Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-19 11:54:21 አንዱዓለም አራጌ እና ኢዜማ ተለያዩ
ለ ኢዜማ የአዲስ አበባ ምርጫ ክልል 12/13 ሊቀመንበር አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- ከአባልነት መልቀቅን ስለማሳወቅ፦

ክቡርነትዎ እንደሚገነዘቡት፣ በኢትዮጵያ ረጅም የህላዊ ዘመን ውስጥ በፓለቲካ ሰማያችን ላይ የደቀደቀውን የሚዳሰስ የአገዛዝ ጨለማ ለመግፈፍ የማያልቁ የሚመስሉ ረጃጅም የመከራ ሌሊቶችን ብናሳልፍም፣ ይልቁንም ጨለማው በርትቶ የነፃነት ጀምበርም ከአድማሳችን እጅግ ርቃ በጭቆና ጥቀርሻ መቀበሯ ጥልቅ ህመም ቢፈጥርብን፤ ለሀገራችን የንጋት ኮኮብ ሆኖ፣ ሕዝባችንንም ከአገዛዝ ቀምበር አላቆ በፍቅር፤ በፍትህና በወንድማማችነት ኮረብታዎች ላይ ግዘፍ ነስታ የምትቆም፣ ያለፉትንም የሃሩር ዘመናት የምታስረሳ ኢትዮጵያ እንድትጠባ ከልብ በመሻት ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)ን መመስረታችን ይታወቃል።

እኔም ኢዜማን ከመጠንሰስ እስከ መመሥረት፣ ከምሥረታ በኋላም ወረዳችንን በአባልነት ፓርቲያችንን በአመራርነት እስከማገልገል የዘለቀ አቅም የፈቀደውን እንቅስቃሴ ማድረጌም ይታወሳል። የቆዩ ስህተቶችን በፓርቲያችን ውስጥ ላለመድገሞ እንዲሁም የህልሞቻችን ሁሉ በኩር የሆነውን ሰብዓዊ ልእልና የነገሠባት ኢትዮጵያን በእርግጠኝነት እውን ለማድረግ በሰከነና በተጠና መንገድ ለመራመድ ከፍ ያለ ጥረት ስናደርግ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በአጋዛዝ ውስጥ ተወልዶ በአገዛዝ መዳፍ ውስጥ እንደ ሸበተ ትውልድ እፍኛችንን የሞላው ጉም ነው ወይንስ የሚጨበጥ ተስፋ የሚለውን ጉዳይ ለመገምገም ፈፅሞ በዚያ መጠን መቸገር ሳይገባን አላስፈላጊ የህልም ሩጫ የሚመሰሉ የሃሳብ ልፊያዎችን ለማድረግ ተገደን ቆይተናል፡፡

ሁኔታዎችን በውይይትና በሀሳብ ፍጭት ለመፍታት መሥራቱ የሚከበርና እንደ ፖለቲካ ባህልም ልናዳብረው የሚገባ መሆኑ እሙን ነው፡፡ይሁን እንጂ ምንም እንኳን በጭንቅም ቢሆን ዛሬ ላይ ቆመን በምልሰት የክርክሮቻችን መቋጫና ውጤቱም ምን እንደሆነ እያየን ቢሆንም፣ በወቅቱ አንኳር በሚሰኙ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በድምፅ ለመሸናናፍ ያደርግናቸው እልህ አስጨራሽ ፍልሚያዎች የፓርቲው አዎንታዊ መገለጫዎች ናቸው ብዬ እወስዳለሁ፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሁሉ መድህን ለመሆን ከሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በተገኙ አባላት የተመሰረተ ፓርቲ ኢትዮጵያ በየትኛውም የታሪክ ድርሳን ላይ ከሰፈረው መከራዋ ሁሉ የከፋውን በምታስተናግድበት በዚህ ዘመን፣ የክብር ፈርጦቿ ሲረግፉና ፀንታ የቆመችባቸው አምዶች በአገዛዝ መዶሻ ሲፈረካከሱ፤ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግ ፤ ታግሎ ሕዝቡን በማታገል ከደመና በላይ አንገታቸውንና ልባቸውን አደንድነው፣ በፈርዖን ሰረገላ ላይ ተዘልለው ፣ ሕዝቡን ወደ ቀይ ባህር ዳርቻ በማሳደድ ሀቅላቸውን የሳቱ ገዢዎች ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ እና ለሁላችንም ድህነት ይሆን ዘንድ መሥራት ቢጠበቅበትም ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ሆኖ የተሳከረ ሚና በመጫወት እየተንጎላጀ ይገኛል ።

እኛም እንዳቀድነው፣ ሕዝባችንም አብዝቶ እንደተመኘው፣ አገዛዝንና ከእርሱም የሚታጨደውን ሰቆቃ በማምከን በሀገራችን ሰማይ ሥር እውነተኛ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ይሰፍን ዘንድ አመርቂ የሚባል አስተዋፅኦ ለማድረግ አለመቻሉ እንዳለ ሆኖ፣ እንደ “የበዐል ነቢያት” አገዛዝን ከቦ እያሸበሽበ፣ የአገዛዝ ጡጫ እንዲፈረጥም ማድረጉ ለብዙዎች ፍች ያልተገኘለት ቅዠት ሆኖአል። ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ ከስሁት መንገዱ ለመመለስ በማይችልበት መዳፍ ውስጥ መጨመቁ ነው። ያነሳኋቸውንና ነገሬን ላለማርዘም እንዲሁም ከተገቢነት አንፃር መዝኘ የተውኳቸውን ሀሳቦች ግንዛቤ ወስጥ በመክተት ደጋግሜ የሁኔታ ትንታኔ ብሰራም የኢዜማ ስብራት ሲጠገን ለማየት አልቻልኩም ። ለመላምታዊ ጥያቄዎቼም አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት ባለመቻሌም አዝናለሁ፡፡

ክቡርነተዎ እንደሚያውቁት፣ የፖለቲካው አውሎ ነፋስ ገና ከሩቅ ግሳንግሱን እየጠራረገ ሲመዘገዘግ፣ የለም የፓርቲያችንን ቁመናና አሰላለፍ ከወዲሁ እናስተካክል የሚል ተማጽኖ ከማቅረብም ባለፈ በአባላት ፊት ቀርቤ ብሞግትም የሚገባውን ድጋፍ ባለማግኘቴ ውሳኔያቸውን በጸጋ ተቀብዬ በአባልነት መቀጠሌ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከፍ ብዬ ካወሳኋቸው ምክንያቶችበተጨማሪ በእለት ከእለት ውሎዬ የማገኛቸው ዜጎች ሁሉ አሁንም የፓርቲው አመራር አባል እንደሆንኩ እንደሚቆጥሩ ለመገንዘብ ችዬአለሁ፡፡ በመሆኑም በሌለሁበት እርምጃ የውግዘትም ሆነ የውዳሴው ተቋዳሽ ለመሆን አልሻም። ስለሆነም ከዚህ በላይ ሳልዘገይ ነገሮች እንደየዘርፋቸው ማሰቀመጥ ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። በሌላ በኩል እንደጠቀስኩት ኢዜማን አይነ -ግቡና ዘመን ተሻጋሪ ለማድረግ የሰነቅነው ህልም እውን ይሆናል ወይ? በሚለው ጉዳይ ላይ ደጋግሜ የሠራሁት የሁኔታ ትንታኔ አዎንታዊ ምላሽ ሊያስገኝልኝ ባልቻለበት ሁኔታ ኢዜማ ውስጥ መቀጠሉ ትርጉም የሚሰጥ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡

በመሆኑም ይህን በመሰለ ሁኔታ ተጨማሪ ቀናትን በኢዜማ ጣራ ሥር መቀጠል የሚያስችለኝ አንዳች አይነት ምክንያት አልቀረኝም።ክቡርነተዎ ፈቃድዎ ቢሆን ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ በተለያዬ ደረጃ ለሚገኙ የኢዜማ ቤተሰቦች መልእክት ለማስተላለፍ እወዳለሁ ፤ለተወደዳችሁ የኢዜማ አባላት፤ አብረን የተለምነው መንገድ የነጠረ የሚባል አይነት ቢሆንም ፤ ከስልት አንፃር የተከተልነው መሰመር እሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ እንዳደረገን በቀና ልቦና በሕዝባችን ዘንድ ያለንን ሥፍራ መረዳት ብቻ ብዙ ይናገራል፤ ሕዝብ ምን ፍሬ አለው ካላልን በስተቀር። በመሆኑም ብዙ ድንቅ የሚባሉ ጊዜዎችን አብረን ብናሳልፍም ከፍ ብዬ በገለፅኳቸው ምክንያቶች አብሬያችሁ ልጓዝ ባለመቻሌ በጣም አዝናለሁ! እዚህ ውሳኔ ላይ መድረስ ፈጽሞ ቀላል እንዳልነበረም ልገልፅላችሁ እወዳለሁ፡፡ከእናንተ ጋር ያሳለፍኳቸው ውስን የትግል አመታት በሕይወቴ ትልቅ ቦታ የምሰጣቸውና ሁልጌዜም አክብሮቴን የምቸራቸው እንደሆኑ እገልፅ ዘንድ ይገባኛል፡፡ እንዲሁም በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኜም ቢሆን ፣ ከልብ ባዘንኩባቸው ጊዜያትም እንኳን ሳይቀር ለእናንተ ያለኝ ፍቅር አለመቀየሩን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡

ፓርቲውን በሃላፊነት እንዳገለግል ለሰጣችሁኝ እድል፣ ላሳያችሁኝ ፍቅርና በጎነት ሁሉ ከልብ አመሠግናለሁ፡፡ አብረን ባሳለፍናቸው አመታት ቅር ያሰኘኋችሁ ወንድሞችና እህቶች ካላችሁ በዚህ አጋጣሚ ከልቤ ዝቅ ብዬ ይቅርታ ልጠይቃችሁ እወዳለሁ፡፡ የእኔ የሁኔታ ትንታኔ ስህተት ሆኖ ያቀዳችሁት ሁሉ ተሳክቶ ኢዜማም የእውነት ዘመን ተሻጋሪ፤ አይነ- ግቡና ለኢትዮጵያ ሕዝብም መድህን እንዲሆን የምታደርጉት ጥረት እንዲሳካ ከልብ እመኛለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ በተለያየ መንገድ ፣ በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ኢዜማን ስትደግፉ አብሬያችሁ ለመሥራት እድሉ ለገጠመኝ ለማከብራችሁና ለምወዳችሁ ወገኖቼ ሁሉ ከብዙዎቻችሁ ጋር ለመሥራት መቻሌን ከፈጣሪ እንደተቸረኝ ትልቅ ጸጋ እቆጥረዋለሁ፡፡ ምናልባትም ከእኔ ከዚህ በላይ ጠብቃችሁ የጎደለ ነገር ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡

በምርጫ ወረዳ 12/13 እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሳይገባኝ ለለገሳችሁኝ ከፍ ያለ አክብሮትና ፍቅር ከልብ እያመሰገንኩ ፍቅርና አክበሮቴ እጥፍ ተባዝቶ ይድረሳችሁ! በተፈጠረው ሁኔታ ስለሚያድርባችሁ ቅሬታ ሁሉ ይቅርታ እየጠየቅኩ አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝ ለተሠሩ ግድፈቶች ሁሉ ሃላፊነት ለመዉሰድ ዝግጁ መሆኔን ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

አንዱአለም አራጌ የኢዜማ የቀድሞ አባል
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.5K viewsedited  08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:04:48 የተመድ ዋና ጸሀፊ ወደ ትግራይ ለመጓዝ ይዘውት የነበረው እቅድ፤ በኢትዮጵያ መንግስት “ውድቅ መደረጉን” አንድ ምስጢራዊ ሰነድ አጋለጠ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፤ ወደ ትግራይ ለመጓዝ የያዙት እቅድ በኢትዮጵያ መንግስት ውድቅ በመደረጉ “ክፉኛ ተበሳጭተው” እንደነበር “ዋሽንግተን ፖስት” ጋዜጣ የተመለከተው አንድ ምስጢራዊ ሰነድ አጋለጠ። የዋና ጸሀፊው ጥያቄ በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት አለማግኘቱን በመግለጽ ለጉተሬዝ ደብዳቤ የጻፉላቸው፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መሆናቸው በዚሁ ምስጢራዊ ሰነድ ይፋ ተደርጓል።

ጉተሬዝ የትግራይ ጉብኝታቸው መሰረዙን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የነበሯቸውን መስተጋብሮች የያዙት ምስጢራዊ ሰነዶች አፈትልከው የወጡት ከአሜሪካ መንግስት እጅ ነው። “ዲስኮርድ” በተሰኘው የመልዕክት መለዋወጫ “ሰርቨር” የተለቀቁትን እነዚህን ሰነዶች ያወጣው፤ የማሳቹሴትስ የአየር ኃይል ብሔራዊ ዘብ ባልደረባ የነበረ የ21 ዓመት ወጣት ነው።

አሜሪካ “በወዳጆቿ እና አጋሮቿ ላይ ስታካሄድ የቆየችውን ስለላ ያጋለጡ ናቸው” ከተባለላቸው ሰነዶች መካከል አራቱ፤ ከጉተሬዝ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን “ዋሽንግተን ፖስት” ትላንት ሰኞ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል። የካቲት 10፤ 2015 የተጠናቀረ አንድ ሪፖርትን በማሳያነት የጠቀሰው ዘገባው፤ ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያደርጉት ያቀዱት ጉዞ መሰረዙን በተመለከተ፤ በወቅቱ በተመድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ታዬ ታዬ አጽቀስላሴን ለመጋፈጥ ፈልገው እንደነበር አትቷል።

ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያቀኑ አቅደው የነበረው፤ በክልሉ የነበረውን ጦርነት ላስቆመው የሰላም ስምምነት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ነበር ተብሏል። ንደ “ዋሽንግተን ፖስት” ዘገባ ከሆነ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ እቅድ የተጨናገፈው፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጉብኝቱን ውድቅ የሚያደርግ ደብዳቤ ከላኩላቸው በኋላ ነው(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)።
ሚያዝያ 11/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.2K views08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:04:48
3.0K views08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 05:19:47
የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጡ ሰብአዊ መብት የሚጥስ ነው ሲል አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በተመረጡ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለዉን ማዕቀብ እንዲያነሳም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠይቋል።አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት እገዳዉን ከጣለ 3ኛ ወሩን ይዟል።እገዳዉ ሰዎች መረጃ እንዳያገኙ መገደብን ጨምሮ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና ያለመጠቀም የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነዉ ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዉሞን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብትን እንዲያከብርና የታሰሩ የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን እንዲፈታ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ትናንት ማምሻ ባወጣዉ መገለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት አማራ ክልል በተፈጠረዉ ሁከት ምክንያት ያሰሯቸዉን 7 የመገናኛ ዘዴ ባልደረቦች ባስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ከእስረኞቹ ባንዷ ላይ ተፈፀመ የተባለዉን አካላዊ ጥቃት እንዲያጣሩ ጠይቋል።

መግለጫዉ እንዳለዉ ባለስልጣናቱ «ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና ሁሉም ወገን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብቱን ማስከበር አለባቸዉ።»ባለፈዉ ሳምንት በአማራ ክልል የመብት ጥሰትና ሁከት መቀስቀሱ እንዳሳሰበዉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታዉቋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉ፣ የሰብአዊ ርዳታ አቀባይ ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ ሰዎች መገደላቸዉ፣ አዲስ አበባ ዉስጥ ሰዎች በጅምላ መታሰራቸዉንም ድርጅቱ «አሳሳቢ» ብሎታል።የመንግስት ኃይላትም ሆኑ ሌሎች ታጣቂዎች «የሰብአዊ ርዳታ ሰራተኞችን ያለማጥቃት ኃላፊነት አለባቸዉ።» ይላል መግለጫዉ።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
784 views02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 05:19:33 በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ

በጦርነቱ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መድረሱ ተገልጿል

ከተቀሰቀሰ አራተኛ ቀኑን በያዘዉ የሱዳን የከተማ ዉስጥ ጦርነት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና የአገሪቱ ጦር ዉግያ ዉስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ በሆነችዉ ሱዳን ኢትዮጵያዊንም ህይወታቸዉ እንዳለፈ ተሰምቷል።

በሱዳን 12 ዓመታትን የቆየዉና አስተያየቱን ለብስራት ራዲዮ የሰጠው የጤና ባለሙያ ወንድወሰን ጌትነት፤ ከትናንት በስቲያ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ኦምዱርማን በተሰኘዉ አካባቢ በጦርነቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን በጦር ጄት ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ተናግሯል። እስካሁን ከ10 በላይ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ ሞተዋል ያለም ሲሆን፤ በትናትናዉ ዕለት በካርቱም ( ጅሬፍ ) በደረሰ ሌላ ጥቃት፤ ባለትዳሮች ሕይወታቸውን ሲያጡ የሦሥት ዓመት ሕጻን ልጃቸዉ ከጥቃቱ መትረፉን ገልጿል።

በተጨማሪም በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይም ጥቃት መድረሱን የገለጸው ወንድወሰን፤ የትኞቹ ታጣቂዎች እንደፈጸሙት ባያረጋግጥም የኤምባሲዉን ቅጥር ግቢ ጥሰዉ በመግባት በግቢዉ በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባለቤት በሆነበት የመጠለያ ማዕከል ዉስጥ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ አጸያፊ ተግባራት ጭምር መፈጸማቸዉን ተናግሯል።

የኤምባሲዉ ጥበቃዎች በጦርነቱ ወቅት ከግዳጅ ቦታቸዉ በመነሳታቸዉ የተባለዉ ጥቃት መድረሱንና፤ ታጣቂዎቹ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ዘረፋዎችን መፈጸማቸዉንም ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን ልዩ ተወካይ ባወጣው መረጃ፤ በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት እስከ አሁን በትንሹ 200 ሰዎች መሞታቸው የገለጸ ሲሆን፤ 1 ሺሕ 8 መቶ ያህል ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸዉን አስታውቋል፡፡

አዲስ ማለዳ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
758 views02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 05:19:33
717 views02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:18:03
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ማንነትን መሰረት ያደረገ እስር መደረጉ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል። ዛሬ አመሻሽ ዮሃንስ የሚባል የህግ ተማሪ መታሰሩን እና ሌሎችም እንደታሰሩ ምንጮች ለሰበር ዜና ET ገልፀዋል።
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.1K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 20:41:20
40 ሺ ብር የወጣበት ሰንጋ 53ሺ ብር ሚያወጣ ወርቅ ሆዱ ውስጥ ተገኘ።
በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶንሾ ቀበሌ ለበዓል ከታረደ ሰንጋ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ተገኝቷል። ለባለቤቶቹ 53 ሺ ብር ገቢ አስገኝቶ ከወጣበት በላይ አስገቷል ተብሏል።

ይህ ነገር በሳይንስ እንዴት ይታያል ለሚለው ጥያቄ በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ አሰላ የሚገኘው የእንስሳት ጤና ጥበቃ ማዕከላዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ የእንስሳት ሐኪም ዘሰጡት አስተያየት።

"በረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ትንንሽ ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች ስለሚመገቡ ከቆይታ ብዛት ወደ ወርቅ ይለወጣል. ብለዋል ። "

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.2K views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 19:21:30 አምነስቲ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአማራ ክልል በቅርቡ ከተቀሰቀሰው ሁከት ጋር በተያያዘ የታሠሩ ሰባት የመገናኛ ብዙኀን ሠራተኞችን ባስቸኳይ ከእስር እንዲለቁ አዲስ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። አምነስቲ፣ ባለሥልጣናቱ ባንዲት አንስት ጋዜጠኛ ላይ ተፈጸመ የተባለውን አካላዊ ጥቃትም እንዲያጣሩ ጠይቋል። መንግሥት "የኹሉንም ዜጎች ሃሳብን የመግለጽና ሰላማዊ ተቃውሞ የማድረግ መብት" እንዲያከብርም አምነስቲ ጥሪ አድርጓል። ድርጅቱ፣ በአማራ ክልል በቅርቡ የተደረጉ የተኩስ ልውውጦችና ሁለት ረድኤት ሠራተኞች በክልሉ ውስጥ መገደላቸውም እንዳሳሰበው ገልጧል(wazema)።
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.3K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 19:21:03 የተለያዩ አገራት ሱዳን የሚገኙ ዜጎቻቸው ደኅንነት እንዳሳሰባቸው በመግለጽ ላይ ናቸው። ኬንያ ግጭቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ ከተባባሰ 30 ሺህ ዜጎቿን ከአገሪቱ የሚያስወጣ ግብረ ኃይል ማቋቋሟን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ግብረ ኃይሉ እስከዚያው ለኬንያዊያኑ የአስቸኳይ ዕርዳታ አቅርቦትን እንደሚያስተባብር የገለጡት ዘገባዎቹ፣ እስካሁን ባለው መረጃ በግጭቱ የተገደለ ኬንያዊ እንደሌለ ጠቅሰዋል። ባሁኑ ወቅት የሱዳን የአየር ክልል ዝግ ሲሆን፣ የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያም የግጭት ቀጠና ኾኗል። በተመሳሳይ፣ የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደዔታ ምስጋኑ አረጋ በኢትዮጵያ ከሱዳን አምባሳደር ጋር ትናንት ባደረጉት ውይይት፣ በአገሪቱ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ደኅንነት እንዳነሱላቸው ሚንስቴሩ ገልጧል። አራተኛ ቀኑን በያዘው ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 እንዳለፈ መረጃዎች ያመለክታሉ።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.2K viewsedited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ