Get Mystery Box with random crypto!

አጣዬ ' ከማረሚያ ቤቱ ካመለጡ ታራሚዎች የተወሰኑት በፍቃዳቸው ተመልሰዋል አጣየ ማረሚያ ቤት በ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

አጣዬ
" ከማረሚያ ቤቱ ካመለጡ ታራሚዎች የተወሰኑት በፍቃዳቸው ተመልሰዋል
አጣየ ማረሚያ ቤት በድጋሚ ወደ ስራ መግባቱንና ታራሚዎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የአጣየ ማረሚያ ቤት ጥበቃ መረጃ እና ደህንነት ቡድን መሪ የሆኑት ዋና ኢንስቴክተር ቁምላቸው ጌጤ ተናግረዋል ፡፡በአጣየ ማረሚያ ቤት በከተማው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተነሳ ማረሚያ ቤቱ በእሳት ተቃጥሎ እና ታራሚዎች ወደ መሃል ሜዳ ተዘዋውረው እንዲሁም የተወሰኑት አምልጠው የነበረ መሆኑ ተጠቁሟል ።

አያይዘውም በመሀል ሜዳ አንድ መቶ አስራ ስምንት ታራሚዎች ወደ ማረሚያ ቤቱ የተመለሱ ሲሆኑ ከነዚህም ዉስጥ አብዛኛዎች አምልጠው የነበሩ እና በፍቃዳቸው የተመለሱት እንደሚገኙበትም ተገለጿል።

በአጣየ ከተማ በአሁን ወቅት አንጻራዊ ሰላም ቢኖርም ወደ ቀደሞ የከተማዉ የንግድ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል/ዳጉ ጆርናል)

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA