Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-22 17:45:09
ወደ ትግራይ ክልል ትራንስፖርት ተጀመረ
ሰላም ባስ ወደ አዲስ አበባ ሲሰጠው የነበረው የትራንስፓርት አገልግሎት ጀመረ
ከሁለት ዓመታት በኋላ የሰላም ባስ የመንገድ ትራንስፖርት በዛሬው ዕለት 51 ተጓዞችን በመያዝ ወደ አዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
አገልግሎት መጀመሩን ተከትሎ ትኬት ሲቆርጡ ያገኘናቸው ደንበኞችም ወደ አዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት በመጀመሩ ደስተኞች መሆናቸውን በመግለፅ ወደ ሌሎች አጎራባች ክልልሎችም ተመሳሳይ አገልግሎት ቢጀመር ሰላሙን ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልፀዋል(ናይል)።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.2K viewsedited  14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 16:00:21 "የውጭ አገራት ዜጎች ከካርቱም ሊወጡ ነው"- የሱዳን ጦር

ሳምንት የደፈነው የሱዳን ጦርነት ተፋፍሞ ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ የውጭ አገራት ዜጎቻቸውን ከመዲናዋ ካርቱም ሊያስወጡ ነው።የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ እና የቻይና ዲፕሎማቶች እና ዜጎች ከሱዳን ሊወጡ መሆኑንም የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን የውጭ አገር ዜጎቹ “በሚቀጥሉት ሰአታት ውስጥ” የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ለማስተባበር ተስማምተዋል ።

ሳዑዲ አረቢያም በሱዳን ያሉ ዜጎቿን “ከወንድም” ሱዳን አገር ልታስወጣ በዝግጅ ላይ መሆኗን አስታውቃለች።የሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማቶች ሱዳንን ለቀው መውጣታቸውን የሱዳን ጦር አስታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ዜጎቹን ከካርቱም ለማስወጣት እቅድ መንደፉን አስታውቋል።አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉ የህብረቱን አባል አገራት ዜጎችም ለማስወጣት የተለያዩ አማራጮችን እያጤኑ እንደሚገኙም ነው።በካርቱም ወደ 1 ሺህ 500 የሚጠጉ የህብረቱ አባል አገራት ዜጎች ይገኛሉ።ሰባት የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት በሱዳን ተልዕኮ አላቸው።የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ባየርቦኮክ ዜጎችን ለማስወጣት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረስ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ግጭቱ ከተከሰተበት ሚያዝያ 7፣ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የካርቱም አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተዘጋ ይገኛል።

አሜሪካ የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች ካርቱምን ለቀው እንዲወጡ ለማድረግ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰች ገልጻለች።ባለስልጣናቱ ከኤምባሲው ሰራተኞች ውጭ ያሉ ሌሎች የአሜሪካ ዜጎች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በራሳቸው እንዲዘጋጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።ባለስልጣናቱ ይህንን ይበሉ እንጂ አሜሪካ ዜጎቿን ለማስወጣት በዝግጅት ላይ መሆኑን ዘገባዎች አሳይተዋል።የአሜሪካ ጦር የኤምባሲውን ሰራተኞች ከካርቱም ለማስወጣት እየተዘጋጀ መሆኑንም ተዘግቧል።የአሜሪካ ወታደሮች በጂቡቲ ወደሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ እየተወሰዱ እንደሆነም የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

አርብ እለት የአሜሪካ የጦር ሰራዊት ጀነራል ማርክ ሚሌይ ከጦር አዛዡ ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር በሱዳን ስላሉት አሜሪካውያን ደህንነት ተወያይተዋል።ፔንታጎን በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

[BBC]
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.5K viewsedited  13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 15:01:48
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የነዳጅ ማደያ ድርጅቶች በሙሉ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ተጠቃሚ ለሆኑ አካላት በሙሉ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚካሄድ ያሳወቀዉ ንግድ ቢሮዉ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም የተከለከለ መሆኑን አሳዉቋል፡፡

ከኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ውጪ በተለይ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈፀም የተከለከለ በመሆኑ ቢሮው በዕለቱ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል ነዉ ያለዉ፡፡ይህ በመሆኑም ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለማንኛውም የነዳጅ ተጠቃሚ አካላት የነዳጅ ሽያጭን በኤክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንዲያስተናግዱ አሳስቧል፡፡

https://t.me/+zsQENK1iuHYzMDFk
https://t.me/+zsQENK1iuHYzMDFk
2.5K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 13:27:23
ስምንተኛ ቀኑን በያዘው በዛሬው ቀን የRSF ወታደሮች በአልሁዳን እስርቤት ላይ ጥቃት በማድረስ እስረኞችን አስፈትተዋል ሲሉ የSAF ( Sudanese Armed Forces) ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.8K viewsedited  10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 10:50:00
አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በሱዳን የተፈጠረውን ችግር የኢትዮጵያ ጣልቃገብነት እንዳለ አስመስለው የሚያናፈሱት መረጃ መሰረተ ቢስ ነው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በሱዳን ግጭት የኢትዮጵያ ጣልቃገብነት እንዳለ አስመስለው የሚያናፈሱት መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም÷ ኢትዮጵያና ሱዳን በመንግስታት መለዋወጥ ያልዋዥቀ ጽኑ ወዳጅ ጎረቤት ሀገራት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሱዳን ካጋጠማት ወቅታዊ ፈተና እንድትወጣ ኢትዮጵያ በየትኛውም ሁኔታ ከሱዳናዊያን ጎን መሆኗንም አረጋግጠዋል።

ያም ሆኖ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በግጭቱ የኢትዮጵያ ጣልቃገብነት እንዳለ አስመስለው የሚያናፈሱት መረጃ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት የማይመጥንመሰረተ ቢስና ሀሰተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ይህን ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በሱዳን የተፈጠረውን ችግር አካባቢያዊ ከማድረግ የመነጨ ፍላጎት መሆኑን ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ መሪዎች ከቀዳማዊ አጼ ኅይለሥላሴ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ ሱዳን ያጋጠሟትን ቸግርች በሰላም እንዲፈቱ ጉልህ ሚና መጫወታቸውን አስታውሰዋል።

 @ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.9K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 10:45:57
በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የተቀሰቀሰው ጦርነት በርካታ ንብረት እና ህይወት እየቀጠፈ ነው። ጦርነቱ ዛሬም እንደቀጠለ ሲሆን በርካታ ዜጎች ካርቱምን ለቀው ወደ አጎራባች ከተሞች እየሸሹ ነው።
አሜሪካ፣እንግሊዝ እና ህንድ ዜጎቻቸውን ከሱዳን የሚያወስወጡበትን መንገድ እያመቻቹ ነው።
#sudan_news
ሚያዝያ 14/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.7K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 17:41:50
በካሮቱም የሁለቱም ተዋጊ ሀይሎች የዒድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ስምምነት ያደረጉ ቢሆንም ጦርነቱ በካርቱም እንደቀጠለ ነው።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
683 viewsedited  14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:40:31 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠየቀ
የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታችሁ ወጥታችሁ ላመለጣችሁ የከተማችንና አካባቢው ሙስሊሞች በሙሉ!!
ዛሬ በነበረው የኢድ ሰላት ፕሮግራም ላይ ለመታደም ጥሪያችንን አክብራችሁ በአንድነት  አምራችሁና ደምቃችሁ ግዙፉ የከተማችን ውበት ሆናችሁ በመዋላችሁ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በድጋሚ እንኳን ለ1444 ዓ.ሂ  የኢድ አልፊጥር በዓል  በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዛሬው እለት የተሰገደው የኢድ ሰላት በሰላም፣በደስታ መጠናቀቁ ቢያስደስትም የዒድ ሰላት ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት ከነበረው ሰአት ቀድሞ በመሰገዱ የዒድ ሰላት ላመለጣችሁ የከተማችን ሙስሊሞች ይቅርታ እንጠይቃለን።

በትናንትናው እለት ከፌደራል መጅሊስ ጋር በጋራ በሰጠነው መግለጫ ሸሪአውን በጠበቀ መልኩ በእለቱ ንግግሮች እንደማይኖሩና በማለዳ ሰግደን እንደምንበተን ለህዝባችን ገልፀን ቢሆንም በእለቱ የተገኙት ሚድያዎች በአብዛኛው በሚባል መልኩ ትኩረት ሰጥተው ባለማስተላለፈቸው እና ከሚዲያዎቹ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በሰፊው  ባለመጠቀማችን ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ተረድተናል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት የነበረውን ሂደትን ለማሻሻል በሚል መልካም እሳቤ በተፈጠረ ክፍተት ሰላት ላመለጣችሁ ሁሉ ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ የሚስተካከል መሆኑን ህዝባችን እንዲገነዘብ እያልን፣
በበጎና ገንቢ በሆነ መልኩ አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የከተማችን ነዋሪዎች ምስጋና እያቀረብን በዓሉ የሰላም የደስታ፣የመተዛዘን፣የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን።
@ET_SEBER_ZENA
1.2K viewsedited  13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:10:38 ሰበር ዜና ET pinned «በታላቅ ቅናሺ ምንምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች ➠ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ ➠ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ ➠ የ ድርጅት ማስታወቂያ ➠ የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ ➠ የ ቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ ➠ ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች ማስታወቂያ የትምህርት ተቋማት…... የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…... የትራንስፖርት አገልግሎት….... የስራ አገናኝ…»
10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:07:29 በጉጂ ዞን የጸጥታ ችግር ያባባሰው ኮሌራ የሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ መሆኑ ተገለጸ
በጉጂ ዞን ዋደራ ወረዳ በተከሠተው የኮሌራ በሽታ፣ ሰዎች እየሞቱ መኾናቸውን፣ ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዋደራ ወረዳ የጤና ባለሞያ፣ በወረዳዋ ከተማ ሳይቀር፣ በበሽታው የተጠቁ በርካታ ሰዎች ሕይወት እያለፈ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

በአካባቢው ያለው የጸጥታ እና የመጓጓዣ ችግር፣ ኮሌራ በወረርሽኝ ደረጃ እንዲባባስ መንሥኤ መሆኑን የጤና ባለሞያው አስረድተዋል።

የዋደራ ጤና ጽ/ቤት በበኩሉ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገር፣ ኮሌራ በወረዳው በ41 ቀናት ውስጥ ብቻ፣ 10 ሰዎችን ለኅልፈት አብቅቷል፡፡

በአንጻሩ፣ በባሌ ዞኖች ተከሥቶ የነበረው የበሽታው ወረርሽኝ፣ በአሁኑ ወቅት መቀነሱን፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.1K viewsedited  10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ