Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-21 11:46:27 "በከፍተኛ ትዕግስት ስናልፋቸው የነበሩ አባቶች ዛሬም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ቤተክርስቲያንን ሲገፉ በዝምታ የምናይበት ሂደት አይኖርም፡፡"
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግርን ለመቅረፍ  በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው ዐብይ ኮሚቴ በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደት ላይ መግለጫ አወጣ።

በአለፉት ሁለት ሦስት ቀናት በአባቶች ዘንድ ውይይት ተደርጎበት ስምምነት ላይ ሳይደረስበት የቀረው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደትን አስመልክቶ በተደረገው  ውይይት ላይ በአባቶች የተፈጠረው  የሐሳብ መከፋፈልና አለመግባባት ሁኔታ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ለኮሚቴው በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል ሲል ከ10 በላይ ማኅበራትን የወከለው ኮሚቴው በመግለጫው ጠቅሷል።

በየጊዜው በሚነሱ ወሳኝ የቅድስት ቤተክርስቲያን አጀንዳዎች ውስጥ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ጀርባቸውን የሚሰጡ፣ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ዓለማዊ አጀንዳ የሚያራምዱና ከዛሬ ነገ የቤተክርስቲያንን ፍቅርና ምህረት ተረድተው ወደልባቸው ይመለሳሉ በማለት በከፍተኛ ትዕግስት ስናልፋቸው የነበሩ አባቶች ዛሬም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ቤተክርስቲያንን ሲገፉ በዝምታ የምናይበት ሂደት አይኖርም ያለው ኮሚቴው በዚህ ታሪካዊ ወቅት ለቅድስት ቤተክርስቲያን መቆም ሲገባችሁ እየሰማችሁ እንዳልሰማችሁ ሆናችሁ በዝምታ የምትመለከቱ አባቶችም ሆነ ዋነኛ የችግሩ አካላት የሆናችሁ አባቶች በእግዚአብሔርም በታሪክም በእኛም በልጆቻችሁ የሚያስጠይቃችሁ መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን ሲል አፅንዖት ሰጥቷል።

ቤተክርስቲያን ከማይጠፋ ዘር በክርስቶስ ደም የተመሠረተች እንጂ እንደ ፖለቲካ ምክር ቤት በዘር በጎሣ የተመሠረተች አይደለችም። ቤተክርስቲያን የሁሉም ለሁሉም ነች ያለው ዐብይ ኮሚቴው ዛሬ በወከባና በጫና ለተለየ ብሔርና ጎሣ ተለይቶ የኢጲስ ቆጶስ ሲመት ቢሰጥ ነገ በዚህ ሰበብ ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈል ዘርና ቋንቋን መሠረት አድርጎ የሚከተለውን ጥያቄና በጥንታዊት  ሐዋርያዊት ዓለም አቀፋዊት አንዲት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተነጣጠረውን የፈተና እና የመከራ ማእበል መመለስም መዳኘትም ይከብዳል ብሏል።

ይህን ጽንፍ የወጣ አጀንዳ በድምጽ ብልጫ በማስወሰን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖናን በመጣስ መፍትሔ የሚያመጡ መስሎአቸው የሚተጉ አባቶችም ቤተክርስቲያንን ወደማትወጣው መከራና ፈተና እየገፏት እንደሆነ ሊረዱት ይገባል ብለን እናምናለን።

በዚህ መግለጫ ብፀዓን አባቶችንን በታላቅ ትህትና ዐቢይ ኮሚቴው ማሳሰብ የሚፈልገው ይህ አጀንዳ አስተዳደራዊ ሳይሆን ሃይማኖታዊ/ዶግማዊ እና ሥርዓታዊ/ቀኖናዊ አጀንዳ በመሆኑ በሕገ ቅድስት ቤተክርስቲያን አንቀፅ 19፡ 5፡ ሐ መሰረት በሙሉ ድምጽ እንጂ በድምፅ ብልጫ ስምምነት ተደርጎበት ውሳኔ ላይ ሊደረስ የማይገባው አጀንዳ መሆኑንም ኮሚቴው በሚገባ ያምናል፡፡

በተለይም ይህ አለመግባባት እየሰፋ መጥቶ ውሳኔው በድምጽ ብልጫ የሚደረግ ከሆነ ሕገ ቤተክርስቲያንን እና ቀኖና ጥሰትን ስለሚያመጣ፤ ውጤቱም በብፁዓን አባቶች መካከል ያለውን መከፋፈል አስፍቶ ቤተክርስቲያንን ወደ ከባድ ፈተና የሚያደርስ ጉዳይ በመሆኑ ብፁዓን አባቶች በፍፁም መከባበር፤ ምድራዊ እና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ፍጹም ጸያፍ እና የተወገዙ በሆኑ ጉዳዮች፣ዘርን፣ ቋንቋን፣ ጎጥን ፖለቲካን፣የግል ጥቅምንና ፍላጎትን ሳይሆን የረቂቃኑ እና ግዙፋኑ፤ የሰማያውያን እና የምድራውያን ልዩ ጉባኤ፤አንዲት የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማዕከል በማድረግ ብቻ አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ሆናችሁ በእርጋታ በመነጋገር ለቅድስት ቤተክርስቲያን የሚጠቅም ውሳኔ በአንድ ድምፅ ሰጥታችሁ እንደምትወጡና የአሁኑንም ሆነ የሚመጣውንም ትውልድ የመከራ ቀንበር እንደምታቀሉ ባለሙሉ ተስፋ ነን፡፡

መግለጫው ከቅዱስ ሲኖዶስ የምንጠብሸው ውጤት በማለት ዐራት ነጥቦችን ዘርዝሯል።

0ቢይ ኮሚቴው በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከተከናወነው  ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ጋር በተያያዘ በቤተ ክርስቲያን ላይ የተጋረጠው አደጋ መነሻ አድርጎ የተቋቋመ ሲሆን ከ10 በላይ ማኅበራትን ማለትም ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፣ ከነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የምዕመናን ኅብረት፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ ጴጥሮሳውያን ኀብረት፣ የጎልማሶች እና ወጣቶች ማኅበር፣ ከወልዳ ዳንዲ አቦቲ፣ ከደጆችሽ አይዘጉ ማኅበር፣ ከሕግ ባለሙያዎች እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያዎች የተወጣጣ ነው።
ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.8K viewsedited  08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 11:46:26
2.5K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 11:09:46
ባሻዬ! መንግሥታችን ከአንድም ሁለት ቤተመንግሥት ለመሥራት ሥራ መጀመሩን ዘግይቶም ቢሆን ሰማሁ። ሃሳቡ ግሩምና ድንቅ ነው።

እኛ በሞቀ ቤት እየኖርን ምስኪኑ መንግሥታችን ምንም ቤት ሳይኖረው እስከዛሬ ማስተዳደሩ የሚያስመሰግነው ነው።

ባሻዬ! አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ፣

ራስ መስፍን ስለሺ የወደፊት መቃብራቸውን ደብረ ሊባኖስ በተክለ ኃይማኖት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ አስገነቡ።

አንድ ቀን ጃንሆይ ቤተክርስቲያኗን ሊሳለሙ ሲመጡ ራስ መስፍን አገኟቸውና እንዲህ አሏቸው "ጃንሆይ! የወደፊት የዘላለም ማረፊያ ቤቴን እዩልኝ"

ጃንሆይ የራስ መስፍንን የወደፊት መኖሪያ አዩና "ወደፊት ስትሞት እዚች ቤተክርስቲያን ውስጥ ለመቀብርህ እንዴት እርግጠኛ ሆንክ?" ብለው መለሱላቸው።

ዕውነትም ራስ መስፍን ስለሺ በደርግ ጥይት ተገድለው የትም ተጥለው ቀሩ።

ባሻዬ! የጻፍኩልህን ታሪክና ይሄንን ፎቶ እንዳታገናኝብኝ አደራ! ለራሴ ጤንነት እየተሰማኝ አይደለም።
Via Tesefay Hailemariam

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 17:27:37
142 ግብር ከፋዮች ያሳተሟቸው እና ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተለያዩ ደረሰኞች ለታክስ ዓላማ የማያገለግሉ ናቸው፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
የገቢዎች ሚኒስቴር በስም የዘረዘራቸው 142 ግብር ከፋዮች ያሳተሟቸው እና ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተለያዩ ደረሰኞች ለታክስ ዓላማ የማያገለግሉ መሆናቸውን አስታወቀ።

በስም የተዘረዘሩት ግብር ከፋዮች ለሦስት እና ከሦስት ዓመት በላይ ግብር ያላሳወቁ መሆናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ያሳተሟቸው ደረሰኞችም በተለያየ የታክስ አካውንቶች እዳ ያለባቸው ናቸው ብሏል።

እነዚህ ደረሰኞችን በማናቸውም የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ አገልግሎት ላይ ውለው የተገኙ ከሆነ ሕጋዊነት እንደሌላቸው ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው።

በመሆኑም ግብር ከፋዮች ይህንኑ በመገንዘብ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የገቢዎች ሚኒስቴር አሳስቧል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.0K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:23:35 የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ ጭማሪ ነዋሪዎችን እያማረረ ነው
በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ የግል ት/ቤቶች ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአብዛኛው  ከ50 እስከ 100 ፐርሰንት የሚደርስ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ እንደሚያደርጉ ለወላጆች ማሳወቃቸው ከፍተኛ አለመግባባትና ቅሬታን ፈጥሯል። በአንዳንድ ት/ቤቶች ስብሰባው ባለመግባባት ተበትኗል።

በት/ቤቶቹ በኩል ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የዋጋ ጭማሪ በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በመከልከላቸው ለመምህራን ደመወዝ ለመጨመር፣ ከዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ ለተከሰተው የአስተዳደራዊ ወጪ ንረት ለመሸፈን መቸገራቸውን በመግለፅ ጭማሪ የማድረጋቸውን ትክክለኝነት ያስረዳሉ።
በወላጆች በኩል እየተጠየቀ ያለው ጭማሪ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን፣ የዋጋ ግሽበቱ ስለባ የሆኑት ወላጆችም ጭምር መሆናቸውን በመጥቀስ የተጋነነ ጭማሪውን እንደማይቀበሉት መናገራቸው ተሰምቷል። በአንዳንድ ት/ቤቶች ወላጆች ከ30 በመቶ በላይ ጭማሪ መጠየቅ እንደሌለባቸው ፍላጎታቸውን ገልፀዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.1K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:21:28 አጣዬ
" ከማረሚያ ቤቱ ካመለጡ ታራሚዎች የተወሰኑት በፍቃዳቸው ተመልሰዋል
አጣየ ማረሚያ ቤት በድጋሚ ወደ ስራ መግባቱንና ታራሚዎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የአጣየ ማረሚያ ቤት ጥበቃ መረጃ እና ደህንነት ቡድን መሪ የሆኑት ዋና ኢንስቴክተር ቁምላቸው ጌጤ ተናግረዋል ፡፡በአጣየ ማረሚያ ቤት በከተማው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተነሳ ማረሚያ ቤቱ በእሳት ተቃጥሎ እና ታራሚዎች ወደ መሃል ሜዳ ተዘዋውረው እንዲሁም የተወሰኑት አምልጠው የነበረ መሆኑ ተጠቁሟል ።

አያይዘውም በመሀል ሜዳ አንድ መቶ አስራ ስምንት ታራሚዎች ወደ ማረሚያ ቤቱ የተመለሱ ሲሆኑ ከነዚህም ዉስጥ አብዛኛዎች አምልጠው የነበሩ እና በፍቃዳቸው የተመለሱት እንደሚገኙበትም ተገለጿል።

በአጣየ ከተማ በአሁን ወቅት አንጻራዊ ሰላም ቢኖርም ወደ ቀደሞ የከተማዉ የንግድ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል/ዳጉ ጆርናል)

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.9K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:21:19 " ክስ ከተመሰረተብኝ እመለሳለሁ! " - አቶ ልደቱ አያሌው
#Ethiopia | መንግሥት በ "ሽብር ወንጀል እጠረጥራቸዋል" ያላቸውን በውጭ ሀገር ያሉና ተላልፈው እንዲሰጡ ማዘዣ ካወጣባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው "ክስ ከተመሠረተባቸው" ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አሳውቀዋል።

አቶ ልደቱ እስካሁን ክስ እንዳልተመሠረተባቸው በጠበቃቸው እንደተነገራቸውና ክስ ከተመሠረተባቸው ግን ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመመለሱ ገልጸዋል።

ይህን የገለፁት ከቢቢሲ አማርኛ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።

ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ምን አሉ ?

"...ከጠበቃዬ ጋር እየተነጋገርኩ ነው። እስካሁን ክስ አልተመሠረተብኝም። ዝም ብሎ በራድዮና በቴሌቪዥን ይነገራል እንጂ የቀረበ ክስ የለም። ክስ ሲመሠረት ነው የምሄደው።

ክስ ከመመሥረቱ በፊት መሄዴ ጥቅም የለውም። በጊዜ ቀጠሮ መጉላላት ነው እንጂ ምንም ፋይዳ የለውም። እስከዚያ ድረስ ሕክምናዬን እከታተላለሁ /አቶ ልደቱ ለልብ ህመም በአሜሪካ የህክምና ክትትል ላይ ናቸው/ ።

ክስ ሲመሠረት ዳኞቹ የሚቀጥለው ሕክምናዬ ድረስ እንድቆይ የሚፈቅዱ ከሆነ እቆያለሁ። የማይፈቅዱ ከሆነም የሕክምና ቀጠሮዬን አቋርጬ እሄዳለሁ። "

አቶ ልደቱ ስለ ሽብር ክስ...

" የሕክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ ነው እንጂ መጀመሪያም የመጣሁት እዚህ ለመኖር አይደለም። በቅርብ ጊዜ ወደ አገሬ እመለሳለሁ ብዬ እያሰብኩ ነበር። የዘገየሁት ያልተቋጨ የሕክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ ነው። የሽብርተኛነት ክስ ሲመጣ ካሰብኩት ጊዜ ፈጥኜ ነው የምሄደው አልኩ።

የሕግ ተፈላጊነት ካለ፣በሽብርተኛነት የመጠየቅ ጉዳይ ካለ፣እኔ ከፍ/ቤት ውሳኔ እና ጥያቄ ርቄ መኖር ስለማልፈልግ ነው ለመሄድ የወሰንኩት።

...አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ተመልሼ ለመውጣት ችግር ሊገጥም ይችላል ብዬ ነው እስካሁን የዘገየሁት። አሁንም የሕክምና ቀጠሮ አለኝ። ግን የሕግ ተጠያቂነት ከመጣ ምንም ማድረግ አይቻልም።

የተከሰስኩበት ወንጀል በፍጹም ከእኔ ታሪክ እና ማንነት ጋር የማይሄድ ነው። ሥርዓቱ ደግሞ ይሄንን ያደረገበት የራሱ ምክንያት አለው። አንደኛው ምክንያት እንደዚህ ዓይነት ክስ ፈርቼ ወደ አገሬ እንዳልመለስ ለማድረግ ስለሆነ ይሄንን በፈቃደኛነት ለመቀበል ዝግጁ አይደለሁም።

እኔ ሰላማዊ ታጋይ ነኝ። ሁልጊዜም በሕግ ነው የምተማመነው። ካሁን ቀደምም አምስት ስድስቴ ታስሬ በፍርድ ቤት ነው ነጻ የሆንኩት። አሁንም በዚያ መንገድ ሄጄ የግድ ሥርዓቱን መጋፈጥ አለብኝ በሚል ነው የምመለሰው።

ማናችንም ላለመታሰር፣ ዋጋ ላለመክፈል የየራሳችን ምክንያት ይኖረናል። ትግል ሲባል ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ጥሶ መከፈል የሚገባውን ዋጋ መክፈል ነው።

ወደኢትዮጵያ ሲገቡ ስለሚገጥማቸው ችግር...

" ስሄድ የሚገጥመኝ ችግር ቀላል ነው ብዬ አይደለም። ከባድ እንደሚሆን አምናለሁ። ያ ችግር ምናልባት ሕይወቴንም ጭምር የሚያሳጣ ሊሆን ይችላል።

ግን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ፣ ሕዝቡ ያለበት ሁኔታ፣ ሰዎች በዚህ ደረጃ ዋጋ ለመክፈል ካልተዘጋጀንና ካልከፈልን ይለወጣል የሚል እምነት የለኝም። በእኔ ደረጃ ያለ ሰው ያን ዋጋ መክፈል እና ለትግሉ አርአያ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ።

ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በፖሊስ ሊያዙ ስለሚችሉበት ሁኔታ...

" ልምዱ አለኝ። መታሰር የመጀመሪያዬ አይደለም። በዚህ ዓይነት ትግል ውስጥ ላለፉት 31 ዓመታት ቆይቻለሁ። ወደ 6 ጊዜ ስለታሰርኩ ለእኔ አዲስ ነገር አይደለም።

ከእኔ ጋር በመግለጫ የተጠቀሱ ግለሰቦች እየታደኑ እያተሰሩ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ኤርፖርት የሚጠብቀኝ ፖሊስ እንደሚሆንና እንደምታሰር አውቃለሁ። ለዚህ የሥነ ልቦና ዝግጅት አለኝ።"
ቢቢሲ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.7K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:20:31 ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልልን ጨምሮ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች እና አአካባቢያዊ ምርጫን በ2016 ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱን አስታውቋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.7K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:20:23
ፕሬዝዳንት ፑቲን “ምዕራባውያን ሩሲያን ለማጥፋት እየሞከሩ ነው” አሉ

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሶቭየት ህብረትን የድል ቀን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት ፑቲን "እውነተኛ ጦርነት" በሩሲያ ላይ በድጋሚ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

ፑቲን አክለውም በፈረንጆቹ 1945 ሶቭየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀውን ድል ምዕራባውያን ዘንግተውታል ብለዋል።

ፑቲን ሞስኮ የወደፊት ሰላምን ማየት እንደምትፈልግ ገልጸዋል(አልአይን)።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.8K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 11:59:24 ሰሞኑን የትግራይ ታጣቂዎች እስከ ግንቦት 3 በሀይል ራያ አላማጣ እንገባለን በማለት ፕሮፖጋንዳ እየነዙ የነበረ ቢሆንም ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር ባደረግነው ውይይት መሰረት በርተክላይን መሳሪያ የያዘ ሰው አያልፍም የሚል ስምንት ላይ መድረሳቸውን ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። የሚመለሱ ተፈናቃዮች ቢኖሩ እንኳን መሳሪያ ሳይዙ በርተኽላይን አልፈው መግባት እንደሚችሉ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር ከስምምነት የተደረሰ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚደረግ የፕሮፓጋንዳ ሽብር አይጠቅምም ብለዋል።ትናንት በማይጨው ከተማ እና ገጠራማ አካባቢዎች ድሽቃ፣ብሬን እና ሞርታር የያዙ ታጣቂዎች መታየታቸውን ትናንት መዘገቤ ይታወሳል(አዩ)።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ