Get Mystery Box with random crypto!

ባሻዬ! መንግሥታችን ከአንድም ሁለት ቤተመንግሥት ለመሥራት ሥራ መጀመሩን ዘግይቶም ቢሆን ሰማሁ። ሃ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

ባሻዬ! መንግሥታችን ከአንድም ሁለት ቤተመንግሥት ለመሥራት ሥራ መጀመሩን ዘግይቶም ቢሆን ሰማሁ። ሃሳቡ ግሩምና ድንቅ ነው።

እኛ በሞቀ ቤት እየኖርን ምስኪኑ መንግሥታችን ምንም ቤት ሳይኖረው እስከዛሬ ማስተዳደሩ የሚያስመሰግነው ነው።

ባሻዬ! አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ፣

ራስ መስፍን ስለሺ የወደፊት መቃብራቸውን ደብረ ሊባኖስ በተክለ ኃይማኖት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ አስገነቡ።

አንድ ቀን ጃንሆይ ቤተክርስቲያኗን ሊሳለሙ ሲመጡ ራስ መስፍን አገኟቸውና እንዲህ አሏቸው "ጃንሆይ! የወደፊት የዘላለም ማረፊያ ቤቴን እዩልኝ"

ጃንሆይ የራስ መስፍንን የወደፊት መኖሪያ አዩና "ወደፊት ስትሞት እዚች ቤተክርስቲያን ውስጥ ለመቀብርህ እንዴት እርግጠኛ ሆንክ?" ብለው መለሱላቸው።

ዕውነትም ራስ መስፍን ስለሺ በደርግ ጥይት ተገድለው የትም ተጥለው ቀሩ።

ባሻዬ! የጻፍኩልህን ታሪክና ይሄንን ፎቶ እንዳታገናኝብኝ አደራ! ለራሴ ጤንነት እየተሰማኝ አይደለም።
Via Tesefay Hailemariam

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    @Dani_peromotor
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA