፊዎችን ስለማውቅ እነሱን አናግሬ የተከሳሽ ክስ እንዲቋረጥና ከእስር እንዲፈታ አደርጋለሁ በማለት እና ይህንን ተሰሚነቱን ለማሳየት በማሰብ 1ኛ ምስክርን በፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ቢሮ ድረስ ከወሰደው በኋላ፤

በዚሁ የካቲት ወር 2015 ዓ.ም ቦሌ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 1ኛ ምስክርን በማግኘት ለጉዳዩ ማስፈፀሚያ 2 ሚሊዮን ብር እንደሚከፍሉት በመንገር ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ከዐቃቤ ህግ ቢሮ ለማውጣት በቅድሚያ 350 ሺ ብር ክፈል በማለት ከጠየቀው በኋላ፤ በ1ኛ ምስክር ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር በተለያዩ 3 ቀናት 180 ሺ ብር በባንክ እዲተላለፍለት አጀ
ድርጓል። በመቀጠልም ተሰሚነቱን የበለጠ ለማሳየት በማሰብ 1ኛ ምስክርን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ድረስ በመውሰድና ሰነዶችን ወደ ዐቃቤ ህግ ቢሮ አስገብቻለሁ ጉዳዩ ለውሳኔ እንዲቀርብ ተጨማሪ 150 ሺ ብር ያስፈልጋል በማለት ከዚሁ ምስክር ጋር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ደሳለኝ ሆቴል ገንዘቡን ይዞ እንዲመጣ ተቀጣጥረው ከተገናኙ በኋላ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ80 ሺ ብር ቼክ እና 50 ሺ ብር ጥሬ ገንዘብ ከተቀበለ በኋላ ሊያመልጥ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል።

በአጠቃላይ ተከሳሽ እንዳለው ያስመሰለውን ተሰሚነት በመጠቀም በአንድ የመንግስት ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰራተኛ ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ልዩ መብት ወይም ጥቅም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ጠቅላላ 310 ሺ ብር የተቀበለ በመሆኑ በፈፀመው በግል ተሰሚነት መነገድ የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡

በ2ኛ ክሱ ላይ ተከሳሽ ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባዉ የንብረቱን ህገ- ወጥ ምንጭ ለመደበቅ ወይም ለመሸፈን ወይም ከወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ በማሰብ ከላይ በ1ኛ ክስ በተጠቀሰው መልኩ ከጠየቀው ገንዘብ ውስጥ ከ1ኛ ምስክር ገቢ የተደረገለትን ገንዘብ ህገ-ወጥ ምንጭ ለመደበቅ እና ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ገንዘቡን በሌላ ግለሰብ የባንክ ሂሳብ ያስተላለፈ በመሆኑ፤ በአጠቃላይ ተከሳሽ ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የንብረቱን ህገ-ወጥ ምንጭ ለመደበቅ ወይም ለመሸፈን ወይም ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ በማሰብ በፈፀመው ህገ-ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

ጉዳዩን ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ተከሳሽ በተገኘበት ክሱ በችሎት የተነበበለት ሲሆን በዋስትና ጉዳይ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል።(ፍትሕ ሚ/ር)
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.7K views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 11:24:39
ዛንዚባር
በፌደራል መንግሥቱ እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት(ሸኔ) መካከል የሚደረገው ድርድር ከትናንት ማክሰኞ ሚያዚያ 17/2015 ዓ.ም. በታንዛኒያዋ ራስ ገዝ ግዛት ዛንዚባር መጀመሩ ይታወሳል።የሰላም ንግግሩ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው ተብሏል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.7K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 22:59:38
የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደ
የአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል አካውታቸው ታግዷል። የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ የ35 የአማራ ባለሃብቶች እንዲሁም 2 የአፋር ባለሃብቶች በባንክ ያላቸው ገንዘብ እንዲታገድ ለሁሉም ባንኮች ተፅፏል። ደብዳቤውን ተመልከቱት።
የሞቱ ሰዎችም ጭምር በእገዳው ስማቸው ተጠቅሷል(ዘሀበሻ)።
ሚያዝያ 17/2015 ዓ.ም

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.6K views19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 12:28:55 ብሄራዊ የተሃድሶ ኮምሽን ተግባራዊ ስራ ለመጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ። ባለፉት ሶስት ወራት ኮምሽኑ ዓላማውን በማስተዋወቅና ግብረ መልስ በመሰብሰብ ላይ አተኮሮ ነበር። ኮምሽኑ በሀገሪቱ ያለ እስከ ሶስት መቶ ሺ የሚደርሱ ተዋጊዎችን በትኖ በመደበኛ ሕይወት የማቋቋም ሀላፊነት አለበት። (Wazema)

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
4.2K viewsedited  09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 12:20:49
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የ72 ሰዓት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለ72 ሰዓት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አስታወቁ።

በተቀናቃኝ ጎራ ተሰልፈው እየተፋለሙ ያሉት የሱዳን ጦርና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ሰኞ እኩለ ሌሊት እንደተጀመረ ተገልጿል።

በሱዳን ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ የአሁኑን ጨምሮ ቢያንስ ለሦስት ጊዜ ያህል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር ፤ እስካሁን የነበሩት የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተፋርሰው ውጊያው ቀጥሎም ቆይቷል።

በመደበኛው ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ለ48 ሰዓታት ያህል ድርድር ከተደረገ በኋላም የአሁነኛው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን ብሊንከን ገልጸዋል።

ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በተናጠል አስታውቀዋል።

ጦርነቱ ሚያዝያ 7/ 2015 ዓ.ም ከተቀሰቀሰበት እለት ጀምሮ ቢያንስ ከ400 በላይ ዜጎች ሕይወት መቀጠፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
4.1K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 12:20:15
“የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ”- ጄነራል ዳጋሎ

ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋና አዛዥ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ” አሉ።

ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ “አሁን ላይ እየተዋጋን ያለነው ከሱዳን ጦር ጋር ሳይሆን ከቅጥረኛ ኃይሎች ጋር ነው፤ ምክንያቱም 90 በመቶ የሱዳን ጦር ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ብለዋል።

ዳጋሎ አክለውም፤ “ከዚህ በኋላ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዣ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተቀምጦ መነጋገር ምንም ዋጋ እንደሌለውና አልቡርሃን ከዚህ በኋላ ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ጦርነት አልፈልግም ነበር፣ ከጦርነት ይልቅ ሰላም እና መረጋጋትን ነው የምመርጠው” ያሉት ዳጋሎ፤ “ወደ ጦርነት እንድንገባ የገፋፋን አልቡርሃን ነው፤ አሁን ግን እጁ ላይ ምንም አልቀረለትም” ሲሉም ተናግረዋል Alain።
@ET_SEBER_ZENA
3.7K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 07:33:26
በሕዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት በማጠናከር ለሠላም ስምምነቱ መጽናት በቁርጠኝነት እንሰራለን

የአፋርና አማራ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች

በሕዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት በማጠናከር ለሰላም ስምምነቱ መጽናት በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ የአፋርና አማራ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳደሮች ገለጹ፡፡

የፕሪቶሪያውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ በሂደቱ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ጦርነት ይብቃ ሰላምን እናጽና በሚል መሪ ሃሳብ የእውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተከናውኗል።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለስምምነቱ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅና ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህን ወቅት በቀጣይ የሠላም ስምምነቱን በህዝብ ለህዝብ ትስስር ማጽናት እንደሚገባ አስገንዝበው፤ ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሚመራና የሁሉንም ክልሎች ርዕሳነ- መስተዳደሮች ያካተተ ቡድን በተያዘው ሳምንት ወደ መቀሌ እንደሚያቀና ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ በቀጣይ የሠላም ስምምነቱን ይበልጥ ለማጽናት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ነው የገለጹት፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ጦርነቱ ኢትዮጵያን በብዙ ዋጋ እንዳስከፈላት ነው ያብራሩት፡፡

ልዩነቶችን በግጭትና ጦርነት ለመፍታት የሚደረጉ ሙከራዎች ውጤታቸው የጋራ ጥፋት መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ የሰላም ስምምነቱ እንዲጸና ሁሉም ዜጋ በባለቤትነት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በኋላ የሚያስፈልገው በኢትዮጵያዊ አንድነት ስር የዜጎችን ወንድማማችነት ትስስር ማጠናከር ነው ብለዋል፡፡

የአማራና የትግራይ ህዝብ ለዘመናት አብሮ የኖረ፤ በባህል እንዲሁም በኢኮኖሚ የተሳሳረ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳደሩ ዶክተር ይልቃል፤ በቀጣይ ይህንን አብሮነት ይበልጥ ለማጠናከር እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

የሚያጋጥሙ ልዩነቶችንም በውይይትና በመነጋጋር ብቻ ለመፍታት እንደሚሰራም እንዲሁ፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያውያን መካከል ያለው አብሮነት ጠንካራ ነው፤ ይህን ማስቀጠል ደግሞ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡

ሰላም ኢትዮጵያውያንን በማስተሳሰር የተሻለ ነገን በጋራ እንዲገነቡ የሚያስችል ቁልፍ መሳሪያ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ አኳያ የሰላም ስምምነቱ ይዞት የመጣውን ብሩህ ተስፋ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት አለብን ነው ያሉት፡፡

ሁሉም ዜጋ ጦርነቱ በኢትዮጵያ ላይ ካስከተለብን ጉዳት በሚገባ በመማር "ጦርነት ይብቃ" ማለት እንዳለበትም ርዕሳነ መስተዳደሮቹ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በጦርነቱ የባከኑ ጊዜያትን በልማት ለማካካስ በጋራ መነሳት እንደሚገባ ጠቅሰው፤ በህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት በማጠናከር ለሰላም ስምምነቱ መጽናት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ርዕሳነ መስተዳደሮቹ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
3.9K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 05:58:40 በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ የእምነት ቅርፅ የያዘ ግጭት ዛሬም ለ2ኛ ጊዜ መከሰቱን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።በተቻለ መጠን ይህንን ጉዳይ በአስቸኳይ ባለበት የመፍታትና የማስቀረት ተግባር ቢከናወን መልካም ነው።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.7K viewsedited  02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 05:58:40 የጉምሩክ ኮሚሽን ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል የገቢ እና የወጭ 447·9 ሚሊየን ብር የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን አስታውቋል።አሁንም የቁጥጥር ስራ በሁሉም ቅርንጫፎች ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክቷል።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.6K viewsedited  02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ