Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-20 13:57:11 የጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤቶች ሊከሰሱ ነዉ ተባለ

ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት በኬኒያ የታገተው የአቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል  ቤተሰቦች በሁለቱ ተቋማት ላይ ክስ ሊመሰርቱ እንደሆነ አስታዉቀዋል፡፡

በሳምሶን ጉዳይ  የውጭ ጉዳይ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ነው ያሉት ቤተሰቦቹ፤ ክስ ሊመሰሩት መሆኑ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሃለፎም እስካሁን በመስራቤቶቹ በኩል እየተሰጠን ያለው መረጃ ለዜጋ የሚመጥን አይደለም ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተሰጠን ምላሽ እና አሁንም እየተሰጠን ያለው ተመሳሳይ ነው ብለዋል፡፡

በኬኒያ የሚገኝው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግለሰቡ ዙርያ ምርመራ እያካሄድን ነው ከማለት ውጭ የሚሰጠን ተስፋ የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፌደራል እንደዚሁም በኦሮሚያ ክልል ማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ዳባ ጩፋ የአቶ ሰምሶን ጉዳይ እልባት አለማግኝት በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድክመት ነው ብለዋል፡፡

ኤምባሲው ልክ እንደ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ ሲጠበቅበት ነገሩን በቸልታ እያለፈው ይገኛል ብለዋል፡፡

የአቶ ሳምሶን ቤተሰቦች ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ቢያቀርቡም አንድም ውጤት አለማምጣቱትን ነው የገለጹት፡፡

በመሆኑም የአቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል   ቤተሰቦች በሁለቱ ፅሕፈት ቤቶች ላይ ክስ በመክፈት የልጃቸዉን አድርሻ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡                      
(ሄኖክ ወልደ ገብርኤል)
ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
3.1K views10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 10:25:01
ራያ ዩንቨርስቲ ስትማሩ ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ ዩንቨርሲቲው ከላይ የሚታየውን ማስታወቂያ አውጥቷል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.2K viewsedited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 10:18:19 በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር ላይ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ!

የሱዳን ሰራዊት ከሕወሓት ጋር የአብይ መንግስት የሚያደርገውን ጦርነት ተከትሎ ወረራ በመፈጸም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቆ መግባቱ ይታወሳል። ዘልቆ በመግባትም ከፍተኛ ጥፋት ከማድረሱም በላይ ተጨማሪ መሬቶችን በቁጥጥር ስር በማዋል ይዞ መቆየቱ ይታወቃል። ሱዳን በአሁን ሰአት በአልቡርሃን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ጦር መካከል ካርቱም ውስጥ ጦርነት ላይ ናቸው። በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ላይ ያሉ ወታደሮችም የኢትዮጵያን ጦርና የአማራ ልዩ ኃይልን ለመተንኮስ ጥረት ማድረጋቸውን ተከትሎ ጦርነት መቀስቀሱን አልሱዳን የተሰነው የዜና ምንጭ ዘግቧል ።  ከምሽቱ ስምንት ሰአት በፊት የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥቃት ሰንዝረው ካምፖችን በማውደም እስረኞችን በማስፈታት መመለሱን ተሰምቷል። ሲል አል ሱዳኒ ዘግቧል።

የሱዳን ሰራዊት በአል ፋሽቃ አል-ሱራ ላይ የኢትዮጵያውያንን ወረራ ለመመከት ተጋድሎ እያደረገ ነው ያለው አልሱዳኒ የተሰነው የዜና ምንጭ  በሰው ህይወት እና በመሳሪያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ሲል ገልጿል። ዘገባው አያይዞም በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ ጦር በታንክ፣ በታጠቁ መኪኖች እና ብዙ እግረኛ ወታደሮች ታግዞ በአል ፋሽቃ አል-ሱግራ ላይ ወረራ እና ጥቃት ፈጽሟል። በሱዳን ወታደሮች እና በመሳሪያዎች ላይ ከባድ ኪሳራ አድርሶባቸዋል ሲል ተናግሯል።

የአልሱዳን ዜና መረጃ እንደሚለው በካርቱም በሱዳን ወታደሮች እና በፈጣን የድጋፍ ሃይሎች መካከል የተካሄደው ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በምስራቅ ድንበር ላይ የሰፈረው የሱዳን ጦር ሃይሎች በኢትዮጵያ ሃይሎች እና ካምፖች ውስጥ የነቃ እና ያልተለመደ እንቅስቃሴ ሲከታተሉ ቆይተዋል። እንዲሁም በኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች የተካሄደው ከፍተኛ የስለላ እና የቁጥጥር ስራ በአል-ፋሽቃ አል-ሱራ ውስጥ በአብዱራፊ ሴክተር ውስጥ በአጥቂ ስፍራዎች ተጨማሪ የታጠቁ ሰዎች ተስተውለዋል፣ እና ይህ በካርቱም ውስጥ በታጣቂ ሃይሎች እና በፈጣን የድጋፍ ሃይሎች መካከል የተፈጠረው ክስተት ከጀመረበት ጊዜ ጋር ተገጣጥሟል። ይላል

የዜናው ምንጭ የኢትዮጵያ ወታደሮች ብቻ ሳይሆኑ ወረራውን የፈጸሙት የአማራ ክልል “ፋኖ” ሚሊሻ፣ ​​ልዩ ሃይል ያቀፈ ነው ያለ ሲሆን የነዚያ ሃይሎች አላማ አል ፋሽቃ አል-ስጉራ እና ደቡብ ከጋላባት ደቡብ እና ከባሳንዳ በስተደቡብ ወደ አል-ዲንድር ሀንጋር ለመመለስ እና አሁን ያለውን የሱዳን ሁኔታ በመጠቀም የግብርና መሬቶችን ማስመለስ ነው። ብሏል ዘገባው በትናንትናው እለት የሱዳን ሃይሎች በአቡ አል ቱዩር ሴክተር ጥቂት ኢትዮጵያውያን የስለላ አካላትን ተከታትለው መትረየስ ተኩሰው አባረዋል። የስለላ አካላቱ ኝ አልተያዙም። 

ምንጭ፦አልሱዳን የዜና ወኪል

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.1K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 10:18:10 አጫጭር መረጃዎች በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ

የሱዳን የባህር ሃይል ጦር አዛዥ የነበሩት ፋት አል ራህማን ሙህይዲን ለአልጀዚራ እንደተናገሩት “ካርቱም በሙሉ” በጦር ኃይሉ ቁጥጥር ስር መግባቷን ገልፀዋል። "ለሱዳን ህዝብ እንደማረጋግጠው ከሁለት ግዛቶች በስተቀር ሁሉም ግዛቶች በጦር ኃይሉ ቁጥጥር ስር ናቸው" ሲሉ አክለዋል።

ከ20,000 በላይ የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች ለሠራዊቱ እጃቸውን መስጠታቸው የሱዳን የባህር ሃይል ጦር አዛዥ የነበሩት ፋት አል ራህማን ሙህይዲን  ተናግረዋል።አንዳንዶች ግን እስከ ሞት ድረስ መታገል ይፈልጋሉ” ሲል ሙህይዲን አክለዋል። አስተያየታቸውን ግን በገለልተኛነት አካል ማረጋገጥ አልተቻለም።

በካርቱም የፖለቲካ ተንታኝ አሽራፍ አብደል አዚዝ የግጭቱ ምንጮች በጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን እና በአርኤስኤፍ መሪ ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን “ሄሜቲ” ዳጋሎ መካከል “ግላዊ” ፀብ ናቸው ብለዋል። "ነገር ግን መጥፎው የሰብአዊ ሁኔታ ግጭቱን እንዲያቆሙ በሁለቱም ወገኖች ላይ ጫና ያሳድራል" ሲሉ ከካርቱም ተናግረዋል።

ድንበር የለሹ የሀኪሞች ቡድን ባልደረባ ባክሪ ባሽር ለአልጀዚራ እንደተናገሩት በሱዳን ያለው የጤና ሁኔታ “ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ” መልኩ አስጊ መሆኑን ተናግረዋል። ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ባሽር እንደተናገሩት “ጦርነቱ በዚህ ፍጥነት የሚቀጥል ከሆነ በሀገሪቱ ያለውን የጤና ስርዓት ሙሉ በሙሉ እናጣለን የሚል ስጋት ተጋርጦብናል” ብለዋል።

በካርቱም ከሚገኙት 59 ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች 39ኙ ህሙማንን ማገልገል የማይችሉ መሆናቸውን የሱዳን የህክምና ኮሚቴ አስታውቋል።በመግለጫውይ አንዳንድ ሆስፒታሎች በቦምብ መመታታቸውን ገልጿል። ታካሚዎችን እና የህክምና ባለሙያዎችን ለመጠበቅ “አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት” እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

በጦር ሠራዊቱ እና በፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ቢያንስ 270 ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የሱዳንን የጤና  ሚኒስቴርን ጠቅሶ አስታውቋል። ሌሎች 2,600 ሰዎችም ቆስለዋል ሲል አክሏል።
ዳጉ_ጆርናል

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.8K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 10:18:00
ትላንት የቱርኳ ኢስታንቡል በድንገት እስከ አስር ኪሎ ሜትር በሚሸፍን ግዙፍ ጥቁር ደመና ተሸፍና ነበር ። ፀሐይ ለ5 ደቂቃ ያህል አልታየችም ። ከተማዋ እንደ ሌሊት ጨለማ ሆና ነበር።

ቪዲዮው ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ነው።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.7K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 07:06:19
ሩሲያ ከተኮሰ በኋላ አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል ማዘጋጀቷን ገለጸች

ሩሲያ ከተኮሰ በኋላ አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል ማዘጋጀቷን ገለጸች።

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 15ኛ ወሩ ላይ ሲሆን ጦርነቱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም እሚቀጥል ይመስላል።

አሜሪካ እና ሌሎች የዓለማችን ሀገራት ለዩክሬን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በመርዳት ላይ ናቸው።

ሩሲያ በበኩሏ ለዩክሬን የሚደረጉ የጦር መሳሪያ ድጋፎች ልዩነት እንደማይፈጥሩ ከዚህ በፊት አስታውቃለች።

ይህ በዚህ እንዳለ በየጊዜው አዳዲስ እና ከዚህ በፊት የተፈበረኩ የጦር መሳሪያዎችን በማዘመን ላይ ትገኛለች።

አሁን ደግሞ ቶርናዶ ኤስ የተሰኘ በየደቂቃው አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል መስራቷን ገልጻለች።

እንደ አርቲ ዘገባ ይህ የጦር መሳሪያ አንድ ጊዜ በሚያደርሰው ጥቃት ብቻ ከ12 ስታዲየም በላይ ስፋት ላይ ያለን ስፍራ ማውደም ይችላል AlAin።
ሚያዝያ 11/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.2K views04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 19:10:25 በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የክልሉ ትምህርት ቢሮ በመጭው ሚያዝያ 23 የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ማለቱን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በዕለቱ ትምህርት የሚጀምሩት፣ በክልሉ የሚገኙ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንደኾኑ ዘገባው አመልክቷል።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.7K viewsedited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 19:10:25 በአርሲ ዞን በድጋሚ ለቅርጫ ከተገዛ ሰንጋ ውስጥ 7.5 ግራም ወርቅ ተገኘ

በምስራቅ አርሲ ለትንሳኤ በዓል የገዙት በሬ ለእርድ በሚቀርበበት ሰዓት በሀሞቱ ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ መገኘቱን የጢዮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ግረማ ጣፋ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቦቹ  ኩማ ተሰማ እና ንጉሴ ዲንቃ የተባሉ ሲሆን ለበዓል ቅርጫ በ38ሺህ ብር በሬ ገዝተው  በሚያርዱበት ወቅት  በበሬው ሃሙት ውስጥ 7.5 ኪሎግራም የሚመዝን ወርቅ አግኝተዋል። ወርቁ  ሃያ አንድ ሺ አምስት መቶ ብር መሸጡ ተሰምቷል።

ከቀናት በፊትም በዚሁ አካባቢ 18.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ በበሬ ሀሞት ላይ ስለመገኘቱ እና ወርቁን 53ሺብር ስለመሸጡ ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው እንዳሁኑ ይፋ የወጣ ነገር ባይኖርም በተደጋጋሚ  በበሬዎች ሃሞት ላይ ወርቅ ስለመገኘቱም ኮማንደር ግርማ ጣፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Via: ዳጉ ጆርናል
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.6K viewsedited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 19:10:04
እኛ እየሰራን ያለነው ለኦሮሞ ጥቅም እና ክብር ነው። - ብርሃኑ ጁላ

"እኔ ወታደር ነኝ። ጄኔራል ነኝ። መለዮን ጥየ ሲብል ልብስ ለብሼ ነው የመጣሁ። ለምንድን ነው? እንደ አንድ የኦሮሞ ልጅ መሳተፍ ሥለምፈልግ ነው።

እኛ እየሰራን ያለነው ለኦሮሞ ጥቅም እና ክብር ነው። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶር አብይም የሚሰራው ለኦሮሞ ክብር እና ጥቅም ነው።

የሚቻል ከኾነ በምሥራቅ አፍሪካ በወታደራዊ አደረጃጀት፣ በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እና በፖለቲካው የታፈረች እና የተከበረች ታላቋን ኦሮምያ ሀገር ለመመሥረት ነው የምንሠራው።

ይህንን ካልቻልን ግን በኦሮሞ ፍላጎት ብቻ የምትተዳደር ኢትዮጵያን እንመሠረታለን። ኹላችሁም የኦሮሞ ልጆች አግዙን። "  

ብርሃኑ ጁላ ደብረ ዘይት ስብሰባቸው ላይ ከተናገረው የተወሰደ !

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.4K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 15:33:17 የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለው የሴቶች የጅምላ ምልመላ ያሳስበናል አሉ
የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች የሳውዲ አረቢያን ደካማ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለው የሴት ሠራተኞች የጅምላ ምልመላ ያሳስበናል ሲሉ ገለጹ፡፡

አሁንም ቢሆን በርካታ ስደተኛ ሠራተኞች በሳውዲ አረቢያ ከሠራተኛ ሕጎች የተገለሉና በዘመናዊ ባርነት ስርዓት ለጥቃት የተጋለጡ ናቸው ተብሏል፡፡

<ካፋላ> በተሰኘው ስርዓት አንድ ሠራተኛ በደል ቢደርስባት እና ከአሠሪዎቿ ብትሸሽ ፓስፖርቷን ጨምሮ የተለያዩ የሰነድ መረጃዎቿን እንድታጣ እንደሚደረግ እና ይህ ስርዓት አሁንም ለውጥ እንዳልተደረገበት ነው የተገለጸው፡፡

‹‹ሳውዲ አረቢያ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በዘፈቀደ በማሰር እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ለእንግልትና ለሞት በመዳረግ፤ ሌሎችንም በመደብደብ ከአገሯ እንዲወጡ አድርጋለች›› ሲሉ የስደተኞች መብት ተመራማሪ ናድያ ሃርድማን ለአልጀዚራ አስረድተዋል፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ ይህን ዓይነት አስከፊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ወደለባት ሳውዲ አረቢያ 500 ሺሕ ሴት ሠራተኞችን ለመላክ ማቀዷን የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎቹ ኮንነዋል፡፡

ከኢትዮጵያ የሚላኩት ሴት ሠራተኞች ከሳውዲ አረቢያ የሠራተኛ ጥበቃ ሕጎች የተገለሉ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ለሚደርስባቸው በደልም ምንም ዓይነት ሕጋዊ መፍትሔ የሌላቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራተኞችን ለተሳዳቢ አሠሪዎች አሳልፎ የሚሰጠውን የካፋላ ስርዓትን ማፍረስን ጨምሮ ሙሉ ጥበቃን ለማረጋገጥ መፍትሔ መፈለግ አለበት ያሉት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች፣ በውሸት የጥበቃና ዋስትና ከለላ ሴቶችን ወደ ስደት መገፋፋት የለበትም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በዘንድሮው በጀት ዓመት የ500 ሺሕ ሴቶችን የጉዞ ወጪ ችሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመላክ ሥልጠና በመስጠት ላይ ሲሆን፣ የመጀምሪያ ተጓዦች ባለፈው መጋቢት ወር አጋማሽ ላይ መጓዛቸው ተመላክቷል፡፡

በ266 ዶላር ወርሃዊ ክፍያ ለቤት ሠራተኝነት የሚሄዱት የኢትዮጵያ ሴቶች፣ ከ18 እስከ 40 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ የኮሌጅና የዩንቨርሲቲ ምሩቃንንም ያካተተ ነው፡፡

ሠልጣኞች ከመንግሥት በኩል እድሉ ሊያመልጣቸው የማይገባ የሕይወት ዘመን ወርቃማ እድል ነው መባላቸውን ገልጸዋል፡፡

በፈርንጆች 2020 የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስቃይና መገደል ካረጋገጠ በኋላ የአገሪቱን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚያወግዝ ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡
አዲስ ማለዳ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.5K viewsedited  12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ