Get Mystery Box with random crypto!

የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ ጭማሪ ነዋሪዎችን እያማረረ ነው በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ የግል ት/ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ ጭማሪ ነዋሪዎችን እያማረረ ነው
በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ የግል ት/ቤቶች ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአብዛኛው  ከ50 እስከ 100 ፐርሰንት የሚደርስ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ እንደሚያደርጉ ለወላጆች ማሳወቃቸው ከፍተኛ አለመግባባትና ቅሬታን ፈጥሯል። በአንዳንድ ት/ቤቶች ስብሰባው ባለመግባባት ተበትኗል።

በት/ቤቶቹ በኩል ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የዋጋ ጭማሪ በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በመከልከላቸው ለመምህራን ደመወዝ ለመጨመር፣ ከዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ ለተከሰተው የአስተዳደራዊ ወጪ ንረት ለመሸፈን መቸገራቸውን በመግለፅ ጭማሪ የማድረጋቸውን ትክክለኝነት ያስረዳሉ።
በወላጆች በኩል እየተጠየቀ ያለው ጭማሪ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን፣ የዋጋ ግሽበቱ ስለባ የሆኑት ወላጆችም ጭምር መሆናቸውን በመጥቀስ የተጋነነ ጭማሪውን እንደማይቀበሉት መናገራቸው ተሰምቷል። በአንዳንድ ት/ቤቶች ወላጆች ከ30 በመቶ በላይ ጭማሪ መጠየቅ እንደሌለባቸው ፍላጎታቸውን ገልፀዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA