Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-21 20:59:30 መንግስት ከእምነት ተቆማት ጋር ያለዉ አቋም በጣም የሚያስገርም ነው መንግስት ሆይ ለሹመት ለክብር ያበቃህ ፈጣሪ ጋር ምን ፈልገህ ነው??? ምንም ደግ መሪ ይሁን አይሁን ያለፈጣሪ ፍቃድ ለዚህ እንዳልበቃ ሁላችንም እናዉቃለን ግን ለመንግስት አንድ መልክት አለኝ መንግሥት ሆይ በዚህ የጫካ ፕሮጀክት በዚህ ሁለት ቤተመንግሥት በዚህ በእጁ አዙር ንፁሃንን መጨፍጨፍ ማፍናቀል ሌሎችም ስራዎች በዝተዉብህ ከሆነ ያላስተዋልከዉ እኔ ላስታዉስህ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን እና የኢትዮጵያን እስልምና ተቋማት ላይ የምትሰራውን የዉስጥ ሴራ አያዋጣህም ያከበረ የሾመ ፈጣሪ ማዋረዱንም ማዉረዱንም ያዉቅበታል እና አስታዉል።

በዳኒ የተፃፈ
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.1K viewsedited  17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 20:46:27
ለመረጃ ያህል
የብሮድካስቲንግ ህጉ እና ተፈፃሚነቱ እንደሚከተለው ነው።
በብሮድካስት አዋጁ መሰረት ህግ ለጣሱ ሚዲያዎች የመጀመሪያው እርምጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡
በመቀጠልም ሚድያው አስተያየቱን በጽሁፍ እንዲሰጥ ይጠየቃል፡፡ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያው ተሰጥቶት ማስተካከያ ካላደረገ ከስርጭት ይታገዳል፡፡
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.2K views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 20:46:15 የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ በ " ቴሌ ብር " መክፈል ሊጀመር ነው
ገንዘብ ሚኒስቴር ፤ በባንኮች በኩል ተከፋይ የሚሆነውን የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ወደ " ቴሌ ብር " የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ለማሸጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕ/ተ/ም/ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህ ይፋ የሆነው።

አቶ አህመድ ሽዴ ምንድነው ያሉት ?

" አሁን በባንኮች የክፍያ ሥርዓት በጥቅል (በበልክ) እየተከፈለ ያለውን ሒደት በቀጣይ ወደ ቴሌ ብር ለማሸጋገር ሥራዎች እየተሠሩ ነው። "

ይህ በተመለከተ ' ኢትዮ ቴሌኮም ' ምን አለ ?

ቺፍ ኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ፦

" በመንግሥት የተያዙት ጉዳዮች ወቅቱን ጠብቀው ቢገለጹ ይሻላል።

ነገር ግን ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን ለማቅረብ የሚያስችል በቂ ዝግጅትና አቅም አለው።

ተቋሙ በሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎቱ እስካሁን ከ32 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን አገልግሎት እየሰጠ እንደገሚገኘው መጠን የተዘረጋው ሲስተም አገልግሎቱን በቀላሉ ለመስጠት ያስችለዋል።

የትኛውም ውሳኔ ከሚመለከተው አካል ከመጣ መሥራት ይቻል።

ደመወዝ በቴሌ ብር መከፈሉ የተቋማትን ቅልጥፍና ለመጨመር አስተዋጽኦ ያድረጋል።

በዕረፍትና በበዓላት ወቅት የሚውል የደመወዝ ክፍያ ቀንና ተዛማጅ ጉዳዮች ለደመወዝ ከፋዩም ሆነ ተከፋዩ በሚያመች ለመክፈል ያስችላል።

እስካሁን ባለው አገልግሎቱ እንደ ደመወዝ ዓይነት የጅምላ (በበልክ) ክፍያ በሚከፈልበት ወቅት ሠራተኞች የደመወዛቸውን እስከ 35 በመቶ ያለምንም ዋስትና መበደር ይችላሉ። በቀጣይ ሌሎች ተጨማሪ አማራጮችም ይቀርባሉ።
እስካሁን ድረስ ግን ከሚመለከተው አካል የመጣ አቅጣጫ የለም። " ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊ ደመወዥ በ " ቴሌ ብር " ለማድረግ ስለታሰበው እቅድ በተመለከተ " እንዲህ መባሉን መረጃ የለኝም " ብለዋል።

በባንኩ በኩል የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ የሚከፍል መሆኑን የገለፁት እኚሁ ኃላፊ ለዚህ አገልግሎቱ ምንም ዓይነት ክፍያ የማይጠይቅበት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በቴሌ ብር በኩል ደመወዝ ይከፈል ከተባለ ግን አሁንም ኢትዮ ቴሌኮም የሚጠቀመው ከባንኮች ጋር በመተሳሰር መሆኑ አይቀርም ብለዋል፡፡

አጫጭር መረጃ ፦

እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ፦

- የመንግሥት ኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ድርሻን ለማሳደግና እስካሁን የ159 ባለ በጀት መ/ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ዘዴ እንዲተገብሩ ተደርገዋል።

- በተያዘው ዓመት የዘጠኝ ወራት 79.2 ቢሊዮን ብር ክፍያ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ተከፍሏል።

- ኢትዮ ቴሌኮም የመንግሥት የኤክትሮኒክስ ክፍያ ድርሻ ለመወጣት እንዲያስችለው የሪፎርም ሥራዎችን እየሠራ ነው የታክስ ክፍያ አሰባሰብም ሥርዓቱ በቴሌ ብር እንዲከፈል የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቷል።

እንደ ኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ፦

- የቴሌ ብር የሞባይል ገንዘብ ዝውውርን ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ እስከ የግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ 32.2 ሚሊዮን ደንበኞች አፍርቷል።

- እስካሁን ከ375.2 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ግብይቶች (ትራንዛክሽንስ) ተፈፅሟል።

- የነዳጅ ክፍያ በአስገዳጅነት በዲጂታል እንዲፈጸም ከተደረገበት ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ 2.7 ቢሊዮን ብር ግብይት ተፈፅሟል።
ሪፖርተር ጋዜጣ
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.0K views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 19:59:19
ሰሞኑን አዲስ በተመሰረተው ሸገር ከተማ የፈረሱ የመስጅዶች ቁጥር ከ8 በላይ ደርሷል።
በመስጅዱ ውስጥ ቅዱስ ቁርዓንን ጨምሮ ሌሎች የእምነት መዛግብቶች ለማውጣት እንኳን እድል አለመሰጠቱ ትንሽ አሳሳቢ ነው።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.0K views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 19:59:10
ዛሬ ፒያሳ በዕድሳት ላይ የነበረ ቤት ተደርምሶ በሰዉ ላይ ጉዳት ደረሰ
ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ 4 ሰዓት በእድሳት ላይ የነበረ ቤት ተደርምሶ በሰዉ ላይ ጉዳት ደርሷል። በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ ደሀብ ሆቴል አጠገብ በእድሳት ላይ የነበረዉ አንድ ካፌ ተደርምሶ በዚያዉ ስፍራ በመንገድ ላይ ሻይ ከሚሸጡት መካከል 5 ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷባቸዋል።
ጉዳት ከደረሰባቸዉ ተጎጂዎች ዉስጥ ሶስቱ በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አንቡላንስ ወደ ጤና ጣቢያ ተወስደዋል ። የእድሳትና የግንባታ ስራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ መሰል አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊዉን የደህንነት መስፈርቶችን አሟልቶና ጠብቆ መስራት አስፈላጊና ግዴታም ጭምር ያለበት በመሆኑ ልዩ ትኩረትም እንዲሰጠዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.0K views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 19:24:46
የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዛሬ በሰበር ዜና ያሰረጨው መግለጫ ግጭት ቀስቃሽ ነው በማለት ሚዲያው ስርጭት እንዲያቆም የኢትዮጵያ ብዙሃን መገናኛ ባለስልጣን በደብዳቤ አሳውቋል።
ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.0K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 19:24:36 በፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተፈፃሚነት የሚቆጣጠርና የሚያረጋግጠው ልኡክ ወይንም (ኤዩ ኤም ቪሲኤም) ለሁለት ቀናት በመቀሌ ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫው የትግራይን መከላከያ ሀይል ወይንም ቲዲኤፍ ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ወሳኝ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ግጭት አስተዳደር ዳይሬክተር አልሀጂ ሳርጆህ ባህ እንደተናገሩት ሁሉም አካላት በበጎ ፈቃደኛነት በመሳተፋቸውና ሰላም ወዳዱ ህዝብ በመተባበሩ የተነሳ ጥሩ ውጤት ሊገኝ ተችሏል፡፡

እስከ ሰማኒያ አምስት ፐርሰንት የሚሆነውን ከባድ መሳሪያ ትጥቅ ለማስፈታት መቻሉንም አስረድተዋል፡፡ ቀጣዩ እርምጃ የሚሆነው ቀላል መሳሪያዎችን ማስፈታት፣ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማምከንና የቀድሞ ታጣቂዎችን ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የልኡካን ቡድኑ ሀላፊ ሜጀር ጄኔራል ስቴፈን ራዲና በመቀሌ ፕላኔት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹በመቀሌ ከባድ መሳሪያዎና የአየር መቃወሚያዎች ትጥቅ ሲፈታ ለመመልከት ችለናል፡፡›› ያሉ ሲሆን የሞርታርና ፀረ ታንክ መሳሪያዎች መፍታቱ ሂደት በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚጠናቀው ገልፀዋል፡፡ በሚቀጥለው ወር ወደሁመራ የመሄድ እቅድ እንዳላቸው ያስታወቁት ሜጀር ጄኔራሉ አክሱምና ሽሬን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የጦርነት ቅሪቶችን የማፅዳት ስራ እንደሚቀርም አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህ ልኡክ እንደልቡ በትግራይ ክልል እንዳይንቀሳቀስ የኤርትራ ወታደሮች እንቅፋት እንደፈጠሩበት ገልጿል፡፡ የኤርትራ ወታደሮች የተቆጣጠሩት የትግራይ ክፍል እንዳለ የጠቆመው ጌታቸው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለቆ እንዲወጣ ግፊት እንዲያደርግም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.1K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 16:13:03 ድሬዳዋ
በድሬዳዋ የተስተዋለውን ከፍተኛ የሙቀት ተከትሎ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፈ
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን መስተዋሉን አስመልክቶ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ለነዋሪዎች የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፏል።

ቢሮው በተለይም አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው(ከፍተኛ ደም ግፊት፣የስኳር ህመም፣የልብ ህመም፣የኩላሊት ህመምና ሌሎችም)፣እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአይምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ ከታች የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

1. ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ፤

2. እቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ፤

3. በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪ/በረንዳዎ ላይ መቆየት፤

4. ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽ/ውሃ/ መውሰድ፤

5. አመጋገብዎን ማስተካከል(ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ)፤

6. ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት፤

7. የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም/መቀነስ፤

8. ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉ/አየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው፤

9.የተለያየ ህመም  ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ማድረግ፣ የታዘዘውን መድኃኒት በትዕዛዙ መሰረት በመውሰድ ጤናዎን እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 16:12:52
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የአስክሬን ሽኝት ተደረገ
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የአስክሬን ሽኝት መደረጉን የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።
ከዩኒቨርሲቲ በተገኘው መረጃ ራቅ ካሉ አካባቢዎች መጥተው በተቋሙ ሲያስተምሩ ለነበሩና በትላንትናው በአሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ላለፈ መምህራን የአስክሬን ሽኝት አድርጓል።

ትናንትና የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር እስካሁን 19 መድረሱ ታውቋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.4K views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 16:12:52
በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ንፋስ ሥልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ።
የትራፊክ አደጋው የደረሰው በወረዳ 11 ልዩ ሥሙ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ሕይወታቸውን ካጡት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና በህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.3K views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ