Get Mystery Box with random crypto!

'የውጭ አገራት ዜጎች ከካርቱም ሊወጡ ነው'- የሱዳን ጦር ሳምንት የደፈነው የሱዳን ጦርነት ተፋፍ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

"የውጭ አገራት ዜጎች ከካርቱም ሊወጡ ነው"- የሱዳን ጦር

ሳምንት የደፈነው የሱዳን ጦርነት ተፋፍሞ ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ የውጭ አገራት ዜጎቻቸውን ከመዲናዋ ካርቱም ሊያስወጡ ነው።የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ እና የቻይና ዲፕሎማቶች እና ዜጎች ከሱዳን ሊወጡ መሆኑንም የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን የውጭ አገር ዜጎቹ “በሚቀጥሉት ሰአታት ውስጥ” የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ለማስተባበር ተስማምተዋል ።

ሳዑዲ አረቢያም በሱዳን ያሉ ዜጎቿን “ከወንድም” ሱዳን አገር ልታስወጣ በዝግጅ ላይ መሆኗን አስታውቃለች።የሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማቶች ሱዳንን ለቀው መውጣታቸውን የሱዳን ጦር አስታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ዜጎቹን ከካርቱም ለማስወጣት እቅድ መንደፉን አስታውቋል።አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉ የህብረቱን አባል አገራት ዜጎችም ለማስወጣት የተለያዩ አማራጮችን እያጤኑ እንደሚገኙም ነው።በካርቱም ወደ 1 ሺህ 500 የሚጠጉ የህብረቱ አባል አገራት ዜጎች ይገኛሉ።ሰባት የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት በሱዳን ተልዕኮ አላቸው።የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ባየርቦኮክ ዜጎችን ለማስወጣት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረስ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ግጭቱ ከተከሰተበት ሚያዝያ 7፣ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የካርቱም አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተዘጋ ይገኛል።

አሜሪካ የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች ካርቱምን ለቀው እንዲወጡ ለማድረግ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰች ገልጻለች።ባለስልጣናቱ ከኤምባሲው ሰራተኞች ውጭ ያሉ ሌሎች የአሜሪካ ዜጎች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በራሳቸው እንዲዘጋጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።ባለስልጣናቱ ይህንን ይበሉ እንጂ አሜሪካ ዜጎቿን ለማስወጣት በዝግጅት ላይ መሆኑን ዘገባዎች አሳይተዋል።የአሜሪካ ጦር የኤምባሲውን ሰራተኞች ከካርቱም ለማስወጣት እየተዘጋጀ መሆኑንም ተዘግቧል።የአሜሪካ ወታደሮች በጂቡቲ ወደሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ እየተወሰዱ እንደሆነም የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

አርብ እለት የአሜሪካ የጦር ሰራዊት ጀነራል ማርክ ሚሌይ ከጦር አዛዡ ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር በሱዳን ስላሉት አሜሪካውያን ደህንነት ተወያይተዋል።ፔንታጎን በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

[BBC]
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA